ኤላጋባሉስ

ከውክፔዲያ
ኤላጋባሉስ፣ የሶርያ በረቅ ያለበት ሠረጋላ በመሐለቅ ተቀርጾ

ኤላጋባሉስ (195 - 214 ዓም) ከ210 እስከ 214 ዓም ድረስ የሮሜ መንግሥት ቄሣር (አውግስጦስ) ነበር። በገሐድ ቡሽቲ የነበረ ቄሣር ሲሆን ከእርሱ በኋላ ከ214 እስከ 2001 ዓም ድረስ በገሐድ ቡሽቲ የሆነ መሪ አልተገኘም።

209 ዓም የቆየው ቄሣር ካራካላ ተገደለ፣ አለቃው ማክሪኑስ ቄሣር ሆነ። የካራካላ አክስት ዩሊያ ማይሳ ግን ወደ ሶርያ ተስድዳ ይህን መንፈቅለ መንግሥት እጅግ ተቃውማ የልጅዋን ልጅ ኤላጋባሉስ ቄሣር እንዲሆን አመጽ አስነሣች። ብዙ ሥራዊቶች ከማክሪኑስ ወደ ኤላጋባሉስ ስለ ዞሩ የማክሪኑስ ስራዊት በ210 ዓም ተሸነፈና ያንጊዜ ኤላጋባሉስ እድሜው 14 ዓመታት ሲሆን የሮሜ መንግሥት ቄሣር ሆነ።

በኤላጋባሉስ እምነት፣ እርሱ የፀሐይ ጣኦት ቄስና ትስብዕት ነበረ። ከሰማይ የተወረወረ አንድ ጥቁር በረቅ ከሶርያ ወደ ሮም አምጥቶ በሠረገላ ላይ እንደ ፀሐይ አምላክ አድርጎት በመንገዶች ይሠልፍ ነበር።

በታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ኤላጋባሉስ ቡሽቲ ሸርሙጣ ስለ ሆነ፣ የቤተ መንግሥቱን ግቢ እንደ ወንድ ሸርሙጣ ቤት አደረገው፣ ቄሣሩ እራሱ ተቀምጦ ለደንበኞች ይጮህ ነበር። በእርሱ አጸያፊ አግባብ ግን፣ አምላክ ስለ ሆነ እርሱ ከነዚህ «ደንበኞች» ክፍያውንም ሊቀበል ተገባ መሰለው። ከዚህ በላይ ለኤላጋባሉስ የሴት እቃ የሚሰጥ ሀኪም ቢኖር ኤላጋባሉስ ብዙ ሀብት ያቀርበው ነበር ተባለ።

ስለዚህ እና ስለ ብዙ ተመሳሳይ ወሬዎች የሕዝብና በተለይ የሥራዊት ስሜት ከተማኝነት ይዞር ጀመር። ይህን አይታ የኤላጋባሉስ አያት ዩሊያ ማይሳ ሌላ የልጇን ልጅ ሰቬሩስ አሌክሳንደር መርጣ እርሱ የኤላጋባሉስ ወራሽ እንዲሆን አደረገች። ኤላጋባሉስ ይህን ስላልወደደ ሰቬሩስ እንዲታሥር አደረገ፣ ታሞ ሊሞት ነው ሲል አባበለ። ከዚያ ሁከት በሮሜ ወታደሮች ተነሣ፤ ሰቬሩስ እንዲታይ ጠየቁ። ኤላጋባሉስ ሰቬሩስን አሳያቸው። ሥራዊቱ ለሰቬሩስ ሆታ አነሡ፣ ለኤላጋባሉስ ግን ቸል አሉ። ኤላጋባሉስ ተናድዶ ሆታ ያነሡት ግለሠቦች እንዲገደሉ አዘዘ። ወዲያው ሥራዊቱ በጦር ጥቃት በቄሣሩ ላይ ጣሉና ቢሸሽም አገኝተውት ገደሉት። 18 ዓመታት ነበሩት። ሰቬሩስም አዲሱ ቄሣር ሆነ።

ከዚህ በኋላ እስከ 2001 ዓም ድረስ በገሃድ ቡሽቲ የሆነ መሪ ባይኖርም፣ ሰዶማዊነታቸው በሰፊ የታወቀባቸው እንጂ በገሐድ ያላወሩት መሪዎች ኑረዋል፤ ለምሳሌ የቡልጋሪያ ንጉሥ ከ1901-1911 ዓም ፩ ፈርዲናንድ፣ የፕሩሲያ ንጉሥ ከ1732-1778 ዓም ፪ ፍሬደሪክ፣ የኢንግላንድ ንጉሥ ከ1299-1319 ዓም ፪ ኤድዋርድ ጥቂት ናቸው።