አባል ውይይት:Samson25

Page contents not supported in other languages.
ከውክፔዲያ

ወደ አማርኛ ውክፔድያ እንኳን ደህና መጡ! ይህንን ውክፔዲያ (ዊኪ) ፕሮዤ በማሻሻልና በማዘጋጀት ደስ እንደሚያስኝዎ ተስፋ አለኝ። እነዚህ ገጾች በተለይ ይጠቅሞታል።

ምንም ጊዜ ስለ ማንኛውም ጉዳይ ጥያቄ ካለዎት፣ በእኔ ወይም በሌላ መጋቢ ውይይት ገጽ ላይ ከመጠየቅ አይቆጠቡ!


Welcome to Amharic Wikipedia! I hope you enjoy improving and editing this Wikipedia project. These pages are especially useful for those who are literate in Amharic. However, even experienced Wikipedians who don't know any Amharic have helped out with other things, like 'Interwikis' and updating images from Commons, etc. So don't be afraid to improve the wiki any way you can! Remember, someone else can always come later and fix any changes you make that are not perfect.

You can set your own language for the interface at Special:Preferences. Just scroll in the box where it says 'am - አማርኛ' until you see your language, then click the ይቆጠብ (save) button at the bottom!

Feel free to use our Sandbox to make test edits. If you want to talk with other members in general, for now you can use the Village pump. Sign your name on any Talk pages by just typing '~~~~' (four tildes) at the end of your message.

If you have any questions about anything, don't hesitate to ask on my or another administrator's Talk page. Happy editing! With regards, --ፈቃደ (ውይይት) 20:31, 28 ጁላይ 2010 (UTC)[reply]

አበበ ቢቂላ[ኮድ አርም]

ሰላም ሳምሶን25፤ አበበ ቢቂላ በሚል አርስት ያዘጋጀኸውን አነበብኩት። አንተ የጻፍከውን 1ኛ ዘመናትን ወደኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በመለወጥ 2ኛ ትርጓሜውን በ'ቀለለ' አማርኛ በማስተካከል 3ኛ ስሕተት የሆኑትን ጽሑፎች በማረም 4ኛ የተደጋገሙ ጉዳዮችን በማጣመር ወይም በመሰረዝ ወ.ዘ.ተ. አሻሽየዋለሁ። ጽሁፉ ረጅም ስለሆነ በቀጥታ ወይም ሳላማክርህ ያንተን ጽሑፍ ለመሰረዝ አልፈልኩም። የኔን ሥራ ሻምበል አበበ ቢቂላ በሚል አርስት ለጥፌዋለሁና እባክህ ካነበብከው በህዋላ እንዳለ ቆርጠህ አበበ ቢቂላ የሚለውን ያንተን ጽሑፍ ተካበት። የሚያስቸግር ወይም የማትስማማበት ከሆነ አስታውቀኝ። ከአክብሮት ጋር --Bulgew1 18:57, 3 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

ሰላም Bulgew1 መልእክትህ ደርሶኛል ጽሁፍንህም አንብቤዋለሁ የኔ የፊደል ገበታ (keyboard)የአማርኛ ቁጥር አይጽፍም ስለዚህ ዓ/ም ብትቀይረው በጣም ነው ደስ የሚለኝ ተደጋጋሚ ጉዳዮች ላልከው ይሄን ታሪክ ከ wikipedia & answer.com ላይ ነው ያገኘሁትን ሁለቱንም እንዳቅሜ ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ። ያንተም ጽሁፍ አንብቤዋለሁ ነገር ግን አንዱን መሰረዝ ለምን አስፈለገ ሌሎች ሰዎችም መጥተው ቢጽፉ ማበረታት ነው የሚያስፈልገው። በጥቅሱ ውስጥ እንደገለጽኩት የሺህ አመት መኩሪያችን ነው። እኔ ሁለቱም ይቀምጥ ነው የምለው አንባቢው ሁለቱንም አንብቦ የሐሳብ አድማሱን እንዲያሰፋ። የአበበ ቢቂላ ታሪክ በ ሁለት ገጽ የሚያልቅ አይደለም። ከአክብሮት ጋር:Samson25 20:55, 3 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

ሳምሶን25 ስለመልዕክትህ አመሰግናለሁ። አንደኛው ጉዳይ ዘመናትን በአማርና ቁጥር መጻፍ ብቻ ሳይሆን በጎርጎራዊ አቆጣጠር በጽሑፉ ምንጭ የሠፈሩትን በተቻለ መጠን አማርኛ ዊኪ ላይ እንደኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በመመንዘር እንድንጠቀምም ነው። በነገራችን ላይ በቀጥታ ዊኪው ገጽ ላይ ለመሚጽፍ የግዕዝ ቁጥሮች 'ቀላል መጨመሪያ' በሚለው ሰንጠረዥ ላይ ይገኛሉ። በሌላ የግዕዝ ሶፍትዌር ከሆነ የምትጽፈው እነዚህም ላይ አብዛኛውን ጊዜ (insert)እና (symbol) የሚሉት ምርጫዎች የግዕዝ ቁጥሮችን ያምጣሉ። ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ የትርጓሜው አጻጻፍ በአማርኛ አንባቢ ሲነበብ በቀላሉ አቀነባበሩንና ፍሬ ነገሩ እንዲገባው ማድረግም ነው። እንኚህን ጉዳዮች አንተ ያዘጋጀሀው ጽሑፍ ላይ ማስተካከል ይቻላል፣ ነገር ግን ጽሑፉ ብዙ በመሆኑ የቀለለኝ ወደ ወርድ ቀድቶ ማስተካከል ስልነበረ ነው። በሁለቱም ዕትሞች ላይ የሠፈረው ፍሬ ነገር ከአቀነባበርና ከአንዳንድ የተጨባጭ ሀተታ ስህተቶች በስተቀር ተመሳሳይ ስለሆነ (የኔም ቅጂ ካንተው ጽሑፍ የመነጨ ነው)ሁለቱንም ገጾች መተው በእኔ አስተያየት አንባቢውን ከማደናበር በስተቀር ጥቅም ያለው አይመስለኝም።--Bulgew1 22:13, 3 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]


Bulgew1 ጥያቀህን ራስህ መለስከው (የኔም ቅጂ ካንተው ጽሑፍ የመነጨ ነው)ሁለቱንም ገጾች መተው በእኔ አስተያየት አንባቢውን ከማደናበር በስተቀር ጥቅም ያለው አይመስለኝም። ለምን ለአንባቢው ምርጫ አንሰጠውም? አንተ የኔን ጽሁፍ አንብበህ ተረድተህ እዚህ ጋ እንዲህ ቢሆን ወይም ቢባል ጥሩ ነበር ብለህ ሌላም ታማኝ ምንጮች ጠቅሰህ ጻፍክ http://www.ethiopianreporter.com/index.php?option=com_content&view=article& ይሄም በመሆኑ ለሚያነበው ሰው ሰፊ ምርጫ እና ብዙ መረጃ ሰጠንው ብዬ ነው እኔ የማስበው። ሌላው እኔ የስነ ጽሁፍ ሰው አይደለሁም ስለዚህ ብሳሳት አይገርመኝም። እንደሌሎቹ እጄን አጣጥፌ ከዳር ቆሜ ብመለከት ክ እንደዚህ አይነቱ ክርክር ራሴን አድናለሁ። ለእናንተም ራስ ምታት ከመሆን እድናለሁ ብዬ አስባለሁ። ለመሆኑ ያልገባህ የትኛው ክፍል ነው በቀላል አማርኛ አልተጻፈም ያልከው? ያንተ ጽሁፍ እኮ ዛሬ ነው የተጻፈው ስላንተ ጽሁፍስ አስተያየት የሰጠ የለም? ሰለ ምክርህ አመሰግናለሁ ። ሴትየዋ "እኔ ካላቦካሁት አይጣፍጥም አለች አሉ"  :Samson25 22:56, 3 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

ሁለታችሁን በማያስከፋ መልኩ የራሴን አስተያየት ልሰጥ አሰብኩና በኋላ ሳስበው ወይ አንዳችሁን ወይም ሁለታችሁን ማስቀየሜ የማይቀር ሆኖ ተሰማኝ። ግን የተሰማኝን ስሜት ከመግለጽ ወደሁዋላ ማለትን አልፈለኩም። በኔ አስተያየት Samson25 በጣም ለፍቶ ብዙ ጽሁፍ አቅርቧል። Bulgew1 ደግሞ በጥሩ ችሎታ ጽሁፉን አርሟል። ስለዚህ የሁለታችሁንም አስተዋጾ በማይቀንስ መልኩ፣ የቡልጌውን እርማት ከሳምሶን25 ጽሁፍ ጋር በማቀናበር አዲሱ ርዕስ ላይ ሳይሆን የቀድሞው ርዕስ ላይ ቢቀርብ ጥሩ ነው። አዲስ ርዕስ መከፍቱ ሳምሶን የለፋበትን ስራ ዋጋ ቢስ ያደርገዋል። የቡልጌው ጽሁፍ ቢጠፋ ደግሞ በጣም በጥሩ ሁኔታ ያስተካከለው ጽሁፍ መጥፋቱ ነው። ስለዚህ ሁለቱ ቢቀናበሩ ጥሩ ነው እላለሁ።
በሁለተኛ ደረጃ ሳምሶን "እናንተ" ብለህ ጽፈሃል። እኔ በበኩሌ እስካሁን ድረስ የ"ቡድን" ስራ ሲሰራ በዚህ ባማርኛው ዊኪፒዲያ ላይ አላየሁም። የየግላችንን ነጻነት የሚንካ መቧደን ሲፈጠር፣ እኔ እራሴ መሳተፍ አቆማለሁ። እዚህ ቡድን የለም። ሁላችንም በግል ነው የምንሳተፈው። ቢያንስ ቢያንስ እኔ በዚያ አምናለሁ።Hgetnet 23:47, 3 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]


ሰላምHgetnet በጣም አመሰግናለሁ ሰለ አስተያየትህ። ፍርድ ልትፈርድ ከመጣህ ሳትፈራ ማንንም አስቀይማለሁ ሳትል በትክክል መፍረድ ነው። እኔ ጽሁፎችን ስተረጉም ለእኔ እንደገባኝ እና እውነቱን ሳለቅ በተቻለኝ መጠን ለአንባቢው ለማቅረብ እሞክራለሁ። ሰለ አበበ ቢቂላም ያደረኩት ይህንኑ ነው። ምንጩንም ታሪኩን ያገኘሁበትን በማመሳከሪያው ላይ አስቀምጠዋለሁ። ይህንንም የማደርገው ከእኔ የተሻለ ተርጓሚ ቢመጣ ምንጩን እንዲያገኘው ብዬ ነው። ስለዚህ በ Bulgew1 ጽሁፍ እኔ ችግር የለኝም ነገር ግን ያንተን አጥፋው ስትለኝ ግን "በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ አይነት ሆነብኝ" ያንተን ጽሁፍ አጥፋው የኔ ይቀመጥ!!!

