አፐር-አናቲ
Appearance
==
አፐር-አናቲ | |
---|---|
«ሂክሶስ አፐር-አናቲ» የሚል ጥንዚዛ | |
የግብጽ (ሂክሶስ) ፈርዖን | |
ግዛት | 1642-1638 ዓክልበ. ግ. ? |
ቀዳሚ | ሳኪር-ሃር |
ተከታይ | ኽያን |
ሥርወ-መንግሥት | 15ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
አፐር-አናቲ በጥንታዊ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን የ15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን ነበር። ስሙ ወይም ሕልውናው በአንድ ቅርስ ብቻ ተገኘ፤ ይህም «ሂክሶስ (ሄቃ-ኻሱት) አፐር-አናቲ» በሚል ጥንዚዛ ምልክት ላይ ነው። ከመጀመርያ ሦስቱ የሂክሶስ ፈርዖኖች አንዱ እንደ ሆነ ይታሥባል፣ የትኛው እንደ ሆነ ግን እርግጥኛ አይደለም።
በማኔቶን ልማድ እንደ ተገለጸ፣ የሂክሶስ ሁለተኛ ንጉሥ «ብኖን» ወይም «ባዮን» ይባላል፣ ለ44፣ 40፣ ወይም በአንድ ምንጭ ለ4 ዓመታት ገዛ። እነዚህ ስሞች በዘመናት ላይ ከግብጽኛ በቅብጥኛ፣ ግሪክኛና በሌሎች ልሳናት በኩል በመተረጎማቸው ቢዛቡም፣ ይህ ሁለተኛ ሂክሶስ አለቃ «ብኖን» እና «አፐር-አናቲ» አንድ ሊሆኑ ይቻላል። ስለዚህ በግምት ዘመኑ ምናልባት 1642-1638 ዓክልበ. ያህል ሊገኝ ይቻላል።
ቀዳሚው ሳኪር-ሃር |
የግብፅ (ሂክሶስ) ፈርዖን 1642-1638 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኽያን |
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)