ኪርጊዝኛ

ከውክፔዲያ
ኪርጊዝኛ የሚነገሩባቸው ሥፍራዎች

ኪርጊዝኛ (кыргызча /ቂውርሕዊውስቻ/) በኪርጊዝስታንና በጎረቤት አገሮች በተለይም በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ በ4.3 ሚሊዮን ያሕል ተናጋሪዎች የሚነገር የቱርኪክ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። በኪርጊዝስታን እስከ 1920 ዓም ድረስ በአረብኛ ጽሕፈት (በፋርስኛ አልፋቤት) ይጻፍ ነበር፤ ከ1920 እስከ 1932 ዓም ድረስ በላቲን ጽሕፈት (የአንድ አይነት ቱርኪክ አልፋቤት) ተጻፈ፣ ከ1932 ዓም እስካሁን በቂርሎስ ጽሕፈት (የኪርጊዝኛ አልፋቤት) ተጽፏል። በቻይና ውስጥ ግን ምንጊዜም እስካሁን በፋርስኛ (በአረባዊ) አልፋቤት ተጽፏል።

Wikipedia
Wikipedia