ኤቂውረውስ
Appearance
ኤቂውረውስ (ግሪክ፦ Ἐχυρεύς) በሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአፒያ (በኋላ ሲክዮን) ንጉሥ ነበር።
ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች ኤቂውረውስ 55 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ።[1][2] ከማራጦስ በኋላ እና ከተከታዩ ኮራክስ በፊት ገዛ።
በፓውሳኒዩስ ጽሑፍ ግን ከኦርጦፖሊስ ቀጥሎ ያለው ቅድም-ተከተል ከሌሎች ምንጮች ይለያያል፤ በማራጦኒዮስ፣ ማራጦስና ኤቂውረውስ ፋንታ አንድ ንጉሥ ኮሮኖስ ብቻ ይጠቀሳል።
በጀሮም ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በዚሁ ዘመን ዳናውስ ከግብጽ ወጥቶ ስጠነላዎስን ከአርጎስ አባረረውና አርጎስን ገዛ።
ቀዳሚው ማራጦስ |
የአፒያ ንጉሥ | ተከታይ ኮራክስ |