አባ ጎርጎርዮስ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
አባ ጎርጎሪዮስ እስክንድር
አባ ጎርጎሪዮስ
የአማርኛና ግዕዝ ቋንቋ ሊቅ
ስም ጎርጎርዮስ 
የተወለዱት ሺ፭፻፺፭ ወሎ ክፍለ ሀገር
መዐረግ አባ ፣ ደራሲ ፣ ጸሐፊ
የአባት ስም እስክንድር
ያረፉት ሺ፮፻፶፰ እስክንድርያ አካባቢ


አባ ጎርጎሪዮስ እስክንድር (1595 - 1658) ከመካነ ስላሴ ወሎ የመጡ ቄስና የመኳንንት ዘር ነበሩ። ከጀርመናዊው ሉዶልፍ እዮብ ጋር በመሆን በአማርኛና በግዕዝ ብዙ መዝገበ እውቀቶችን የጻፉ ናቸው ።

በመርከብ መሳፈር (ኤቲኒሬሪ=itinerary)ስሕተት ምክኒያት ከኢትዮጵያ ወደ ሕንድ ከዛም ወደ አውሮፓ የገቡት[1] አባ ጎርጎርዮስ እስክንድር በ፲፮፶፪ ዓ.ም. ሉዶልፍና እሱን ይደጉመው የነበረው የሳክስ ጎታ እና አምስታድት መስፍን ኸርነስት ዘ ፒየስ ባደረጉላቸው ግብዣ[2] ፣ ጎርጎሪዮስ ለጥያቄያቸው መልስ በመስጠት የግዕዝ መዝገበ ቃል እና ከዚያም የአማርኛ ሰዋሰው እና መዝገበ ቃል ሊያሳትሙ በቁ። ከዚህና መሰል ሥራዎቻቸው በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የተሳፈሩበት መርከብ በመስጠሙ እስክንድርያ አካባቢ በ1658 በሞት አረፉ ።

ከአስተዋፆዋቸው በጥቂቱ

  • መዝገበ ቃላት በአምኅርኛ

በጀርመናዊው ጸሐፊ እዮብ ሉዶልፍ እና ኢትዮጵያዊው አባ ጎርጎርዮስ ትብብር የተደረሰ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ነው ። በላቲን ቋንቋ ግምገማ የተካሄደበት ይህ መጽሐፍ በ1690 ዓ.ም. ሊታተም በቅቷል ።

  • መጽሐፈ ትምህርት ዘልሳን አምኅራ

በጀርመናዊው ጸሐፊ እዮብ ሉዶልፍ እና ኢትዮጵያዊው አባ ጎርጎርዮስ ትብብር የተደረሰ የአማርኛ ሰዋሰው ነበር። በላቲን ቋንቋ ግምገማ የተካሄደበት ይህ መጽሐፍ በ1686 ዓ.ም. ሊታተም በቅቷል።

መጽሐፉ፣ ከተለያዩ የሰዋሰው ጥናቶች በተጨማሪ የሉቃስ ወንጌል ም:፲፩ ፣ ቁ. ፩ - ፲፫ ትርጓሜን፣ አባ ጎርጎሪዮስ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የደረሱትን ምስጋና፣ ግጥሞችና የለተ ተለት ንግግሮችን መዝግቦ ይገኛል ።

  • ፊደሎችን በሚመለከት

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ የአማርኛ ቃላት በርግጥም የአሁን ዘመን አማርኛን ለሚናገር ሰው እንግዳ አይደሉም። ሆኖም አልፎ አልፎ ለየት ያሉ የፊደላት አቀነባበር ይታያል። በአሁን ጊዜ «አ»ን የሚጠቀሙ ቃላት «ሐ»ን ሲጠቀሙ ይታያሉ፣ በአ እና ዐ ም መካከል ልዩ አጠቃቀም ይታያል ። ሀ፣ ሐ እና ኅ እንዲሁ አገባብቸው ውሱንና የጠራ መሆኑ ግልጽ ነው ። በተረፈ አንድ አንድ ፊደላት ከአሁኑ ዘመን በተለይ መልኩ ሲቀረጹ ይታያሉ ። ለምሳሌ "ጨ" ፊደል "ጠ" ሆኖ ከጎንና ጎኑ መያዣ ቀለበት ያለው ፊደል ሆኖ ቀርቧል።


የኣባ ጎርጎሪዮስ አጭር የሕይዎት ታሪክ በእዮብ ሉዶልፍ መጽሐፍ መቅድም እንደሰፈረ

ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ እዮብ ሉዶልፍ ከጻፈው ሕይወት ታሪካቸው የተገኘ
  2. ^ እዮብ ሉዶልፍ ከጻፈው ሕይወት ታሪካቸው የተገኘ