Jump to content

ኢሳያስ አፈወርቂ

ከውክፔዲያ
(ከኢሳይያስ አፈወርቂ የተዛወረ)


==

ኢሳያስ አፈወርቅ
አቶ ኢሳያስ እኤአ በ2022 የተነሱት
አቶ ኢሳያስ እኤአ በ2022 የተነሱት
ባለቤት ሳባ
ልጆች 3 ልጆች
አብርሃም ኢሳያስ
ኤልሳ ኢሳያስ
ብርሃኔ ኢሳያስ
የተወለዱት አስመራ፣ ኤርትራ
ፊርማ የ{መለጠፊያ:ስም ፊርማ

==

ኢሳያስ አፈወርቅ (እኤአ ፌብራሪ 2፣1946 የተወለዱ) ፖለቲከኛ እና የኤርትራ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፣ ለ30 ዓመት የዘለቀው እና የኤርትራ የነጻነት ትግል እየተባለ የሚጠራው ጦርነት ተጠናቆ የኤርትራ ሀገረ መንግስት ከትቋቋመ እኤአ ክ1991 ዓም ጀምሮ እስክ አሁን የኤርትራ መንግስት ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። በተጨማሪም፣ ኢሳያስ አፈወርቅ መጀመሪያ የህዝባዊ ግንባር (ሻዕብያ) መሪ፣ በኋላም ህዝባዊ ግንባር ወደ ህግደፍ ሲቀየር የህግደፍ መሪ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።

በኤርትራ ህገመንግስት፣ ምርጫ፣ ህግ አውጭ፣ እንዲሁም የሚታወቅ በጀት የሌለ ሲሆን፣ የህግ አስፈጻሚው፣ ወታድራዊወ፣ እንዲሁም የህግ አውጪው ስልጣን በፕሬዝዳንቱ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ይህም በመሆኑ የተነሳ፣ አንዳንድ የአካዳሚክ ምሁራን እና የታሪክ አዋቂዎች አቶ ኢሳያስን እና መንግስታቸውን ፈላጭ ቆራጭ መንግስት እና አንባገነን እያሉ ይጠሯቸዋል። በተጨማሪም፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ደግሞ በሃገሪቱ ያለው የአገራዊ አገልግሎት በአስገዳጅነት የሚፈይፀም የጉልበት ብዝበዛ ነው በማለት በሰብአዊ መብት ጥሰት ይከሷቸዋል። እኤአ ሪፓርተርስ ዊዛውት ቦርደርስ፣ ኢሳያስ የሚመሯትነ ኤርትራ በጋዜጠኝነት ነጻነት ከ180 ሀገራት ውስጥ የመጨረሻዋ አድርጓታል።

የህይወት የመጀመሪያዎቹ አመታት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ኤርትራ፣ አስመራ ውስጥ አባሻውል እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ተወለዱ። አባታቸው ከአስመራ በቅርብ ርቅት ላይ ከምትገኘው ሳሎት አካባቢ የተገኙ ሲሆኑ፣ የትንባሆ ሞኖፐል ፋብሪካ የመንግስት ሰራትኛ ነበሩ። እናታቸው ደግሞ ክትግራይ እንደርታ አካባቢ የተገኙ ናችው። እኤአ በ1965 ዓም በቅድሞው ሃይለ ስላሴ ዩኒቨርስቲ የኢንጂነሪንግ (አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ) ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ። ይሁንና በቅጣዩ አመት ትምህርታችውን አቋርጠው በአስመራ በኩል አድርገው ጀብሃን ለመቀላቀል ሱዳን ከሰላ ገቡ።

እኤአ በ1967 ዓም የቻይና መንግስት የቀላል ጦር መሳሪያ ድጋፍ ለጀብሃ ያደረገ ሲሆን ለተውስኑ የድርጅቱ ተዋጊዎችም ወታደራዊ ስልጠና ሰጥቷል። ለወታደራዊ እና ፖለቲካ ስልጠና ከተላኩት የመጀመሪያ ተዋጊዎች ውስጥ ኢሳያስ አንደኛው ነበሩ። ከስልጠና እንደተመለሱም በጀብሃ ዞን 5፣ሃማሴን አውራጃ ውሰጥ የፖለቲካ ኮሚሳር በመሆን ተመደቡ።