Hgetnet በጣም አዝናለሁ ""እንደሌሎቹ እጄን አጣጥፌ ከዳር ቆሜ ብመለከት ክ እንደዚህ አይነቱ ክርክር ራሴን አድናለሁ። ለእናንተም ራስ ምታት ከመሆን እድናለሁ ብዬ አስባለሁ።"" ለእናንተም ያልኩት ለእንደ አንተ አይነቶች ለማለት ነው እንጂ አስተዳዳሪዎቹን ወይንም ተሳታፊዎችን በሙሉ ለመወንጀል አይደለም። ሌሎች አስተዳዳሪዎች ይህንን ውይይት አይተውት ጥፋተኛ ነህ ከተባልኩ ይቅርታ ለመጠየቅ እና እኔ የሰራኋቸውን ጽሁፎች በሙሉ አጥፍቼ ሁለተኛ በዚህ በኩል ላላልፍ ቃል ለመግባት ዝግጁ ነኝ። እኔ አልገባ ያለኝ ሁለቱም ቢቀመጥ ችግሩ ምንድነው?? Hgetnet ጊዜ ካለህ እኔ የጻፍኩትን አንብበህ ችግሩን ንገረኝ አብራራልኝ የ Bulgew1 ተመልከተው እኔ የሱ መጥፋት አለበት አላልኩም እሱ የኔን ጽሁፍ ለማጥፋት ምን አሳሰበው? አልገባ ያለኝ ይህ ነው። ከአክብሮት ጋር ፡Samson25 00:27, 4 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

እኔም ያልኩት ያንተ ርዕስ አይሰረዝ ግን የተሰተካከለው ጽሁፍ ካንተ ጽሁፍ ጋር ይቀናበር። አዲሱ ርዕስ አያስፈልግም ነው። የገመትኩት ሁለታችሁንም አላስቀይምም ብየ ነበር ግን አልተሳካም። ርግጠኛ ነኝ ቡልጌው1ንም አስቀይሜአለሁ። ግን ይህ የኔ አቋም ነው! Hgetnet 00:36, 4 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]


፡ Hgetnet ጥያቄዬን አልመለስክልኝም ሁለቱም ቢቀመጥ ችግሩ ምንድነው ? በነገራችን ላይ እኔ አልተቀየምኩም ግን የእኔ ጽሁፍ መሰረዝ ለምን እንዳስፈለገ ግን አልገባኝም። የዚህን መልስ ነው ከተሳታፊዎች ወይም ከአስተዳዳሪዎች ማወቅ የምፈልገው። ይሄ የራሱ ቃል ነው ከፍ ብለህ እየው (የኔም ቅጂ ካንተው ጽሑፍ የመነጨ ነው)የእኔ ጽሁፍ መጥፋት ካለበት የሱም አብሮ መጥፋት አለበት ባይ ነኝ ምክንያቱም ኮፒ እና ፔስት የተደረገ የኔ ጽሁፍ በመሆኑ። ፡Samson25 00:49, 4 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

ጥያቄውን ስለመለስኩና ከዚህ በላይ አስተያየት ስሌለኝ እዚህ ላይ አቆማለሁ። ላንተም ሆነ ለ Bulgew1 አድናቆትና ክብር እንጂ ሌላ ስሜት የለኝም። አመሰግናለሁ Hgetnet 00:58, 4 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]
ችግሩ እዚህ ላይ ነው Hgetnet አቋም ይዘሀል 100% መብትህ ነው ። ለ እኔ እንደገባኝ ያንተ አቋም ያንተ አርእስቱ ብቻ ይቀመጥ ነገር ግን ጽሁፉ (የራሴን ጽሁፍ)እሱ እንደጻፈው ተደርጎ የሱ ጽሁፍ ይቀመጥ ያንተ ይጥፋ ማለትህ ነው አይደልም? አያያዙን አይተህ ጭብጦውን ቀማው መሆኑ ነው? አመሰግናለሁ Hgetnet ሰላም ሁን ፡Samson25 01:09, 4 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

