ኢሳያስ አፈወርቂ

ከውክፔዲያ


ኢሳይስ አፈወርቂ ኣብረሃም እስካሁን ድረስ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ናቸው። ኢሳያስ አፈወርቅ ለረጅም አመታት ለኤርትራ ነፃነት የታገሉ መሪ ናቸው። አሁን በስልጣን ዘመናቸው አገሪቱን ለማልማት በጥቂት ደሞዝ ያገለግሉ ይገኛሉ። የኢሳያስ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቅ አብርሃ ይባላሉ፤ እናቱ ወይዘሮ አዳነች በርሄ ይባላሉ።

ልጆቻቸውም፦

  • አቶ አማረ አፈወርቅ (አፈወርቂ)
  • አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ
  • አቶ አማኑኤል አፈወርቅ
  • አቶ ኤርሚያስ አፈወርቅ
  • አቶ ዮናስ አፈወርቅ
  • ወ/ሮ ጽጌረዳ አፈወርቅ
  • ወ/ሮ አርዮን አፈወርቅ


በናታቸው በኩል የኢሳያስ አጎቶች፦

  • ደጃዝማች ሰለሞን አብርሃ
  • ካፒቴን መኮንን አብርሃ
  • አቶ ሓጎስ አብርሃ ናቸው።

የአቶ ኢሳያስ አጎት ደጃዝማች ሰለሞን አብራሃ (በጊዜው ሲጠርዋቸው በነበሩ ጋዜጦች አጠራር «ሰለሞን አብሃም») በዓጼ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥት ማለት (በ1946 ዓ.ም.) የወሎ እንደራሴ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። በዚያ ጊዜ መቀሌ ከተማ ውስጥ ተደራጅቶ የነበረው የባህል ቡድን አስመራን ከጎበኘ በሗላ ወደ ደሴ መጣ። እንደራሴው ደጃዝማች ሰለሞን ለክብር እንግዶቹ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ምስጋናቸውን ለቡድኑ ከገለጹ በሗላ እሳቸውም ትግሬ መሆናቸውን አንስተው የባህል ቡድኑ የትግራይ ባህላዊ ሙዚቃ እና ባህላዊ ውዝዋዜ ለማስፋፋት ላደረገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸው ገለጹ።

በተጨማሪም የደጃዝማች ሰለሞን እናትም አጋሜ አውራጃ ውስጥ ተወላጅ ትግሬ መሆናቸውን እና አባታቸውም በትግራይ ክ/ሃገር ውስጥ የተምቤን ተወላጅ መሆናቸውን አንስተው ለባህል ቡድኑ ገልጸውላቸዋል።

የባሕር ሃይል ካፒቴን የሆኑት ካፒቴን መኮንን አብርሃ የእቴጌ መነን ትምሕርት ቤት ተማሪ የነበረቺው የደጃዝማች ገብራይ ልጅን አግብተው ሦስት ልጆች እንደወለዱ ይታወቃል። አቶ ሐጎስ አብርሃም ቢሆን በአዲስ አበባ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የጥንት ተማሪ ሲሆን ለዚያው ተማሪ ቤት የእግር ኳስ ቡድን በረኛ ነበር፣ ሆኖም በበሽታ ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ ለጥቂት ጊዜ በብሔራዊ ባንክ ስራ ተቀጥሮ እየሰራ እንዳለ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ይታወቃል።

የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አያቶችና ሌሎች ዘመዶቻቸውም - በሚመለከት፦ በእናቱ በኩል የኢሳያስ አፈወርቂ አያት (የእናት እናት) ወይዘሮ መድህን «በራድ» ይባላሉ። በራድ (ተብለው በቅጥያ ስም የተጠሩበት ምክንያት ወ/ሮ መደህን በጠጅ ስራ ንግድ ተሰማርተው ይኖሩ ስለነበር «ጠጅ» ባካባቢው የሚቀዳው «በራድ» ተብሎ በሚታወቀው «ማንቆርቆርያ» ስለነበር ነው። መድህን የኢሳያስ እናት የወይዘሮ አዳናች በርሄ እናት ናቸው። ኢሳያስ የልጅነት ትምህርቱ የተከታተለው በሴት አያቱ በወይዘሮ መድህን ተንከባካቢነት ነው። ወ/ሮ መድህንም በትውልዳቸው ዓድዋ ሲሆኑ፣ የፊታውራሪ ኪዳነ መስቀል አጎት ናቸው።

ፊታውራሪ ኪዳነ የአቶ የማነ ኪዳነ (የየማነ ጃማይካ) አባት ናቸው ይባላል። ይህ እውነት ከሆነ የአቶ የማነ ኪዳነ (ጃማይካ) እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ «በኢትዮጵያ አጠራር» ወንድማማቾች ናቸው። በአውሮጳውያኖች አጠራር ግን «የአጎት ልጆች ናቸው»። ባጭሩ አሥመራ የሚገኙ አክራሪ ጠላቶች ናቸው የሚባሉት አብዛኛዎቹ የትግራይ ዝርያ የሆኑና በተለይ ከትግራይ በጠቅላላም ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ የስጋ ፣ የአጥንት እና የደም ቁርኝት ያላቸው ናቸው። የኢሳያስ አክስት (የኢሳያስ እናት እህት) ወ/ሮ ሃና ይባላሉ። የአቶ በላይ ባለቤት ናቸው። አቶ በላይ የዓድዋ ሰው ናቸው። እንደሚባለውም ልጆቻቸው ስዊድን ሃገር ውስጥ ይኖራሉ። በእናታቸው በኩል የአቶ ኢሳያስ አጎት የሆኑት ከዓድዋ ተወላጅ ከሆኑት በአሁኑ ጊዜ ጀርመን ውስጥ የሚኖሩ ወ/ሮ ዘውዴ የሚባሉትን ወልደዋል። ከላይ በተገኘው መረጃ መሰረት የአቶ ኢሳያስ ኤርትራዊነት ኤርትራ መሬት መወለዳቸው ብቻ ነው። የአቶ ኢሳያስ ባለቤትም ወ/ሮ ሳባ ሃይለ ይባላሉ። ኤርትራዊት ናቸው።