ከባቢ አየር

ከውክፔዲያ
ሰማያዊ ቀለም ከሌሎች ቀለማት የበለጠ በከባቢ አየር ተውጦ ይቀራል። ለዚህም ነው መሬትኅዋ ስትታይ የሰማያዊ ቀለም የሚኖራት

የመሬት ከባቢ አየርመሬት ዙሪያ የሚገኝ የጋዝ ክምችት ሲሆን እውን የሆነውም በመሬት ስበት የተነሳ ነው። ይህ የጋዝ ክምችት በተለያዩ ግዜያት የተለያዩ ይዘቶች ነበሩት። በውስጡ የሚገኙት ህይወት ላላችው ነገሮች አስፈላጊ የሆኑ ነገርችም (የኦዞን ንጣፍን ጨምሮ) በየግዜው ተለዋውዋል። ከባቢ አየራችን በውስጡ 78 በመቶ ናይትሮጅን፣ 21 በመቶ ኦክስጅን፣ 0.93 በመቶ አርገን፣ 0.038 በመቶ ካርቦን ዳይኦክሳይድ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን (ጋዞችን) በውስጡ ይዟል። አሁን ያለው ሁኔታ መሬት ለተጨማሪ 1.5 ቢሊዮን አመታት ህይወት ያላቸው ነገሮች እንዲኖሩባት ያስችላል ተብሎ ይታመናል።