Samson25 ጽሑፍህን ለማረም መሞከሬና እና በሰፊው ደግሞ የአማርኛውን ዊኪ በማንኛውም መንገድ ለማዳበር መልፋታችን ካልቀረ በቋንቋችን ፊደላትና ቁጥሮች እየተጠቀምን አቀነባበሩንም ለአማርኛ አንባቢዎች በቀለለ ሁኔታ እናቅርብ ማለቴ ያንተን ስሜት ለመንካት ወይም በዚህ አርዕስት ላይ የሠራኸውን ሥራ ዋጋ ቢስ ለማድረግ አልነበረም። እስካሁን ያደረግነው የጽሑፍ ግንኙነት ግን ባንተ በኩል ስሜትህን የነካው ከሆነ በጣም አዝናለሁ። እንደሚመስለኝ የዊኪፔዲያ አሠራር ባንዱ የተዘጋጀ ጽሑፍና ያዘለውም ዕውቀት በሰፊው እንዲዳረስና ተጨማሪም ዕውቀት ከተሳታፊ አንባብያን ካለ እንዲጨምሩበት ሌሎችም ደግሞ ያዘለው ግድፈት ካለ ማረም እንዲችሉ ነው። በሌላ አባባል ሊጡን ማንም ያቡካው፣ ብቻ እንጀራው ይጣፍጥም ያጥግብም ነው ቁም ነገሩ። በመጀመሪያ መልዕክቴ ልገልጽልህ እንደሞከርኩት ጽሑፉ ረጅም ስለሆነና በእኔ አስተያየት የሚያስፈልገው የማሻሻል ሥራ በመላው የጽሑፉ አካል ላይ ሲሆን በዝግታ ከዊክፐድያ ውጭ (off line) አዘጋጅቶ መመለስ ነው። ይሄንን እርማት ደግሞ መልሶ አንተ ገጽ ላይ ማሥፈር ማለት ጽሑፉን የበለጠውን ፍቺ የለሽ ማድረግ ነው የሚሆነው። ያለው አማራጭ እንግዲህ በአዲስ ገጽ ላይ አስፍሮ አንተን ማማከርና እኔም የደከምኩበት እርማት ዋጋቢስ እንዳይሆን ማድረግ ነው። ይሄ ላንተ ስላልመሰለህ ወይም ስላልታየህ እጅግ በጣም አዝናለሁ! "ለመሆኑ ያልገባህ የትኛው ክፍል ነው በቀላል አማርኛ አልተጻፈም ያልከው?" ብለኸኛል። ለምሳሌ ያህል የሚከተለውን ክፍል ስንመለከት ያንተ ትርጉም ከሞላ ጎደል ቃል በቃል ከእንግሊዝኛው ዊኪፔድያ የተወሰደ ሲሆን የአማርኛው ትርጉም ፍሰት እና ይዘት ወይም አገባብ የሌለው ሆኖ እናገኘዋለን። “አበበ ቢቂላ ግን ለዚህ ማራቶን ውድድር ተሰለፈ። በዚህ ውድድር ግን ጫማ አድርጎ።” ነው የሚሻለው ወይስ እንደኔ “አበበ ግን (ጫማ አድርጎ) ለዚህ ማራቶን ውድድር ጥቅምት ፲ ቀን ከአርባ አንድ አገሮች ከተውጣጡ ሰባ ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ጋር ተሰለፈ። አንተ “አበበ ቢቂላ ከ ኪሀቺሮ ኦኒሱካ ጋር ስለ ሩጫ ጫማ ውይይት አድርጎ ነበር። ከ (አሲክስ) ካምፓኒ ጋር። በአዲዳስ እና በፑማ መካከል ከፍተኛ ፉክክር ነበር አበበ ቢቂላ ፑማን መርጦ የፑማን ጫማ አድርጎ ለውድድር ገባ።” ብለህ አስፍረሃል። የአማርኛው ፍሰተ ቢስ መሆንና አገባብ ማጣት እንዳለ ሆኖ የዚህ ዐውደ ምንባብ ጥቅም ጭርሱን ስላልታየኝ ትቼዋለሁ። ጽሑፉን በሙሉ በንዲህ ዓይነት ግምገማ ማየት ይቻላል። ጊዜ ይወስነናል እንጂ። ይሄንን አጭር ክፍል የራስህን ትርጉም ከኔ ለውጥ ጋር ያለስሜት ብታነጻጽረው እስካሁን ያሳየኸውን አቋም ትገነዘበዋለህ ብዬ አምናለሁ። 1964 Summer Olympics Abebe Bikila traveled to Tokyo but was not expected to compete. He did enter the marathon, this time wearing Puma shoes. While he had spoken with Kihachiro Onitsuka of the future Asics company, he was pursued actively by Adidas and Puma, ultimately deciding to wear Puma shoes. He used the same strategy as in 1960: to stay with the leaders until the 20 kilometer point, then slowly increase his pace. After 15 km he only had company from Ron Clarke of Australia and Jim Hogan of Ireland. Shortly before 20 km only Hogan was in contention and by 30 km, Bikila was 40 seconds in front of Hogan and two minutes in front of Kokichi Tsuburaya of Japan in third place. He entered the Olympic stadium alone to the cheers of 70,000 spectators. He finished the marathon in a new world record time of 2:12:11:2, 4 minutes, 8 seconds in front of the silver medalist Basil Heatley of Great Britain. Kokichi Tsuburaya was third. He was the first athlete in history to win the Olympic marathon twice. After finishing he astonished the crowd: not appearing exhausted, he started a routine of stretching exercises. He later stated that he could have run another 10 kilometers.

1964 የበጋ ኦሎምፒክ

አበበ ቢቂላ ከኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ጋር አብሮ ወደ ቶኪዮ ተጓዘ ነገር ግን ይወዳደራል ብሎ ያሰበ ምንም ስው አልነበረም። አበበ ቢቂላ ግን ለዚህ ማራቶን ውድድር ተሰለፈ። በዚህ ውድድር ግን ጫማ አድርጎ። አበበ ቢቂላ ከ ኪሀቺሮ ኦኒሱካ ጋር ስለ ሩጫ ጫማ ውይይት አድርጎ ነበር። ከ (አሲክስ) ካምፓኒ ጋር። በአዲዳስ እና በፑማ መካከል ከፍተኛ ፉክክር ነበር አበበ ቢቂላ ፑማን መርጦ የፑማን ጫማ አድርጎ ለውድድር ገባ። ለአበበ ቢቂላ ምንም አዲስ ዘዴ አላስፈለገውም። የተጠቀመውም የ 1960 ውን ዘዴ ነው። ይሀውም እስከ 20 ኪሎ ሜትር ድረስ ከፊት ከሚመሩት ቡድኖች ጋር አብሮ መሮጥ። ከዚያ ፍጥነቱን በጥንቃቄ ቀስ በቀስ እየጨመረ ሄደ። በ15 ኪሎ ሜትር ላይ አብሮት ይሮጥ የነበረው የአውስትራሊያው ሮን ክላርክ እና የአየርላንዱ ሆግን ብቻ ነበሩ። 20 ኛው ኪሎ ሜትር ከመጀምሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ሆገን ብቻ ነበር ተፎካካሪው። በ 30 ኛው ኪሎ ሜትር ላይ አበበ ቢቂላ 40 ስከንድ ሆገንን ቀድሞት ነበር። እንዲሁም ሁለት ደቂቃ የጃፓኑን ኮኪቺ ሱባራያ ሶስተኛ የወጣውን። አበበ ቢቂላ ኦሎምፒክ ስታዲዮሙ ውስጥ የገባው ብቻውን ነበር። በዚያም ይጠባበቅ የነበረው 70,000 ተመልካች በከፍተኛ ሁኔታ አድናቆታቸውን ገልጸውለታል። በዚህ ውድድር ላይ የራሱን ክብረ ወሰን በድጋሚ በመስበር አሻሽሎታል። አዲሱ ክብረ ወሰንም 2፡12፡11.2 ነበር። አበበ ቢቂላ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚውን እንግሊዛዊ ባሲል ሄትሌይ በ4 ነጥብ 8 ሰኮንድ ቀድሞት ነው ውድድሩን የጨረሰው። ውድድሩንም እንደጨረስ ምንም አይነት ድካም አልታየበትም። እንዲያውም ገና ሊሮጥ የሚሰናዳ ነበር የሚመስለው። ተመልካቹን በጣም ነበር ያስገረመው በውድድሩ ምክንያት ጡንቻው እና መገጣጠሚያዎቹ እንዳይተሳሰሩ የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ ስፖርቶች ሲሰራ መመልከታቸው። ተመልካቹን በጣም ያስገረመው እርጋታው እና ቅልጥፍናው ነው። አበበ ቢቂላ ከውድድሩ በኋላ ተጠይቆ ሲመልስ ሌላ አስር ኪሎ ሜትር ጨምሮ መሮጥ ይችል እንደነበር ተናግሯል።

እኔ ደግሞ የሚከተለውን ጽፌያለሁ የ፲፱፻፶፮ ዓ/ም ፲፰ኛው የቶክዮ ኦሊምፒክ ሊካሄድ አርባ ቀናት ሲቀረው አበበ ቢቂላ በማራቶን ውድድር ልምምድ ላይ ነበር። በልምምዱ ላይ እያለም ህመም ቢሰማውም ህመሙን ችላ በማለት ልምምዱን ቀጠለ። ነገር ግን በልምምድ ላይ ራሱን ስቶ ይወደቅና አንስተው ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱት ህመሙ ያበጠ የትርፍ አንጀት ሆኖ ተገኘ። ወዲያው ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ለጥቂት ቀኖች ካገገመ በኋላ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በምሽት ልምምዱን ቀጠለ። አበበ ቢቂላ ከኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ጋር አብሮ ወደ ቶኪዮ ሲጓዝ በርትቶ ይወዳደራል ብሎ ያሰበ ሰው አልነበረም። አበበ ግን (ጫማ አድርጎ) ለዚህ ማራቶን ውድድር ጥቅምት ፲ ቀን ከአርባ አንድ አገሮች ከተውጣጡ ሰባ ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ጋር ተሰለፈ። ለአበበ ቢቂላ ምንም አዲስ ዘዴ አላስፈለገውም። አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን እንደ ሮማው ኦሎምፒክ ከፊት ከሚመሩት ቡድኖች ጋር እስከ ሃያ ኪሎ ሜትር ድረስ አብሮ እንዲሮጥና ከዚያ በኋላ ውድድሩን እንዲመራ መከሩት። በዚህም ዕቅድ መሠረት ከሮጠ በኋላ ፍጥነቱን በጥንቃቄ ቀስ በቀስ እየጨመረ ሄደ። በአሥራ አምስተኛው ኪሎ ሜትር ላይ አብረውት የነበሩት የአውስትራሊያው ሮን ክላርክ እና የአየርላንድ ጄምስ ሆጋን ብቻ ነበሩ። አበበ ቢቂላ በቀዶ ጥገናውም ሆነ በሞቃታማው የአየር ሁኔታ ምንም ዓይነት እንከን አልታየበተም። እንዲያውም ሲሮጥ ለሚመለከተው ከመሬቱ በላይ የሚንሳፈፍ ይመስል ነበር። አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን ትንሽ ጉልበት በመጠቀም እንዴት መሮጥ እንዳለበት ያስተማሩትን አበበ ቢቂላ በተግባር ላይ ሲያውለው እና ሩጫው ምንም ዓይነት ጥረት የማያስፈልገው ያስመስለው ነበር። አበበ ቢቂላ ኦሎምፒክ ስታዲዮሙ ውስጥ የገባው ብቻውን ነበር። በዚያም ይጠባበቅ የነበረው ፸ ሺህ ተመልካች በከፍተኛ ሁኔታ አድናቆቱን ገልጾለታል። በዚህ ውድድር ላይ የራሱን ክብረ ወሰን በድጋሚ በመስበር አሻሽሎታል። አዲሱ ክብረ ወሰንም ሁለት ሰዐት ከአሥራ ሁለት ደቂቃ ከአሥራ አንድ ነጥብ ሁለት ሴኮንድ (2፡12፡11.2) ነበር። ውድድሩንም እንደጨረስ ምንም አይነት ድካም አልታየበትም። እንዲያውም ገና ሊሮጥ የሚሰናዳ ነበር የሚመስለው። ተመልካቹን በጣም ያስገረመው በውድድሩ ምክንያት ጡንቻው እና መገጣጠሚያዎቹ እንዳይተሳሰሩ የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ ስፖርቶች ሲሰራ መመልከታቸው እንዲሁም እርጋታው እና ቅልጥፍናው ነበር። አበበ ከውድድሩ በኋላ ተጠይቆ ሲመልስ ሌላ አስር ኪሎ ሜትር ጨምሮ መሮጥ ይችል እንደነበር ተናግሯል። ደምሴ ወልዴ በአሥረኛ ደረጃ ሲጨርስ ማሞ ወልዴ ግን አሥራ አምስት ኪሎሜትር ላይ አቋርጦ ከውድድሩ ወጣ። ቻርሊ ሎቬት “ማራቶን በኦሎምፒክ” በሚለው መጽሐፉ ላይ ስለቶክዮው ውድድር ሲዘግብ “ግማሽ ሩጫውን እንዳገባደደ በአምስት ሰከንድ ልዩነት ይመራ ነበር” ይላል ። ሎቬት “የክፍለ ዘመኑ ሩጫ ብዙ ታሪክ የተጻፈለት እና የተወራለት ውድድር ነው” ሲል አበበ ቢቂላን ደግሞ “ወደር የማይገኝለት እውነተኛ የማራቶን ሯጭ ምሳሌ ነው” ይለዋል። ሪቻርድ በኔዮ ደግሞ “የማራቶን ጌቶች” በሚለው መጽሐፉ “አበበ ቢቂላ ሩጫው ምንም አይነት ጥረት የማያስፈልገው ያስመስለዋል” ብሎታል። “አበበ ቢቂላን ሲያዩት ረጅም ቀጠን ያለ በቀላሉ ተሰባሪ ይመስላል፣ ነገር ግን ከሚገባው በላይ ጠንካራ አትሌት” ነው ይልና “አበበ ቢቂላ ማናቸውም የማራቶን ሩጫ ተወዳዳሪ ሊሆን የሚገባው ምሳሌ ነው” ብሏል። ቀጥሎም “አበበ ቢቂላ ተፈጥሮ ካፈራቻቸው ምርጥ የዓለማችን አትሌቶች አንዱ ነው” ይልና “በዚህም (በቶክዮው) ድል የተነሳ ለሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ማራቶንን ያሸነፈ ብቸኛ አትሌት አድርጎታል” ይላል። አበበ ቢቂላ ሁለተኛውን ወርቅ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሰ የአዲስ አበባ ሕዝብ ተገልብጦ ወጥቶ የጀግና አቀባበል ካደረገለት በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ የሻምበልነት ማዕረግና አዲስ ቮልስ ዋገን ቢትል ሸለሙት። --Bulgew1 03:01, 4 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]