የኤርትራ የነጻነት (ከኢትዮጵያ የመገንጠል) ትግል

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኤርትራ የነጻነት እንቅስቃሴ (ክኢትዮጵያ መገንጠል) እኤአ 1967 የተጀመረ ሲሆን፣ አቶ ኢሳያስም ክጅብሃ ጋር አብረው የቆዮት ለ ሶስት ዓመታት ብቻ ነው። እኤአ ነሃሴ 1971 ዓም የተወሰኑ የጀብሃ አባላት በሰሜናዊ ቀይ ባህር አውራጃ ልዩ ስሙ ጠቅል በሚባል ስፍራ ስብሰባ በማድረግ ሰልፊ ናጽነት በኋላም ህዝባዊ ግንባርን መሰረቱ። በዚህም ስብሰባ ኢሳያስን ጭምሮ አምስት አመራሮች ተመርጠዋል። እነዚህም አመራሮች ኮሚቴ በማዋቀር በትግርኛ ንህና ዕላማና (እኛና አላማችን) የሚል ሰነድ አዘጋጅተው በማሰራጨት፣ የጀብሃን አመራር የትቹበት እና ራሳቸውን ከጅብሃ ለይተው አዲስ ድርጅት እንዳቋቋሙ ይፋ ያደረጉበት ዶሴ ነበር። እኤአ 1971 ዓም ህዝባዊ ግንባር የመጀመሪያውን ጉባኤ ያደረገበት ጊዜ ሲሆን በወቅቱም ኢሳያስ የድርጅቱ ምክትል ጸሀፈ ጀነራል ተደርገው ተመርጠዋል።

በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት በኤርትራ ትጥቅ ትግል ውስጥ ከነበሩት አመራሮች ውስጥ በድርጅቱ ደጋፊ እና አባላት ዘንድ ከፍተኛ ዝናን ያገኙት ኢሳያስ፣ በሰላሳ አመት የትጥቅ ትግል ውስጥ ድርጅታቸው ህዝባዊ ግንባርን እየመሩ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በትብብር የስሩ ሲሆን፣ ክዚህ ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ ድርጅት ደግሞ ህወሀት ነው። ሻዕቢያ እና ህወሀት በትጥቅ ትግል ወቅት በአብዛኛው የትብብር ታሪክ ያላቸው ሲሆን፣ ይህም ትብብር እና ግንኙነታቸው ለውጤት በቅቶ እኤአ በግንቦት በ1991 ደርግን እንዲያሸንፉ አስችሏቸዋል። እኤአ በሚያዝያ 1991 ዓም ህዝባዊ ግንባር (ሻዕቢያ) አስመራን ሲቆጣጠር፣ በቀጣዩ ወር ደግሞ ህወሃት (ኢህአዴግ) አዲስ አበባን ሊቆጣጠር ችሏል። በዛው ዓመት ሰኔ ወር ላይም ኢሳያስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ታዛቢ የሆነበት ሪፈረንደም በኤርትራ እንዲደረግ የመንግስታቱን ድርጅት ጠየቁ።

ፕሬዝዳንትነት (እኤአ ከ1991ዓም እስክ አሁን)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኤርትራ ነጻ ሀገር መሆን

እኤአ በሚያዝያ 1993 ዓም የመንግስታቱ ድርጅት በታዛቢነት የተሳተፈበት በኤርትራ ነጻ ሀገርነት ላይ የሚወስን ሪፈረንደም የተደረገ ሲሆን በቀጣዩ ወርም ኤርትራ ከኢትዮጵያ የትለየች ሀገር እንደሆነች አለማቀፋዊ የህግ እውቅና ልታገኝ በቅታለች። አቶ ኢሳያስም የአዲሷ አገር ኤርትሪያ የመጀምሪያው ፕሬዝዳንት ሆነው በብሄራዊ አሴምብሊ የተመረጡ ሲሆን ሌላ ዙር ምርጫ እስከ አሁን አልተካሄደም።

እኤአ በፌብራሪ 1994 ዓም ህዝባዊ ግንባር ሶስተኛውን ጉባኤ በማካሄድ የፓርቲውን ስም ወደ ህዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲ እና ፍትህ (ህግዴፍ) የቀየረ ሲሆን አቶ ኢሳያስም በጉባኤው ተመርጠው የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆኑ።

