ኦነሲሞስ ነሲብ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ቅዱስ ኦነሲሞስ ነሲብ ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሓፍ ቅዱስን በግዕዝ ፊደል ወደ ኦሮምኛ ወይም ኣፋን ኦሮሞ የተረጐሙና የጻፉ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው። «መጫፈ ቁልቁሉ ኣፋን ኦሮሞ» የተተረጐመው ከፈረንጆች ቅጂ ሲሆን ኦነሲሞስ በኣሜሪካ ሉተራን ኣምልኮ መጽሓፍ ኣፍሪቃዊ ቅዱስ ናቸው። መጽሓፉ የታተመው በ፲፰፻፺፪ ዓ.ም. ነው።

Portrait of Onesimus Nesib.jpg

ኦነሲሞስ መጽሓፉን ሲጽፉ የግዕዝ ኆኅያት ውስጥ ያልነበረውን «ዸ» ወይም በላቲን ወደ «dh» ድምፅ የቀረበውን ቀለምና እንዚራኖቹን በመፍጠር ተጠቅመውበታል። እነዚህን ቀለሞች ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙባቸው ቆይቶ የግዕዝን ፊደል ለመጀመሪያ ጊዜ ኮምፕዩተር እንዲጠቀም ዘዴውን የፈጠሩትም ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ኣበራ ሞላ በ፲፱፻፸ዎቹ ጨምረውታል።

ደግሞ ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የውጭ ማያያዣዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]