አናሲሞስ ነሲብ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search


አናሲሞስ ነሲብ ( አባ ገመቺስ ) 1842-1923

በ 1842 በቀድሞ አጠራር ኢሉባቦር ክ. ሀገር ሀሩሙ በምትባል ትንሽ መንደር የተወለደው አናሲሞስ ወላጆቹ «ሂካ» የሚል ስም አወጡለት ......ይህ ሂካ የሚለው ስም ተርግዋሚ ለሚለው የአማርኛ ቃል አቻ ቀረቤታ እንዳለው የቋንቅዋው አዋቂዎች ይናገራሉ ........በአራት አመቱ ወላጅ አባቱን በሞት ያጣው ህፃኑ ሂካ .....12 አመት ሲሆነው በባርያ ፈንጋዮች ከተወለደበት ቀዬ ከዕናቱ እቅፍ ተመንጭቆ ተወሰደ ........ከዚያ በህዋላ የባርነት ኑሮውን በመቀጠል የምፅዋን አፈር ረግጦ ባርያ እየገዛ ነፃ በሚያወጣ በአንድ የፈረንሳይ ቆንሲል እጅ እስኪገባ ድረስ ሁለቴ ተፈንግሎ አራት ጊዜ እንደ እቃ ተቸርችሯል .....

መኩርያ ባልቻ ( Onesimus Nesib's pioneering contribution to oromo writings) በሚለው ጽሁፉ እንደገለጸው በዚህ የባርያ ዝውውሩ ወቅት ነበር በአንዱ ጌታው <ነሲብ > የሚል ስም የተሰጠው .........ይህ ፈረንሳዊ ቆንሲል ነበር ከባርነት ነፃ አውጥቶ ከመጀመርያ መምህሩ ፒተር ሉንድህል ጋ ያገናኘው ...............ታህሳስ 24/1872 ይሄው መምህሩ ፒተር ሉንድህል የሂካን ሁኔታ አስመልክቶ ሲፅፍ

ጥቅስ፦ ከጥቂት ወራት ቆይታ በህዋላ ሂካ ክርስቶስን አመነ ....እናም ተጠመቀ ...በራሱ ምርጫም አናሲሞስ የሚለውን የክርስትና ስም ተቀበለ ........አናሲሞስ የልብ ወዳጅ ሊቀርቡት የሚገባ ትሁት ፍጹም ደከመኝን የማያውቅ ነው አሁንማ የአማርኛን መፅሀፍ ቅዱስ ጠንቅቆ ከማወቁም በላይ በውስጡ ያሉትን እውቀቶች ከቅን ልብ ጠልቆ ተረድቷል ሲል አብራርቷል

The swedish mission in Ethiopia የሚል ፅሁፍ የፃፈው አለም እሽቴ እንደገለጸው ቀዳሚዎቹ የሁንድህል ተማሪዎች አናሲሞስን ጨምሮ 6 ሲሆኑ ት .ቤቱ በታሪክ በካታኪዝም በቤተ ክርስትያን ታሪክ ጊኦግራፊና አርቲሜቲክ እንዲሁም ቅዋንቅዋ ( አማርኛ ኦሮምኛ ስዊድንኛ ጀርመንኛ ) ተማሪዎችን ያሰለጥን እንደነበር ፅፏል

አናሲሞስ በነበረው የትምህርት ብቃት የተነሳ ከተማሪዎቹ ተመርጦ ወደ ስዊድን ለከፍተኛ ትምህርት ተልኳል .....Onesimos nesib የተሰኘወን መፅሀፍ የደረሰው ተርፋሳ ዲጋ በኢትዮጵያ ጥናት ተቅዋም የተዘጋኘውንና ለህትመት ያልበቃውን Dictionary of Ethiopian Biography በመጥቀስ አናሲሞስ የስካንዲኒቭያን ምድር ለምርገጥ የበቃ ቀዳሚ የኦሮሞ ተወላጅ እንደነበር ይናገራል ...........

ቄስ ተስገራ Abba Gemmechis, Onasimos Nesib በተሰኘ ስራቸው አናሲሞስ አማርኛን አረብኛን የስዊድንና የእንግሊዝኛ ቅዋንቅዋዎችን አቀላጥፎ ይናገር እንደነበር እንዲሁም ጀርመንኛ ማጥናቱን ፅፈዋል ..... ኢዶሳ ገመቺስ ደግሞ ትግርኛና ጣሊያንኛ ይናገር እንደነበር ፅፈዋል

በስዊድን ኮሌጅ ለአምስት አመታት የተሰጠውን ትምህርት ተከታትሎ ካጠናቀቀ በህዋላ በ 1873 አ .ም ወዳገሩ ተመልሶ ምፅዋ ደረሰ .....እዝያው ምፅዋ ውስጥ በማስተማር ሙያ ተመድቦ ማገልገል ጀመረ .......ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ pioneers of change in Ethiopia በተሰኘው መፅሀፋቸው እንደገለፁት በወቅቱ አፄ ዮሀንስ በሚስዮናውያን ላይ አርገውት በነበረው የእንቅስቃሴ እገዳ ምክንያት ወደ ትውልድ መንደሩ ኢሊባቡር ለመመለስ በርካታ አመታት ፈጅቶበታል ........