ኢሳያስ ኤርትራን እንደተረከቡ አንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ዋነኛ እና እስከ አሁንም ድረስ አከራካሪው የአገራዊ አገልግሎት ፕሮግራም ነው። አገራዊ አገልግሎት ፕሮግራም እኤአ 1994 ዓም ሲታወጅ ለ 18 ወራት ብቻ የሚቆይ ተበሎ የተነገረ ቢሆንም፣ ተግባር ላይ ሲውል ግን የጊዜ ጣረያ የለውም ተብሎ በብዙ አለም አቅፍ ተቋማት እስከ አሁን ድረስ ውግዘት እየደረሰበት ይገኛል። ሃገራዊ አገልግሎት አላማው መሰረታዊ የውትድርና፣ ስለ ሃሪቱ ለሁሉም ማስተማርን አላማው አድርጎ የተንሳ ነው ቢባልም ተግባራዊንቱ ላይ ብዙዎች እስካሁን መራር ተቃውሞ እያነሱበት ይገኛሉ።

የሃገር ውስጥ ፖሊሲዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ምርጫ

በመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመን አቶ ኢሳያስ ተራማጅ አስተሳስብ ያላቸው የአዲሱ ትውልድ የአፍሪካ መረ ተብለው ተብለው በጊዜው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በነበሩት ቢን ክሊንተን ተሞካሽተው ነበር። እኤአ በ1997 ዓም ህገ መንግስት የተረቀቀ ቢሆንም ተግባር ላይ ሳይውል፣ ታቅዶ የነበረ ምርጫም ሳይደረግ እንዲሰረዝ ተደርጓል። እኤአ በ2001 በአሜሪካው ፕሪስተን ዩኒቨርስቲ ባደረጉት ንግግር፣ ህገ መንግስታዊነት፣ ፖለቲካዊ ብዝሃነት፣ ነጻ እና ገለልተኛ ምርጫ የሃገራቱን እውነታ ከግንዛቤ አስገብተው ከተተገብሩ በተፈጥሮአቸው ኢኮኖሚያዊ ብልጽናን ለማረጋገጥ ምርጥ ተቋማዊ መሳሪያዎች ናችው ሲሉ ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ እኤአ በ2001 ዓም ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል።

እኤአ በ2018 ዓም የቀድሞ ጓዳቸው አቶ አምደብርሃን ወልደጊዮርጊስ አቶ ኢሳያስ ስልጣንን የግል ንብረታቸው አድረገው ለመያዝ ብዙ ርቀት የሚጓዙ እና በስልጣን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰው ናቸው ሲሉ ይተቻሉ። አቶ ኢሳያስ ግን ስልጣንን አላግባብ መጠቀምን አስመልክተው እኤአ በ1993ዓም በካይሮ ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሎሎች የአፍሪካ መሪዎችን በስልጣን ላይ ረጅም ጊዜ በመቆየት እና የአምልኮተ ስብእና ግንባታ ላይ መጠመዳቸውን ኮንነው ነበር።

ኢሳያስ ከራምስፊልድ ጋር ያሉበት ፎቶ 2001 ዓም
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር ዶናልድ ራምስፊልድ ጋር እኤአ ዲሴምበር 2002 ዓም

እኤአ በ2000 ዓም፣ 15 የኤርትራ ሚኒስቴሮች (ምክትል ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ) ኢሳያስ ስልጣናቸውን እንዲለቁ በደብዳቤ ጠይቀው ነበር። እኤአ መስከረም 18 በ2001 የብሄራዊ ፕሬስ እንዲዘጋ እና ግንባር ቀደም ተቃዋሚዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አዘዋል። እኤአ በ2010 ዓም በኤርትራ መች ምርጫ እንደሚደረግ በተጠየቁ ጊዜ 3 ወይም 4 አስርታትን መጠበቅ ይኖርብናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኢኮኖሚ

እኤአ በ2009 ዓም ኢሳያስ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ተቋማት እንዲኖሩ እና የኤርትራን ሀገራዊ ሁኔታ እና ሀገራዊ ሀብትን ማዕከል ያደረገ እስትራቴጅ አስፈላጊነትን ጠቅሰዋል። ለእነዚህም ስትራቴጅ መሳካት በትራንስፖርት፣ በኤሌክትሪክ ሃይል፣ በቴሌኮም እና በጤና አገልግሎት መሰረተ ልማት ግንባታ የሚገለጽ ልማት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

የኤርትራ ባንክ እኤአ በ2005 ዓም
የኤርትራ ባንክ እኤአ በ2005 ዓም

እንደ አለም ባንክ ሪፖርት ከሆነ የቅርቡ የኤርትራ የኢኮኖሚ እድገት በግብርና (ግብርና የኤርትራን አንድ ሶስተኛ ኢኮኖሚ የሚሸፍን ወይም 20 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን አጠቃላይ ምርት አስተዋጽኦ ያደርጋል) እና በማዕድን ልማት (ማዕድን 20 በመቶ የሃገሪቱን አጠቃላይ ምርት ይሸፍናል) መስክ መሆኑ ተመልክቷል። እኤአ በ2018 ዓም የኤርትራ አጠቃላይ ምርት በ12 በመቶ ያደገ ሲሆን እኤአ በ2015 እና በ2018 መካከል ምርት በ2.7 በመቶ ቀንሶ ነበር። እኤአ በ2016 እና 2018 መካከል የዋጋ ቅናሽ የታየ ሲሆን ምክያቱ ደግሞ በኤርትራ የተደረገው የገንዘብ ለውጥ እና ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት እንደሆነ ይጠቀሳል።

ኢሳያስ ከቪኦኤ ጋዜጠኛ ጋር በኒውዮርክ እኤአ 2011 ዓም
ኢሳያስ ከቪኦኤ ጋዜጠኛ ጋር በኒውዮርክ እኤአ 2011 ዓም

እኤአ በ2012 ዓም ከአሜሪካ ድምጽ ድርጅት (ቪኦኤ) ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ኤርትራ ለሁለት አስርት አመታት ያስመዘገበችው እድገት በስኬትነት ሊጠቅስ የሚችል እንደሆነ ገልጸዋል። እኤአ በ1998 ዓም በነበረው ቀጣናዊ አለመረጋጋት የተነሳ ኤርትራ ጠንካራ የፊስካል ፖሊስ ተግባራዊ ያደረገች ሲሆን ይሄው ፖሊሲ የመንግስት የካፒታል ፍሰት እና የመንግስት የግብር ገቢ እንዲቀንስ አስተዋጻኦ አድርጓል። አጠቃላይ ሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ ያለው ጫና ሊቀጥል እንደሚችል ይገመታል።

ሰብአዊ መብቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሌሎች ያልተረጋገጡ የቤተሰብ ታሪኮች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢሳያስ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቅ አብርሃ ይባላሉ፤ እናቱ ወይዘሮ አዳነች በርሄ ይባላሉ።

ልጆቻቸውም፦

  • አቶ አማረ አፈወርቅ (አፈወርቂ)
  • አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ
  • አቶ አማኑኤል አፈወርቅ
  • አቶ ኤርሚያስ አፈወርቅ
  • አቶ ዮናስ አፈወርቅ
  • ወ/ሮ ጽጌረዳ አፈወርቅ
  • ወ/ሮ አርዮን አፈወርቅ

በናታቸው በኩል የኢሳያስ አጎቶች፦

  • ደጃዝማች ሰለሞን አብርሃ
  • ካፒቴን መኮንን አብርሃ
  • አቶ ሓጎስ አብርሃ ናቸው።

የአቶ ኢሳያስ አጎት ደጃዝማች ሰለሞን አብራሃ (በጊዜው ሲጠርዋቸው በነበሩ ጋዜጦች አጠራር «ሰለሞን አብሃም») በዓጼ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥት ማለት (በ1946 ዓ.ም.) የወሎ እንደራሴ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። በዚያ ጊዜ መቀሌ ከተማ ውስጥ ተደራጅቶ የነበረው የባህል ቡድን አስመራን ከጎበኘ በሗላ ወደ ደሴ መጣ። እንደራሴው ደጃዝማች ሰለሞን ለክብር እንግዶቹ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ምስጋናቸውን ለቡድኑ ከገለጹ በሗላ እሳቸውም ትግሬ መሆናቸውን አንስተው የባህል ቡድኑ የትግራይ ባህላዊ ሙዚቃ እና ባህላዊ ውዝዋዜ ለማስፋፋት ላደረገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸው ገለጹ።

