አዊ ብሄረሰብ ዞን

ከውክፔዲያ

አዊ ዞን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

➡ የዞኑ ዋና ከተማ፡- እንጅባራ

➡ የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለው ርቀት-122 ኪ.ሜ

➡ የወረዳዎች ብዛት፡- 9

  1. አንካሻ ጓጉሣ
  2. ባንጃ ሽኩዳድ
  3. ጓጉሣ ሽኩዳድ
  4. ፋግታ ለኮማ
  5. ዳንግላ ወረዳ
  6. ጃዊ ወረዳ
  7. ጓንጓ ወረዳ
  8. ዚገም ወረዳ
  9. አዘና ወረዳ
➡ የከተማ አስተዳደሮች 

ብዛት፡- 5

➡ የቀበሌዎች ብዛት፡-201

  • የገጠር፡-180
  • የከተማ፡- 23

➡ በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡-1,058,289

  1. ወንድ=916,015
  2. ሴት=142,274

➡ የወረዳው ስም የወረዳው ዋና ከተማ

  1. አንካሻ ጓጉሣ - አገው ግምጃ ቤት
  2. ባንጃ ሽኩዳድ - እንጅባራ
  3. ጓጉሣ ሽኩዳድ - ቲሊሊ
  4. ፋግታ ለኮማ - አዲስ ቅዳም
  5. ዳንግላ ወረዳ - ዳንግላ
  6. ጃዊ ወረዳ - ፈንድቃ
  7. ጓንጓ ወረዳ - ቻግኒ
  8. ዚገም ወረዳ - ቅላጅ
  9. አዘና/አዮ ወረዳ - አዘና

የአገው ሕዝብ አሁን በሚገኝባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ራሱን የሚገልጸው  አዊ ፡ኽምራ፡ቅማንት ፡ብሊን በሚሉ አካባቢያዊ መጠሪያዎች ነው ![ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የስያሜው እድገት ከራሳቸው ወይም በጋራ  ከሚገኝ ማህበረሰብ ክፍሎች ተጨማሪ ቋንቋ የተዋሱት  ነው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

✓አዊ ማለት አገው ማለት ነው ፡የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ ቋንቋ አገውኛ ነው ሌሎችንም ራሱንም  አገው ለማለት ና ለመግለጽ ይህንኑ ቃል ይጠቀማል።[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ትርጉሙ በአዊኛ ብራሃን ማለት ነው

✓ ኽምራ ማለት አገው ማለት ነው የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ ቋንቋ አገውኛ ነው ፡ሌሎቹንም ራሱንም  አገው ለማለት ይኸንኑ ቃል ይጠቀማል።[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

✓ቅማንት ማለት የቤተሰብ ውቅር  አሰያየም ወይም የባሕላዊ ሃይማኖት ማህበረሰባዊ ልየታ ሲሆን የቃሉ መነሻና ምንጭ  አማርኛ ነው ፡  ቃሉን የሚጠቀሙት   የኦርቶዶክስ ክርስትያን ተከታዬች ሲሆኑ  ክርስትናም ይሁን ይሁዲ እምነት የማይከተሉትን  ቀደምት አገዎችን ክርስትያን አማሮች የሚገልጹበት ስያሜ ነው ።[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