በእምኩሉ (ምፅዋ ) ቆይታው በ 1878 አ .ም አነስተኛ የማተምያ መሳርያን ወደ ምፅዋ በማስመጣት 100 songs and psalms (Gallata Wooqayoo Gofta Maccaa) የተሰኘው የአናሲሞስ ስራ የማተምያ ቤቱ የመጀመርያ ስራ በመሆን የህትመትን ብርሀን አየ .........

እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቀው የመፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም ስራ ከፍፃሜ ለመድረስ በርካታ አመታትን ወስዶበታል ...የአዲስ ኪዳን ትርጉም ከሰባት አመታት በህዋላ ተጠናቀቀ ...ብዙም ሳይቆይ በተከታታይ የብሉይ ኪዳንን ትርጉም በታላቅ ትጋት አጠናቆ መፅሀፉን ለማሳተምና የፊደል ለቀማውን ለመስራት እንደገና ወደ ስዊዘርላንድ ለዘጠኝ ወራት ያህል መሄዱን ዶ .ር ድርሻዬ መንበሩ በመፅሀፋቸው ጠቅሰውታል ....በነዚሁ ዘጠኝ ወራትም በባለሙያዎች እንደገና ተሻሽሎ ለመታተም እስከተወሰነበት ድረስ ለሰባ አመታት ያገለገለውን የኦሮምኛ መፅሀፍ ቅዱስ እትመት አጠናቆ ወደ አገሩ ተመለሰ .....

በወቅቱ መሪ ለነበሩት አፄ ሚኒልክም ይህንን የኦሮምኛ መፅሀፍ ቅዱስ በስጦታ በማበርከት ወደ ወለጋ ሄዶ እንዲያስተምር ነጋድራስ ሀይለጊዮርጊስን ባልደረባ በመስጠት የሚከተለውን ንጉሳዊ የይለፍ ደብዳቤ ሰጥተውታል

ጥቅስ፦ ሞአ አንበሳ ዘዕም ነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ሚኒልክ ስዩመ እግዚአብሄር ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ይህን ደብዳቤ ይዞ ደጃዝማች ገ .እግዚአብሄር አገር ለሚያቀናው አናሲሞስ ከርሱ ጋ ላሉት 10 ሰዎችና 3 ጠባቂዎቻቸው ፈቃድ ሰጥተናቸዋልና ማንም መንገዳቸው ላይ አይቁም :


ዋና የትምህርት ጣብያውን ነቀምት ያረገው አናሲሞስ በአገሩ ሰዎች የሞቀ አቀባበል ቢደረግለትም .......ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ በእምነቱ ምክንያት ፊታቸውን ስላዞሩበት .....በደረሰበት ስደት ምክንያት ንብረቱን ከመውረስ አልፈው በእግረ ሙቅ ታስሮ ውህኒ እንዲወርድ አርገውታል ........ለጥቂት ጊዜያትም ቢሆን አንፃራዊ እረፍት ያገኘው በ 1909 አካባቢ ከልጅ እያሱ ባገኘው የእምነት ነፃነት በህዋላ ነው ....

ከመንፈሳዊ ትምህርቱ ጎን ለጎንም የአገሬውን ሰዎች ልጆች በመሰብሰብ ማንበብና መፃፍ ከማስተማሩም በላይ ባንድ ወቅት የተማሪዎቹ ቁጥር ወደ 100 ያህል ደርሶ እንደነበር ይነገራል .....በአካባቢው ሰዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ያስደነገጣቸው አቡነ ማቴዎስና ተከታዮቻቸው በተደጋጋሚ ክስ እየሰነዘሩበት ማስፈራራትና ዛቻ በመቀበል እስከ መጨረሻው ድረስ በእምነቱ ፀንቶ ኖርዋል ... ይህን ታላቅ ሰው በእለተ ሰንበት በሰማንያ አንድ አመቱ በወርሀ ሰኔ 1923 አ .ም እስከወድያኛው ድረስ ሩጫውን ፈፅሞ አንቀላፍቷል .......ነፃው አናሲሞስ የቀዳሚውንም ሆነ የህዋላኛውን ስሙን ትርጉም በሚገባ ኖሮ አለፈ .....አናሲሞስ የሚለው የተፀውኦ ስም የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ጠቃሚ ማለት ነው .....