Jump to content

ዘጠኙ ቅዱሳን

ከውክፔዲያ
ዘጠኙ ቅዱሳን
ከአቡነ አረጋዊ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ የተገኘ በ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን የተሳለ የቅዱሳኑ ምስል
የክርስትና ሃይማኖት ሊቃውንት
-ስም ዝርዝር
-የትውልድ ሀገር
-በኢትዮጵያ
የመሠረቱዋቸው
ገዳማት
-ዓመታዊ ክብረ
በዓላቸው

፩ኛ - አቡነ አረጋዊ ሮም ደብረ ዳሞ ጥቅምት ፲፬
፪ኛ - አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም አክሱም ጥቅምት ፮
፫ኛ - አቡነ የማታ አቡነ የማታ ጎህ ቆስይ ገርዓልታ ጥቅምት ፳፰
፬ኛ - አባ ገሪማ ሮም መደራ/ዓድዋ ሰኔ ፲፯
፭ኛ - አባ ድሕማ አንጾኪያ እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ ጥር ፲፮
፮ኛ - አባ አፍፄ ታናሽ እስያ የሓ ግንቦት ፳፱
፯ኛ - አባ ሊቃኖስ ቁስጥንጥንያ አክሱም ህዳር ፳፰
፰ኛ - አባ አሌፍ ቂሳርያ ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩

፱ኛ - አባ ጉባ ኪልቂያ ዓድዋ አጠገብ ግንቦት ፳፱
የተገናኙበት ቦታ በቃልኬዶን በ፬፻፶፩ ዓ.ም.በተደረገው የሃይማኖት አበው ጉባዔ
ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት ዘመን ፭ኛው ምዕተ ዓመት በንጉሥ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት
ቅርጽ
በአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አክሱም አጠገብ የሚገኝ የቅዱሳኑ ምስል
የሚከበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን


ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት አከፋፈል መሰረት “ ጥንታዊው የታሪክ ዘመን” ተብሎ በሚጠራው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ዘጠኝ የውጭ ሀገር ታላላቅ የክርስትና ሃይማኖት አባቶች ናቸው ፡፡[1] የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ አስተዋጽኦን ማለትም በመንፈሳዊ ህይወት ፣ በስብከተ ወንጌል፣ ገዳማዊ እና የምንኩስና ሕይወትን በማስፋፋት ፣ መጽሐፍትን በመተርጎም፣ አበርክተዋል፡፡

ለአገራችን ሥነ-ፅሑፍ እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ከደጋግ ነገስታት ጋር በመሆን ለትምህርት ፣ ለማህበራዊ ኑሮ ወዘተ መሠረት የሆኑ ገዳማትን ከመመስረት ከቤት ክርስቲያን አልፎ ለአገራችን ኢትዮጵያ አያሌ አበርክቶት አድርገው አልፈዋል፡፡ በአገራችን ለቅድስናና ምንኩስና ፣ ለመፈንሳዊነት ትልቅ አብነት አላቸው፡፡ ከሮም ፣ ታናሽ እስያ፣ቁስጥንጥንያ ፣ ቂሳሪያ እና ሌሎች የእስያና ኤሮፓ አገሮች ቢመጡም ግዕዝን አጥንተው የአገሩን ባህልና አኗኗር ለምደው ክርስትናን በምድረ ኢትዮጵያ አስፋፍተዋል፡፡

ክርስትናን ወሰን አይገድበውምና ፣ ክርስቲያን ሃይማኖት እንጂ የድንበር አገር የለውምና የመጡበትን ቦታ ሳይሆን ህዝቡ መንፈሳዊ አባትነታቸውን ተቀብሎ! ቤተክርስቲያንም ውለታቸውን ቆጥራ የቅድስና ማዕረግ ሰጥታ ታከብራቸዋለች፡፡ ዕለት ተሰይሞላቸውም ክብር ይደረግላቸዋል፡፡

ከተለያዩ አካባቢ መምጣታቸውም ከየመጡበት አገር ወደ ግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ አያሌ መንፈሳዊ መጽሐፍትን እንዲተረጉሙ አስችሏቸዋል፡፡ በዚህች ትንሽ ርዕስ ስለተሰዓቱ ቅዱሳን ይህን ያክል ካነሳን በሚከተለው አንቀጽ ደግሞ ማንነታቸውን እናስተዋውቃልኋለን፡፡ ስም የመጡበት አገር የገደሙበት ቦታ የመታሰቢያቸው ቀን

፩- አቡነ አረጋዊ ሮም ደብረዳሞ ጥቅምት ፲፬

፪- አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም አክሱም ጥቅምት ፮

፫- አቡነ የማታ ቆስይ ገርዓልታ ጥቅምት ፳፰

አቡነ የማታ ገዳም የሚገኝ ጥንታዊ የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስዕል

፬- አቡነ ገሪማ ሮም መደራ/ዓድዋ/ ሰኔ ፲፯

፭- አባ ጽሕማ አንጾኪያ እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ ጥር ፲፮

፮- አባ አፍፄ ታናሽ እስያ የሓ ግንቦት ፳፱

፯- አባ ሊቃኖስ ቁስጥንጥንያ አክሱም ህዳር ፳፰

፰- አባ አሌፍ ቂሳርያ ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩

፱- አባ ጉባ ኪልቂያ አድዋ አጠገብ ግንቦት ፳፱

የኣቡነ ጽሕማ ክብረ በዓል ጥር 19 ነው የሚከበረው ኣቡነ ይሞኣታ ማለት የማታ ማለት ሊሆን ኣይችልም። ምክንያቱ የማታ የሚለው ቃል የኣማርኛ ቃል ስለሆነ ኣማርኛ ደግሞ በስድስተኛ ክፍለዘመን ስለአልነበረ ትክክል ኣይደለም

  1. ^ በ፬፻፵፫ ዓ.ም. የቃልኬዶን ጉባዔ Monophysitism ስሕተት ነው ብሎ ወሰነ ። በዚህም ምክኒያት ከቤዛንታይን መንግሥት ለመሠወር ሊቃውንት ወደ ግብፅ ፣ አሬብያና ፣ ኢትዮጵያ ተሰደዱ (Ullendorff 1960;101) እነዚህ የተሰደዱ ክርስቲያኖች "ፃድቃን" ተብለው ይጠሩ ነበር ። በጣም ከታወቁት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ነበር የተሰደዱት እነሱም ዘጠኙ ቅዱሳን በመባል ይታወቃሉ ።

አቡነ ጰንጤሌዎን ትክክለኛ ኣፃፃፍ ኣይደለም ትክክለኛው ኣቡነ ጰንጠሌዎን ነው።