✓ብሊን ማለት አገው  ማለት ነው ፡የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ አገውኛ ቋንቋ፡የቤላ ትውፊትና በጋራ ካሉት የሳሆ  ቋንቋ ተናጋሪዎች የተወሰደ ሲሆን አገዎች ራሳቸውንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ደግሞ አገዎችን ለመግለጽ ይጠቀሙበታል።[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአገው ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እማዱክ ታሪክ መግቢያ አገው ምድር (አዊ ላጜታ) በሀገሪቱ ስርዓት አዊ ብሄ/አሰ/ዞን እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰው ያልነበረበት ፣ጥቅጥቅ ያለ ጫካ በዱር አራዊት የተሞላ ፣ ንፁህ የአየር ንብረት ለም አፈር ፣በቂ ውሃ ምቹ መልካአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የጫካ ማር ያለበት ጠፍ እንደነበረ አፋአዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ቦታ ስያሜ የተሠጠው በአካባቢው በቀዳሚነት በሰፈሩት ሰባቱ አገው ወንድማማቾች መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አገው ምድር እየተባለ የሚጠራው ቦታ በመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ሲሰየም ክልሉ (ወስኑ እስከ የት እንደነበር በትክክል መግለፅ ባይቻልም ከአሁኑ አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስር ካሉ ወረዳዎች በላይ እንደነበር እንዲሁም በምስራቅ ጎጃምና ደ/ጎንደር አካባቢ በአዊኛ ቋንቋ የሚጠሩ አካባቢዎች (ቦታዎች )መኖራቸው ለብሄ/አስ/ዞን ወስንና ስፋት ዋነኛ እማኞች ለምሳሌ፡- ድኩል ካን ፣ዳድ ዩሃንስ (ምስ/ጎጃም ) ቢዝራ ካኒ (ጎንደር) ጻና (ጣና) የሚባሉት ተጠቃሽ ናቸው ሰባት ቤት አገው (ላጜታ አዊ) የተጠናከረና የተደራጀ መረጀ ባይኖርም በአፈ ታሪክ ደረጃ ከተለያዩ አባቶችና ታሪክ አዋቂዎች የተገኙ መረጃዎች (oral sources) እንደሚጠቁመን የእስራኤል ደም ወገን የሆነው ንጉስ ሰለሞን የልጅ ኩሳ ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር ታቦተ ፅዮንን ከእየሩሳሌም ይዘው ከመጡ በኋላ ንጉስ ኩሳ ሰቆጣ አካባቢ ትዳር መስርቶ በመኖር አዲልን ወለዱ ፣አዲል ደግሞ እና አንከሻ፣ባጃ፣መተከል፣አዘ ና፣ዚገም፣ኳኩራና ጫራን ወለዱ እነዚህ ወንድማማቾች ከአካባቢያቸው ወደ ተለያዩ ቦታ እየተዘዋወሩ ዱር አራዊትን በማደን አዘውትረው ሲኖሩ ኑሮን ለማሸነፍ ፣ህይወትን በተሻለ መንገድ ለመምራት ከተፈጥሮና አካባቢ ጋር መታገል ግድ ይላል ፡፡ ካልሆነም አካባቢን ለቆ የተሻለ አካባቢ ፍለጋ መኳተን አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋል ተግባር ነው ፡፡ ስለሆነም ስባቱ አገዎች በአንድ ተሰማርተው በወቅቱ ውድና ተፈላጊ የሆኑ የዱር አራዊት ማለትም የዝሆን ጥርስ ፣ጥርኝ ፣ዝባድና የመሳሰሉትን ፍለጋ ሲጓዙ የትውልድ ቦታቸውን ስቆጣ ለቀው አሁን እንጅባራ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ (ከሰንግ ይባል )ነበር ደርሰው አሁንም በአዊኛ “አንጉች ካና” ይባላል ፡፡ አካባቢው ምንም ሰው የሌለበት ፣በቂ የሆነ የዱር አራዊትና ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ፣የዱር ማር ያለበት ፣ምቹ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥና ሰላም የሰፈነበት ቦታ ሆኖ በማግኘታቸው በአካባው ሁኔታና ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ በመማረክ ለሰባት ወራት ያህል የዱር አራዊትን በማደን ቆይተው ሰባቱም ወንድማማቾች ወደ ቤተሰቦቻቸው (ሰቆጣ ) በመመለስ፣ለቤተሰቦቻቸውም ተመላልሰው ስለተመለከቱት አካባቢ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ ፣ለኑሮ ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት ፣በውስጡ ያሉ የዱር አራዊትና ተፈጥሮአዊ ገፅታ ሲገልፁላቸው ቤተሰቦቻቸውም በሀሳባቸው ተስማምተው ለጥያቄአቸው አወንታዊ ምላሽ በመስጠት መልካም ፈቃዳቸውን መርቀው ልጡን ገመድ፣ባዳውን ዘመድ ያድርላችሁ ሲሉ ሰባቱ ወንድማማቾች ሚስቶቻቸውን ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውን እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው አገልጋያቸው ትሆን ዘንድ የተላከቸውን አዱክን ጨምረው ጎዞቸውን ወደ ተመለከቱት አካባቢ ቀጠሉ፡፡ ወደ አዲሱ አካባቢ ደርሰው በታላቃቸው አንከሻ መሪነት ቦታ ሲከፋፈሉ አንከሻና ባንጃ አማካኝ የሆነ ቦታ ሲይዙ ኳክራን በምስራቅ ፣ጫራን በምዕራብ፣ዚገም፣መተከልና አዘና በስተደቡብ እንዲቀመጡ አድርገዋል፡፡ አማካይ በሆነ አቅጣጫ አንከሻና ባንጃ በመሆን አዱክ ታገለግላቸው ነበር ፡፡ በተጨማሪም ለሌሎች ወንድማማቾች በመሆኑ እንደ መገናኛ ይጠቀሙበት ነበር ይላሉ የታሪክ አባቶች ፡፡ አዱክ ከሰባቱ ወንድማማቾች ጋር በአገልጋይነት ከሰቆጣ የተላከችው አዱክ ስትቅልባቸውና ስታገለግላቸው ኑራ አምስቱ በተልያዩ አቅጣጫ ቦታ ቦታቸውን ሲይዙ እሷ ግን በታላቃቸው አንከሻና ባንጃ መካከል በመሆን እንድትኖር ተደርጓል፡፡ በመሆኑም አገልጋያቸው አዱክ በዕድሜ እየገፋች ለስራ ጉልበቷ እየደከመ ሲሄድ እንደገና መጦር ግድ ሆነባት ፡፡ በሁለቱ ወንድማማቾች ትርዳና ትጦር ጀመር ይህም ሲሆን አንከሻ በደቡብ አብልቶ አጠጥቶ አጥቦና አልብሶ ድንበራቸው በሆነ ቦታ ላይ ፀሐይ ሲሞቅ ብርዱም ሲለቅ አስቀምጦ ሲሄድ ፣ባንጃም በተራው በመውሰድ ቤቱ አሰንብቶ ለተረኛው ሲሰጥ እንደቤቱ አብልቶና አጠጥቶ በጥዋቱ ፀሐይ ሰትታይ ከቦተዉ የደርሣት ነበር በመሆኑም አዱክ በጥዋቱ ቁርና በቀጥር ሙቀት ይፈራረቀባት ስለነበር አንከሻንና ባንጃን ትመርቃቸው ነበር ይላሉ አባቶች(አባሆይ ዘሩ አለሙ) አንከሻን /ክምምባ ኹ ክም አንካ እይምኽ /እስከ ማታ ብላ ባንጃን ስግላ ቻንቑዋ ስግላ አንካ ኹ /የማለዳ እንጀራ ብላ/ እማ አዱክ የተለያዩ መላምቶች “አዱክ” የሰባቱ አገው እናት ናት እየተባለ ሲወራ ይስተዋላል ፡፡ ስለሆነም ከተለያዩ አባቶች ታሪክ አዋቂዎችና የአካባቢ ነዋሪዎች የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው አዱክ የሰባቱ አገው ወንድማማቾች “ ወላጅ እናት ” አይደለችም ነገር ግን እነሱ ወደ ዚህ አካባቢ ሲመጡ ከቤተሰቦቻቸው የተላከች አገልጋያቸው (ሞግዚታቸው ናት ) የሰባቱ ወንድማማቾች እናት ማናት ? ሲባል አዱክ ይባላል ይህም የሆነበት ምክንያት 1. የብረሄረሰቡ ባህል ፣ ቋንቋና ወግ መሰረት በዕድሜ ትልቅ የሆነች እህት ፣አክስት ፣የእንጀራ እናት ወይም አሳዳጊ 2. በኢትዮጴያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት የክርስትና እናት 3. በመኳንት ወይም መሳፍንት ቤተሰብ ቤት ውስጥ የምታገለግል ፣ሴት የልጅ ጠባቂ ፣ቀላቢ እና ተንከባካቢ እንደ ወላጅ እናት “እናት” ተብላ እንደምትጠራ ይታወቃል ፡፡ ስለሆነም አዱክ የሰባቱ አዊ እናታቸው ሳትሆን