አባ ጉባ
አቡነ አባ ጉባ | |
---|---|
የጻድቁን ስዕል ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ | |
ጻድቅ ፣ ቅዱስ | |
የተወለዱት | ታህሣሥ ፳፱ ቀን ፫፻፴፮ ዓ.ም. |
የአባት ስም | ጌርሎስ |
የእናት ስም | ቴዎዶክሲያ |
የሚከበሩት | በመላው የኢትዮጵያ ርትዕት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለይ በአድዋ |
በዓለ ንግሥ | ባረፉበት ዕለት ፣ ግንቦት ፳፱ ቀን በኢትዮጵያ |
በየወራቱ የሚታሰቡት | ወር በገባ በ፪ኛው ቀን |
የትውልድ ሀገር | ኪልቂያ |
አባ ጉባ የተወለዱት ታኅሣሥ ፳፱ ቀን በ፫፻፴፮ ዓ.ም በመንፈቀ ሌሊት ነው ። አባታቸው ጌርሎስ እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጋጎች ሰዎች ነበሩ ። ጉባ ማለትም አፈ መዐር ፣ ጥዑመ ልሳን ማለት ነው ። ከዘጠኙ ቅዱሳንም አንዱ ናቸው ።
አባ ጉባ በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለሰባት ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር ። ሕፃኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን "ሃሌ ሉያ" ብለው አመስግነዋል ።
በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል ። ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ሒድ ።" ብሏቸው ከስምንቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል ። ጻድቁ አቡነ አባ ጉባ በአራተኛ አጋማሽ ክፍለዘመን ከዘጠኙ ቅዱሳን ጋር ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት ውስጥ አንዱ ናቸው ።
ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል ፣ መጻሕፍትን በመተርጐም ፣ ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል ። በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት እርሳቸው የመሠረቷት ገዳም ናት ።
ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ይሉ ነበር ። ብዙ ጠበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል። ሙታንንም አንስተዋል ። እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች ። ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል ።
በዘመኑ ትኩረ ካጡት ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሄው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው ።