ኦሳጉ

ከውክፔዲያ

ኦሳጉ (ኮሪይኛ፦ 오사구) ወይም ኦሳኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዳንጉን» ነበር። እርሱ ከአባቱ ዳንጉን ካርግ መንግሥት ቀጥሎ ገዛ።

በጠቅላላ ለ፴፰ ዓመታት (ምናልባት 1919-1881 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ሚኒስትሩ ጉዕል ተከተለው።

ኋንዳን ጎጊ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ኦሳጉ ካደረጋቸው ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንዲህ ናቸው፦

  • በ1919 ዓክልበ. ግድም ዳንጉን ካርግ ዓረፈ፤ አልጋ ወራሹም ኦሳጉ ወደ ዙፋኑ ተከተለው።
  • በ1918 ዓክልበ. ግድም ኦሳጉ ወንድሙን «ኦሳዳል» የ«ሞልጎሊ» ንጉሥ ሆኖ ሾመው፤ ይህ የሞንጎላውያን ወላጅ ይባላል። በተጨማሪ በዚህ ዓመት ኦሳጉ የሕክምና ዕፅ ጊንሰንግቴቤክ ተራሮች አገኘ።
  • በ1914 ዓክልበ. ግድም ቅርጹ እንደ ዛጎል አሣ ቀዳዳ ያለበት መሐልቅ (ሳንቲም) ተመሠረተ። በተጨማሪ በዚህ ዓመት አንድ ተልእኮ ከሥያ ስርወ መንግሥት (ቻይና) ለግቢው ደርሶ አዳዲስ መጻሕፍት አቀረበ። በዚህ ጊዜ የዋና ከተማ ክልል ወሰን ደግሞ በድንጋይ ጽሑፍ ተመለከተ።
  • በ1912 ዓክልበ. ግድም የመርከብ መሥራት ሠፈር በላይኛ ሳልሱ ወንዝ (አሁን በቻይና ያለው ሏን ወንዝ) ተመሠረተ።
  • በ1900 ዓክልበ. ግድም «የሥያ የንጉሥ ሥያንግ መንግሥት ሞገስ ከሕዝቡ ዘንድ ጠፍቶ ዳንጉን (ኦሳጉ) አለቃውን ሺክዳል ከነሦስት ሠራዊት አገሩ እንዲያስገዛለት አዘዘው» ሲል በዚህ ዘመን የሥያንግ ልጅ ሻውካንግ እንደ ነገሠ ይመስላል።
  • በ1881 ዓክልበ. ግድም ዳንጉን ኦሳጉ ዓረፈ፤ ሚኒስትሩም ጉዕል ተከተለው
ቀዳሚው
ካርግ
ጆሰን ዳንጉን
1919-1881 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ጉዕል

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]