ቀላቢያቸውና አገልጋያቸው እንዲሁም የልጆቻቸው ሞግዚታቸው በመሆኗ እናት ተብላ ትጠራለች ፡፡ አዱክ በአንዳንድ አካባቢዎች እማ-አዱክ ተብሎ ስሟ ሲጠራ ይስተዋላል፡፡ ይህ የሆነው “እማ” የሚለው ቅፅል ስም በዕድሜ ትልቅ ለሆኑ ሴቶችና እናቶች የሚሰጥ የክብር ስም በመሆኑ አዱክ የሰባት አገዋች አገልጋያቸውና የልጆቻቸው ሞግዚትም ስለሆነች እማ አዱክ እየተባለች በክብር ስትጠራ፣(በማ/ሰቡ ባህል ፣ወግ፣ቋንቋ የእምነት ስርዓት መሰረት ፣ታላቆችን በስም ብቻ አይጠሩም ፣በአክብሮት፣በትህትናና በማዕረግ ስማቸው ይጠራሉ። የአዱክ መቃብር በኳሪ ጎኻና ቀበሌ ፣በተርዬ ታራረ ዙሪያው በጥድ ዛፍ የተከበበ ካችንቲ ተራራ (አለት በስተ ደቡብ ፣የእማ አዱክ መቃብር ስፍራ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም የድንጋይ ቁልል ይታያል፡፡ የመቃብር ቦታ እዚህ ለመሆኑ የሚያመለክቱ መረጃዎች 1. እማ አዱክን አንከሻና ባንጃ ይጦሯት ስለነበረና ይህ ቦታ ደግሞ የሁለቱ ወሰን (ድንበር መሆኑ ) 2. አንከሻና ባንጃ በሚጦሯት ጊዜ የሚረካከቡበት ቦታ ስለነበር 3. ይህ ቦታ ለሰባቱም ወንድማማቾች አማካይ (መገናኛ) በመሆኑ በታላቆች ምክርና መሪነት መመሪያቸው 4. በወቅቱ በቅርብ ርቀት (አካባቢ ቤተ ቤተክርስቲያን አለመኖር ተጠቃሽ አፋዊ መረጃዎች ናቸው ፡፡ በሰሜን የባንጃ በአሁኑ ወረዳችን ፋግታ ለኮማ ፣በስተ ደቡብ የአንከሻ (በሁኑ ባንጃ ወረዳ ) ክልል ፣ከአ/ቅዳም ከተማ ወደ ኮሰበር በሚወስደው ------መንገድ ፣አሮጌ እንጅባራ ወይም በድሮ አጠራር ሰፈር ገቢያ እንዳደረስን ወደ ቀኝ በኩል በመታጠፍ ቀጥ ብለን ብንሄድ በግራና በቀኝ በጥድ ዛፍ የተከበበ ልዩና ማራኪ የሆነ ታሪካዊ ቦታን እናገኛለን፡፡ ይህ ቦታ - በቀደምት አዱክን አንከሻና ባንጃ የሚረካከቡበት ሲሆን - ዙሮ ዙሮ ቤት ፣ኑሮ ኑሮ ሞት እንዳሉ በኋላም የእማዱክ መቃብር ስፍራ ነው ፡፡ እዚህ ቦታ መሀል ለመሀል ሰፊ የሆነ ጎዳ/መንገድ ከአ/ቅዳም ና እንጅባራ ወደ ኳሪ ጎኻና የሚያደርስ ሲኖረው በዚህ መንገድ የሚያልፍ ማንኛውም ሰው እንደሌለው አካባቢ ምንገድ አቋርጦ አያልፍም / አይሄድም ልዩ የሆነ ባህላዊ ታሪካዊ ስርዓት ያለማንም መካሪነትና ትዕዛዝ ሲፈፀም/ሲከናወን ይታያል፡፡ ይኸውም መንገደኛው እማዱክ መቃርብ ሊደርስ የተወሰነ ርቀት ሲቀረው በቀኝ እጁ ድንጋይ ይዞ መጣል አያያዙም እንደ ማንኛውም ተራ ውርወራ ሳይሆን ልክ በቀኝ እጁ ይዞ በትክሻው ቀጥታ ቦታው ላይ ሲደርስ በቀኝ በኩል ካለው የድንጋይ ክምር ይጠለዋል ፡፡ በመቀጠልም እዚች ቦታ ላይ ቁጭ ብሎ ያርፋል ፡፡ ይህ የሚካሄደው ምን ጊዜ በቀኝ በኩል ባለው ስፍራ ነው ፡፡ ለምን ቢሉ - በቀኝ እጅ መያዛቸው ቀኝ እጅ ሁልጊዜም ገር ፣ቀናና መልካም ዕድልና ምኞች በመሆኑ - ከቦታው ሲደርሱ ማረፊያ መቀመጫቸው ከእናታቸው በረከት ለመሳትፍ - ድንጋይ መጣል እረም ማውጣት ለመቃብር መታሰቢያነት ይህም በማ/ሰብ ወግና ባህል መሰረት ሰው ሲሞት እልቅሶ ቦታ ላይ ሲደርሱ ፊት ይጠረጋል ፣ቁጭ ብለው መነሳት፣ለወደፊቱም ለነፍስ መልካም መመኘት የተለመደ ስርዓት ነው ፡፡ የተለያዩ የፅሑፍ መረጃዎችን አፋዊ መረጃዎችን በመጠቀም መረጃዎችን በመሰብስብ ፅሑፉን ማጠናከር ተችሏል ፡፡ ማጠቃለያ ወረዳችን ይህንና የመሳሰሉ ጥንታዊና ታሪካዊ ህዝብ ባለቤት ልዩ ልዩ ጥንታዊና ባህላዊ ቅርሶች መገኛ የተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ መስህብ ስፍራዎች ባለቤት መሆኑን መገለጫ ለሆነው ባህላችንና ቅርሶቻችን ትኩረት ሰጥተን መጠበቅ መንከባከብና ተጠብቀው ለትውልድ የሚተላለፉበትን መንገድ ማመቻቸት የሁላችንም የህሊና ግዴታ ሊሆን ይገባናል ፡፡