Bulgew1 ምን ልበልህ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ አሉ። የኔ ጥያቄ ላንተ የነበረው እኔ ያንተን ጽሁፍ ይሰረዝ ይጥፋ አላልኩም አንተ የ እኔን ጽሁፍ ለምን ማጥፋት ፈለክ ነበር ጥያቄው? በራስህ ጽሁፍ "(የኔም ቅጂ ካንተው ጽሑፍ የመነጨ ነው)" ብለህ ስታበቃ ቁም ነገሩን ትተህ ስለ ዊኪፒዲያ አሰራር ገለጻ ለኔ መስጠት ጀመርክ። በነገራችን ላይ የአማርኛ መምህር ነህ?

የማራቶኑ ውድድር እሑድ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፷ ዓ/ም ሲጀመር ከአርባ አንድ አገራት የተውጣጡ ሰባ አራት ሯጮች ተሰልፈው ነበር። ኢትዮጵያ በቶክዮው ማራቶን እንድተደረገው በሜክሲኮም ከአበበ ጋር ሦስት ሯጮችን አሰልፋለች። ማሞ ወልዴ እና ገብሩ መራዊ ሌሎቹ ተሳታፊዎች ነበሩ። አበበ ውድድሩን ጀምሮ ከፊት ከሚመሩት ጋር እስከ አስራ ሰባተኛው ኪሎሜትር ድረስ ከሮጠ በኋላ የእግሩ ሕመም ስለጠናበት አብሮት የነበረው ማሞ ወልዴ ባልገመተውና ባላሰበው ሰዓት በጆሮው ተምዘግዝጐ የገባውን የአበበን ቃላት ማመን አቃተው። እንደመደንገጥ ብሎ «ምን አልከኝ ?» በማለት ጠየቀው። አበበም የማሞን መደናገጥ ስለተገነዘበ እንደ ማባበል ዓይነት አለና « አይዞህ ታሸንፋለህ፤ እኔ አልቻልኩም፤ የ እግሬ ወለምታ በጣም ተሰምቶኛል፤ ሌላም የማላውቀው ስሜት እየተሰማኝ ነው። ስለዚህ አደራዬን ተቀበለኝ፤ የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠብቀናል፤ እኔ ስላልቻልኩ አንተ ቀጥል፤ የ ኢትዮጵያ አምላክ ይከተልህ» ካለው በኋላ አስፋልት ዳር ወደቀ። እውነትም በጣም ታሟል። ወዲያውኑ አበበ ሜክሲኮ ሆስፒታል በአስቸኳይ ተወሰደ።

የአበበ አለመጨረስ ሲሰማ ያልደነገጠ ኢትዮጵያዊም ሆነ የአበበ አድናቂ አልነበረም። ሁናቴውን ታዋቂው ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ እንዲህ ገልፆት ነበር፤ «የአበበን መውጣት ስሰማ ማሞን ለማበረታታት የጮህኩት ጩኸት ድምፄን ለሦስት ቀናት ያህል ዘግቶት ነበር።» አበበ እና ማሞ ያደረጉትን ንግግር ከየት አመጣህው? ስለ ሰለሞን ተሰማ የጻፍከውን? ምንጩን ጻፍልኝ። እኔ ግን እንደገባኝ ያንተ ምክንያት ይሄ ነው "('አበበ ቢቂላ' በሚለው አርስት ላይ የሰፈረው ጽሑፍ እስኪተካከል)"

ሌላው በጣም ያስገረመኝ ::ውይ! ውይ! ውይ! ጉዴ ፈላ Bulgew1 እና Hgetnet ያላወቁ አለቁ አሉ ለካ ሁለታችሁም የዊኪፒዲያ admin is traitor ናችሁ። ወይ እኔ ወይ እኔ ወይ እኔ እኔ እኮ የገባኝ አሁን ነው ኢሜይል ለማንበብ ስሄድ የኢሜይሉ ሳጥን ሞልቶ ደብዳቤው መሬት ፈሶ ደረስኩኝ ከዊኪፒዲያ admin is traitor ይላል። Hgetnet ለካ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ አይኔን ግንባር ያድርገው እያልክ የምትለኝ ለካ ሁለታችሁም admin is traitor ስለሆናችሁ ነው። ምን ይባላል Hgetnet እንዲያው ለነገሩ ቀስ ብለህ ከባለስልጣን ጋር አትጋፋ እንኳን ብትለኝ አሁን ገብቶኛል ስልጣናችሁን ማስየታችሁ ነው ትክክለኛው ምክንያት ይሄ ነው። አሁን ገባኝ ክርክር ዋጋ የለውም ለነገሩ አንተ ግን የምትተረጉመው ወይም የምትጽፈው አጥተህ ነው ሽንጥህን ገትረህ የምትከራከረው አሁን ገብቶኛል ስልጣናችሁ admin is traitor መሆናችሁ ስለዚህ የፈለከውን ማድረግ ትችላለህ። ሁለተኛ ወደዚህ አልደርስም ሌላ ብዙ የሚሰራ ነገር አለ በያለበት። ይህ የመጨረሻ ጽሁፌ ነው ሁለተኛ በዚህ በኩል አላልፍም።