በተጨማሪም የደጃዝማች ሰለሞን እናትም አጋሜ አውራጃ ውስጥ ተወላጅ ትግሬ መሆናቸውን እና አባታቸውም በትግራይ ክ/ሃገር ውስጥ የተምቤን ተወላጅ መሆናቸውን አንስተው ለባህል ቡድኑ ገልጸውላቸዋል።

የባሕር ሃይል ካፒቴን የሆኑት ካፒቴን መኮንን አብርሃ የእቴጌ መነን ትምሕርት ቤት ተማሪ የነበረቺው የደጃዝማች ገብራይ ልጅን አግብተው ሦስት ልጆች እንደወለዱ ይታወቃል። አቶ ሐጎስ አብርሃም ቢሆን በአዲስ አበባ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የጥንት ተማሪ ሲሆን ለዚያው ተማሪ ቤት የእግር ኳስ ቡድን በረኛ ነበር፣ ሆኖም በበሽታ ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ ለጥቂት ጊዜ በብሔራዊ ባንክ ስራ ተቀጥሮ እየሰራ እንዳለ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ይታወቃል።

የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አያቶችና ሌሎች ዘመዶቻቸውም - በሚመለከት፦ በእናቱ በኩል የኢሳያስ አፈወርቂ አያት (የእናት እናት) ወይዘሮ መድህን «በራድ» ይባላሉ። በራድ (ተብለው በቅጥያ ስም የተጠሩበት ምክንያት ወ/ሮ መደህን በጠጅ ስራ ንግድ ተሰማርተው ይኖሩ ስለነበር «ጠጅ» ባካባቢው የሚቀዳው «በራድ» ተብሎ በሚታወቀው «ማንቆርቆርያ» ስለነበር ነው። መድህን የኢሳያስ እናት የወይዘሮ አዳናች በርሄ እናት ናቸው። ኢሳያስ የልጅነት ትምህርቱ የተከታተለው በሴት አያቱ በወይዘሮ መድህን ተንከባካቢነት ነው። ወ/ሮ መድህንም በትውልዳቸው ዓድዋ ሲሆኑ፣ የፊታውራሪ ኪዳነ መስቀል አጎት ናቸው።

ፊታውራሪ ኪዳነ የአቶ የማነ ኪዳነ (የየማነ ጃማይካ) አባት ናቸው ይባላል። ይህ እውነት ከሆነ የአቶ የማነ ኪዳነ (ጃማይካ) እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ «በኢትዮጵያ አጠራር» ወንድማማቾች ናቸው። በአውሮጳውያኖች አጠራር ግን «የአጎት ልጆች ናቸው»። ባጭሩ አሥመራ የሚገኙ አክራሪ ጠላቶች ናቸው የሚባሉት አብዛኛዎቹ የትግራይ ዝርያ የሆኑና በተለይ ከትግራይ በጠቅላላም ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ የስጋ ፣ የአጥንት እና የደም ቁርኝት ያላቸው ናቸው። የኢሳያስ አክስት (የኢሳያስ እናት እህት) ወ/ሮ ሃና ይባላሉ። የአቶ በላይ ባለቤት ናቸው። አቶ በላይ የዓድዋ ሰው ናቸው። እንደሚባለውም ልጆቻቸው ስዊድን ሃገር ውስጥ ይኖራሉ። በእናታቸው በኩል የአቶ ኢሳያስ አጎት የሆኑት ከዓድዋ ተወላጅ ከሆኑት በአሁኑ ጊዜ ጀርመን ውስጥ የሚኖሩ ወ/ሮ ዘውዴ የሚባሉትን ወልደዋል። ከላይ በተገኘው መረጃ መሰረት የአቶ ኢሳያስ ኤርትራዊነት ኤርትራ መሬት መወለዳቸው ብቻ ነው። የአቶ ኢሳያስ ባለቤትም ወ/ሮ ሳባ ሃይለ ይባላሉ። ኤርትራዊት ናቸው።