የአገው ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአገው ታሪክ እጅግ ሰፊ ነው፡፡ ባለታሪክ ህዝብ አሁን ሰዓት በአስተዳደር ችግር ወደ ልመነ ወጦዋል

  • የላስታ _ ዋግ ( ዛጔ ) ነገሥታት ስም ዝርዝርና የነገሱበት ዘመን

1. መራ ተክለ ሃይማኖት ...920 _ 933 አ.ም ...13 አመት

2. ስቡሀይ ( ድልነአድ )...933 _ 943 አ.ም ...10 አመት

3. መይራሪ ... 943 _ 958 አ.ም ...15 አመት

4. ሀርቦይ ( ሀረየነ እግዚእ ) ...958 _ 966 አ.ም ...8 አመት

5. መንግሥትነ ይትባረክ...966 _ 973 አ.ም ...7 አመት

6. ይእቀብከ እግዚእ...973 _ 983 አ.ም...10 አመት

7. ዜና ጴጥሮስ ...983 _ 989 አ.ም...6 አመት

8. ባሕር ሰፍ...989 _ 1003 አ.ም....14 አመት

9. ጠጠውድም ( ፀር አሰግድ )...1003 _ 1013 አ.ም ...10 አመት

10. ጃን ስዩም ( አኩቴት ) ...1013 _ 1033 አ.ም...20 አመት

11. በእምት ( ግርማ ስዩም )...1033 _ 1053 አ.ም ...20 አመት

12. ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ...1053 _ 1093 አ.ም...40 12. ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ...1053 _ 1093 አ.ም...40 አመት

13. ቅዱስ ገብረ ማርያም...1093 _ 1133 አ.ም...40 አመት

14. ቅዱስ ላሊበላ...1133 _ 1173 አ.ም...40 አመት

15. ነአኩቶ ለአብ ...1173 _ 1213 አ.ም...40 አመት

16. ይትባረክ ... 1213 _ 1253 አ.ም...40 አመት

  • የነገሱበት አመት ድምር 333 ይሆናል።

@ ምንጭ # የአገው ህዝቦች ና የዛጉዌ ስርወ መንግስት ታሪክ

  • በ ዶ/ ር አያሌው ሲሳይ

@ ከገፅ 92 የተወሰደ።