ኪንዳቱ

ከውክፔዲያ

ኪንዳቱ ከ1901 እስከ 1878 ዓክልበ. አካባቢ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) የኤላም ስሜናዊ ጐረቤት አገር ሲማሽኪ ንጉሥና በኤላም የሲማሽኪ ሥርወ መንግሥት ስድስተኛው ንጉሥ ነበር።

የርሱን እና የሲማሽኪን ነገሥታት ታን-ሩሁራተር፣ ኢዳዱና ኢማዙ ሕልውና የሚያረጋግጡ ሰነዶች ከዑር-፫ አሉ። መጨረሻ ሁለቱ የኪንዳቱ ልጆች ተባሉ።[1]

በኪንዳቱ ዘመን ሲማሽኪ ለታላቁ የዑር-፫ መንግሥት ተገዥ ነበር።[2] ከኤላም ክፍሎች ለምሳሌ የሱሳን ሸለቆ በቀጥታ ከሱመራውያን ግዛት በታች ቆሙ። በ1879 ዓክልበ. ግን ኪንዳቱ የኤላማውያንና የሲማሽኪን ኃያላት ለማዋሀድ የዑርንም ንጉሥ ኢቢ-ሲን በጭራሽ ለማሸንፍ ቻለ። ኢቢ-ሲን እንደ እስረኛ ወደ አንሻን ተጎትቶ ከታሪኩ ጠፋ። ዑር ተፈረሰ።

በኪንዳቱና በኢሽቢ-ኤራ አሞራውያን መካከል የነበረው መተባበር በመጀመርያ ምናልባት በጋራ ጠላት በዑር-፫ መንግሥት ላይ ቢሆንም፣ ለእሽቢ-ኤራ ለኢሲን መጀመርያው ሥርወ መንግሥት መሥራች ክብር በኋላ የተጻፈ አንድ መዝሙር ኪንዳቱን ከመስጴጦምያ እንዳባረረው ይጠቅሳል። የኤላማውያን-ሲማሽኪ አስተዳደር እንግዲህ ለአጭር ጊዜ ነበር።

ልጁ ኢዳዱ እንደ ተከተለው ይሆናል።

  1. ^ Arsacids and Sassanians. M.Rahim Shayegan 2011 ISBN 978-0-521-76641-8
  2. ^ The Oxford handbook of Iranian history. Touraj Daryaee. ISBN 978-0-19-973215-9