Jump to content

ኢቢ-ሲን

ከውክፔዲያ

ኢቢ-ሲን ከ1901 እስከ 1879 ዓክልበ. ግድም ድረስ የኡርና የሱመር ንጉሥ ነበር። የአባቱ ሹ-ሲን ተከታይ ነበር።

ለ፳፫ ዓመቶቹ ሁላቸው በስም ይታወቃሉ፣ ከነዚህም ውስጥ ለምሳሌ፦[1]

  • ኢቢ-ሲን ንጉሥ የሆነበት አመት። (1901 ዓክልበ.)
  • ኢቢ-ሲን የዑር ንጉሥ ሲሙሩምን ያጠፋበት አመት፡ (1899 ዓክልበ.)
  • ኢቢ-ሲን የዑር ንጉሥ ከብዙ ኃያላት ጋር ወደ ሑሕኑሪ ወደ አንሻን ምድር ሄዶ [...] (1893 ዓክልበ.)
  • ኢቢ-ሲን የዑር ንጉሥ በሱስን፣ አዳምዱንና አዋን ላይ እንደ አውሎ ንፋስ ደርሶ በአንድ ቀን አሸንፎአቸው የሕዝባቸውን አለቆች የያዘበት ዓመት። (1888 ዓክልበ.)
  • አሞራውያን፣ ከጥንት ጀምሮ ከተሞች ያላወቁት ኃይለኛ ንፋሶች፣ ለኢቢ-ሲን ለኡር ንጉሥ የገዙበት ዓመት። (1885 ዓክልበ.)
  • ዑር በታላቅ ዐውሎ ንፋስ ተመትቶ ኢቢ ሲን የዑር ንጉሥ ኡርን ጸጥ ያደረገበት ዓመት። (1880 ዓክልበ.)
  • የውጭ አገር ደደብ ዝንጀሮ በኢቢ-ሲን በዑር ንጉሥ ላይ የመታበት ዓመት። (1879 ዓክልበ.)

በኢቢ-ሲን ዘመን የዑር መንግሥት ኃይል እየወደቀ ነበር። በመጀመርያው ዓመት ጠላቶቹ አሞራውያንና ኤላም ያስቸግሩት ጀመር። በዚያም ዓመት ታላቅ ረሃብ በመካከለኛ ምሥራቅ ጀመረ። ኢሽቢ-ኤራ አንድ አሞራዊ ሹም ከማሪ ሲሆን ኢቢ-ሲን የኒፑርና የኢሲን ገዥ አደረገው። በረሃብ ምክንያት እህል ለዑር ለመግዛት ኢቢ-ሲን ብዙ ብር ለኢሽቢ-ኤራ ሰጠው። ኢሽቢ-ኤራ ግን የኢሲን መንግሥት ነጻነት አዋጀ። ኤላማውያን ሲያስቸግሩ ኢሽቢ-ኤራና ኢቢ-ሲን ይዋጋቸው ነበር። በመጨረሻ በ1879 ዓክልበ. ግድም ኤላማውያን በንጉሣቸው ኪንዳቱ ሥር ዑርን አጠፉ። በሚከተለው ዓመት አሞራዊው እሽቢ-ኤራ ኤላማውያንን ከዑር አስወጣቸውና የሱመርና አካድ ላዕላይነት ያዘ።

ቀዳሚው
ሹ-ሲን
ሱመር ነጉሥ
1901-1879 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኢሽቢ-ኤራ
  1. ^ የኢቢ-ሲን ዓመት ስሞች