አብደላ እዝራ

ከውክፔዲያ

ሃያሲ አብደላ እዝራ ከአባቱ ከአቶ መሐመድ ሳልህ አልአረግስኢ እና ከእናቱ ወ/ሮ መሪሃም በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባመርካቶ አንዋር መስጊድ አካባቢ ተወለደ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ከ1ኛ-6ኛ ክፍል በአፍሪካ አንድነት ትምህርት ቤት የተከታተለ ሲሆን 7ኛ እና 8ኛን በልዑል ወሰን ሰገድ ትምህርት ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡

ወደ የመንሰንዓ በመጓዝም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቱን አጠናቋል፡፡ እዚያው የመን ውስጥ በየመኒ ኤርዌይስ ተቀጥሮም ጡረታ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ሠርቷል፡፡ አብደላ አብላጫውን የሕይወት ዘመኑን በሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ ያሳለፈ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላም የበርካታ ገጣምያንና ደራስያን ሥራዎችን በሂሳዊ ብዕሩ ጎብኝቷል፡፡

ሃያሲው ቀደም ባሉት ዓመታት በ“አዲስ ዘመን” እና “የዛሬይቱ ኢትዮጵያ” ጋዜጦች እንዲሁም የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር (ኢደማ) በሚያዘጋጀው ብሌን መጽሔት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት እስከተለየበት ጊዜ ድረስ ደግሞ በ“አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ላይ ጥልቅ የሥነጽሁፍ ትንታኔዎቹን አቅርቧል፡፡ አንጋፋው ሃያሲ ሥራዎቻቸውን በጥበባዊ ሂስ ከተነተነላቸው ዕውቅና ድንቅ ደራሲያን መካከል በዓሉ ግርማደበበ ሰይፉሲሳይ ንጉሡአዳም ረታስብሐት ገብረእግዚአብሔርነቢይ መኰንንዓለማየሁ ገላጋይአበራ ለማኤፍሬም ሥዩምደምሰው መርሻበድሉ ዋቅጅራ ይጠቀሳሉ፡፡

አብደላ እዝራ የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር፡፡ አብደላ እዝራ ድንገት ባደረበት ሕመም፣ ለአጭር ጊዜ ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ፣ ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30፣ በ58 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