ትንሽ ሰው ሁል ጊዜ ትንሽ ነው ስለዚህ ዞር እልላችኋለሁ አመሰግናለሁ ፡Samson25 04:23, 4 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

Samson25, አንተ ከዚህ ውክፔዲያ እንድትጠፋ ማንም አይመኝም። ቀስ ብለን ጉዳዩን ከሌሎች አባሎች ጋር በስፋት ብንወያይበት? Elfalem 00:48, 5 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]


ሰላም ላንተ ይሁን Elfalem በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ። እንዳንተ ያሉ እውነተኛ ሰዎች የሉም ብዬ ደምድሜ ነበር። ነገር ግን ይህን መልእክት ሳገኝ በጣም ገረመኝ። Elfalem አንድ ውለታ ስራልኝ ይህን ውይይት ከላይ ጀምረህ ካላነበብካው አንብበው እና የእኔን ስህተት ጠቁመኝ አደራህን ስለ እውነት ብለህ። እኔ ከላይ እንደጠቀስኩት የክፍሉ አለቃ መሆናቸውን አላውቅም ነበር እስከ ትናንት ድረስ አሁንም ያንተን መልእክት በኢሜይሌ ጠቋሚነት ነው ያገኘሁት። ደግመው ደጋግመው ያንተ ጽሁፍ መጥፋት አለበት ሲሉኝ ግራ ገባኝ ምክንያቱም እሱ ጻፍኩ ያለው የኔን ጽሁፍ ኮፒ እና ፔስት አድርጎ ያንተ ይጥፋ አማርኛህ ልክ አይደለም ጽሁፍህ አያምርም "የአማርኛው ትርጉም ፍሰት እና ይዘት ወይም አገባብ የሌለው ሆኖ እናገኘዋለን።" እኔ ያልተጻፈ አልተረጎምኩም ለምሳሌ "አበበ ቢቂላ እና ማሞ ወልዴ ያደረጉት ንግግር" ምንጩ ከየት ነው? "ሰለሞን ድምጹ ሶስት ቀን ተዘጋ" እዚህ እኮ የምናወራው ስለ አበበ ቢቂላ ነው። ስለ ሰለሞን አይደለም ስህተት ልፈልግ ካልኩ ብዙ ምስሌ ማቅረብ እችላለሁ አንባቢውን አናወናብደው ነው ያልኩት። እኔ አሁንም የ Bulgew1ጽሁፍ ይጥፋ አላልኩም እሱ ግን የእኔን ጽሁፍ ለማጥፋት ለምን ፈለገ ያውም በራሱ ቃል (የኔም ቅጂ ካንተው ጽሑፍ የመነጨ ነው)ብሎ እያለ የእኔ ጽሁፍ የሚጠፋ ከሆነ የሱም መጥፋት አለበት ብዬ አልኩኝ። ጥፋቴን ማወቅ አልቻልኩም። "('አበበ ቢቂላ' በሚለው አርስት ላይ የሰፈረው ጽሑፍ እስኪተካከል)" < - - ይህን ጽፎ መጥቶ ግን የእኔን ስራ ጥሩ ነው ይላል ብዬ አልገምትም። ለመሆኑ የሚጻፍ ወይም የሚተረጎም ጉዳይ ጠፍቶ ነው? በዚህ ጉዳይ እንዲህ የምንባላው በጣም ያሳዝናል። ፡Samson25 02:48, 5 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

Samson25, በዚህ ጉዳይ ካንተ ጋር ከዚህ ወዲህ መወያየት ከስድብ በስተቀር ምንም የበሰለ ውጤት እንደማያመጣልኝ ስለማውቅ አልመለስበትም። ነገር ግን ስለ"ክብረ ቅርጹ" (for the record) ብቻ አንተ "ለካ ሁለታችሁም admin is traitor ስለሆናችሁ ነው። ምን ይባላል Hgetnet እንዲያው ለነገሩ ቀስ ብለህ ከባለስልጣን ጋር አትጋፋ እንኳን ብትለኝ አሁን ገብቶኛል ስልጣናችሁን ማስየታችሁ ነው ትክክለኛው ምክንያት ይሄ ነው። አሁን ገባኝ ክርክር ዋጋ የለውም ለነገሩ አንተ ግን የምትተረጉመው ወይም የምትጽፈው አጥተህ ነው ሽንጥህን ገትረህ የምትከራከረው አሁን ገብቶኛል ስልጣናችሁ admin is traitor መሆናችሁ ስለዚህ የፈለከውን ማድረግ ትችላለህ። ሁለተኛ ወደዚህ አልደርስም ሌላ ብዙ የሚሰራ ነገር አለ በያለበት። ይህ የመጨረሻ ጽሁፌ ነው ሁለተኛ በዚህ በኩል አላልፍም።ትንሽ ሰው ሁል ጊዜ ትንሽ ነው ስለዚህ ዞር እልላችኋለሁ አመሰግናለሁ ፡Samson25 04:23, 4 ኦገስት 2010 (UTC)" ብለህ ላስቀመጥከው መልስ ብቻ እንዲሆን፤ በመጀመሪያ "admin is traitor " ማለት ምን እንደሆነ አላውቅም። የአማርኛ ውክፔዲያ አስተዳደር ውስጥ ያለሁ መስሎህ እንደሆነ በጣም ተሳስተሃል። ስለ Hgetnet የማውቀው የለም። እንደገመትኩት የ Hgetnet አስተያየት እንደተጠቃሚ ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት እንጂ እንደአንተ ስህተተኛ አስተያየት እሱ/ሷ ከእኔ ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ወይም "ዓላማ" ኖሮን አይደለም። በነገራችን ላይ እኔ ራሴን "የአማርኛ መምሕር" ሳይሆን "የአማርኛ ተማሪ" ብዬ ነው የምገምተው። ስለዚህም የእኔን ጽሑፎችም፣ ትርጉሞችም ስህተት (የአማርኛ አጻጻፍም ሆነ የይዞታ) ሌላ ሰው ሲያስታውቀኝ በብስለቴ የማመዛዘንና እስከመቀበልም ችሎታ አለኝ። " ትንሽ ሰው ሁል ጊዜ ትንሽ ነው " ብሎ መጻፍ አንተን እራስህን እንዴት እንደሚያስገምትህ እራስህ አስላው። ከአክብሮት ጋር --Bulgew1 12:48, 5 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

