Jump to content

ኪሮስ ዓለማየሁ

ከውክፔዲያ
(ከኪሮስ አለማየሁ የተዛወረ)
ኪሮስ ዓለማየሁ

ኪሮስ ዓለማየሁ (፲፱፻፵፰ ዓ.ም. ተወለደ[1]) ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ የነበረ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የትግርኛ ሙዚቃ ሥራዎችን በማቅረብ ይታወቃል።

የህይወት ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ኪሮስ ዓለማየሁ በ፲፱፻፵፰ ዓ.ም. በትግራይ ተወለደ። ኪሮስ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በዓፄ ዮሐንስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ፫ ዓመታት በመምህርነት አገልግሏል። ከዚያም ለሙዚቃ ባለው ዝንባሌ በራሱ ግጥም ደራሲነት የትግርኛ ጨዋታዎችን ለሰፊው ሕዝብ በማቅረብ እና በክራር ተጫዋችነቱ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አግኝቷል።[1]

ኪሮስ በ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. በራስ ቲያትር ቤት ተቀጥሮ ከመስራቱ በፊት የትግራይ ክ/ሀገር የኪነት ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ አገልግሏል። ኪሮስ በሀገር ውስጥ ከሚጫወታቸው አዝናