ኤሌክትሪክ ምህንድስና

ከውክፔዲያ

ኤሌክትሪካል ምህንድስናኤሌክትሪካል ኤንጂነሪንግ በመባል የሚታወቀዉ የምህንድስና ክፍል ስለ ኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ ኤልክትሮ-መግነጢዝምነት የሚያወሳ የትምህርት የትግበራ ዘርፍ ነው። ይህ የምህንድስና ክፍል ተለይቶ የተጠራዉ እንደ ቴሌግራፍ ስልክ እና የኤልክትሪክ ኀይል ጥቅም ተገኝቶ ትግበር ላይ ከዋለ በኋላ ነዉ፤ ወደ ታሪኩ ስንመጣ ኤሌክትሪሲቲ ኮረንቲነት በሳይንሳዊ አስተሳሰብ መታሰብ ምንአልባትም ዊሊያም ጊልበርት ስታቲካሊ ቻርጅድ(የማይለዋወጥ የሀይል ሙል) የሆኑ ቁሶች የሚለይ መሳሪያ በመፈልሰፉ ነው። ከ1830ዎቹ ጀምሮ የቴሌግራፍ ጥቅም ላይ መዋል ሙከራ ተደርጎም መሳካት ዐለምን ወደ ፈጣን ግኑኝነት እንዳስገባዉ ይታመናል።

የሚከተሉትን በዘርፉ ልብ ይሏቸዋል፣ ባትሪ (የኀይል ሙል)፤ የኀይል ፍሰት ጥርቅም እና ማስተላለፊያው፤ ኤሌክትሮ መግነጢዝም፤ ተለዋዋጭ የማይለዋወጥ የኀይል ፍሰት፤ ትራንስፎርመርሞተርራዲዮ፤ መስመር አልባ ግንኙነት፤ ሞገድ፤ የጨረር ቱቦዎች፤ ቴሌቪዥንቫኪዉም ቱቦዎች፤ ትራንዚስተሮች፤ የተቀናጁ ሽቦዎች፤ ፕሮሰሰሮች፤ አስተላላፊዎች ተቀባዮች፤ መንሰላስል(ኮምፒውተር)… የኀይል ምህንድስና Power Engineering፤ የመቆጣጠር ምህንድስና Control Engineering፤ ኤሌክትሮኒክስ Electronics፤ የመረጃ ትንተና Signal Processing፤ የግንኙነት ምህንድስና (Tele) Communication Engineering ፤ የመሳሪያዎች ምህንድና Instrumentation Engineering ፤ የመንሰላስል ምህንድስና Computer Engineering፤ እንዲሁም ኤሌክትሮ መካኒክስስነህይወት Mechanotronics, Biomedics,…

ከዘርፉ ተያያዥነት ካላቸዉ ታዋቂ ሊቆች መካከልም ዊሊያም ጊልበርት፣ ቮልታፋራዳይኦህምማክስዌልኤዲሰንስታንሌይቴስላስቴይንሜትዝዶቦሎቮሎስኪይሀርትዝማርኮኒፍሌሚንግሾክሌይ፡ ይጠቀሳሉ።

በዘርፉ የታወቁ ባለሙያዎች

ደግሞ ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]