በመጀመሪያ የምለው ይህ ውክፔዲያ በተፈጥሮ የጋራ ሥራ ስለሆነ የሀሳብ አለመስማማት መኖሩ የሚጠበቅ ነገር ነው። የዚህ አለመስማማት ብቸኛው መፍትሄ ደግሞ የአክብሮትና ትኩረት ያለው ውይይት በማድረግ ነው። ሌላው የምጠቅሰው ይህ ውክፔዲያ ከትላልቆቹ ጋር ሲተያይ አነስተኛ ስለሆነ ሁሉም መመሪያዎችና ልምዶች በግልፅ አልተጻፉም። እኔ በዚህም በእንግሊዝኛውም ዓመታት ስላሳለፍኩኝ የማውቀው፦
  • ቀናት በግዕዝ አቆጣጠር ቢጻፍ ነው የሚመረጠው - ይህ ነጥብ ብዙም አካራካሪ አይደለም። ነገር ግን ለግልፅነት ሲባል ነው። ይህ የአማርኛ ውክፔዲያ ስለሆነ በተቻለን መጠን የግዕዝ አቆጣጠርን (፩፣ ፪ ወዘተ) ለመጠቀም እንሞክር።
  • መጋቢነት - Hgetnet እና Bulgew1 መጋቢ (Administrator) አይደሉም። የመጋቢዎች ዝርዝር ልዩ:ListUsers/sysopን በማየት መገንዘብ ይቻላል። ሌላው ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በዚህ ውክፔዲያ ላይ ታላቅ ተሳትፎ የሚያደርጉት ወደ ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑት አባሎች የሚስጥራዊ ሽርክ ወይም ቡድን አላቸው የሚል ምንም መረጃ የለም።
  • ውክፔዲያ የጋራ ነው። - ይህ ነጥብ ከሁሉም በበለጠ ዋና ነጥብ ነው። የውክፔዲያን የሕግ አቋም አንብባችሁት ከሆነ ማንኛውም እዚህ መዝገበ ዕውቀት ላይ የሚጻፍ ነገር የሁሉም ነው። ማለትም ማንኛውም ሰው የጻፈው ነገር በሌሎች ሰዎች መታረም ይቻላል እናም "የኔ የብቻዬ ነው" ማለት አይቻልም። በተጨማሪም "እኔ የሰራሁትን አጠፋለው" ማለት አይቻልም።
  • ውይይቱን በተመለከተ በተቻለን መጠን ማተኮር ያለብን በተጻፉት ዐረፍተ ነግሮችና ሀሳቦች ላይ ነው። (በዚህ ውይይት ላይ አንዴ ስለ ቶኪዮው ውድድር እንደተደረገው)
ስለዚህ ይህን የአበበ ቢቂላ መጣጥፍ በተመለከተ ከአንድ በላይ መጣጥፍ ሊኖር አይችልም። ይህ አንባቢዎችን ከማደናበርና ሁለቱን ፅሁፎች ለመንከባከብ ተጨማሪ ስራ ከመፍጠር ሌላ ምንም ጥቅም የለውም። በአሁኑ ሰዓት በ"ሻምበል አበበ ቢቂላ" ስር የሚገኘው ጽሁፍ በSamson25 ነው የተመሠረተው በBulgew1 ተሻሽሏል። ወደፊትም በኔም በSamson25ም በሌሎችም አባሎችም እንደገና ይሻሻላል። ሁለቱ አባሎች በጣም ጠቃሚ አስተዋጽኦ አድርገዋል ግን ጽሁፉ የSamson25ም የBulgew1ም አይደለም የጋራ ነው። ስለዚህ ይህ ዕትም አዲሱ ነው (the current version). Elfalem 03:55, 6 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]

ሰላም Elfalem መልካም ስራ ይሁንላችሁ

  1. (ለውጡ | ታሪክ) . . አበበ ቢቂላ‎; 19:18 . . (+29) . . Elfalem (ውይይት | አስተዋጽኦች)
  2. (የማዛወር መዝገብ); 19:16 . . Elfalem (ውይይት | አስተዋጽኦች) «ሻምበል አበበ ቢቂላ» ወደ «አበበ ቢቂላ» አዛወረ
  3. (የማጥፋት መዝገብ); 19:16 . . Elfalem (ውይይት | አስተዋጽኦች) «አበበ ቢቂላ» አጠፋ (ይዞታ፦ «አበበ ቢቂላ (ቁጥር 11) አበበ ቢቂላ የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ማራቶን አሸናፊ ኢትዮጵያዊ ከመሆኑም ሌላ በሮም ኦሊ...» አለ።)
Samson25 20:54, 7 ኦገስት 2010 (UTC)[reply]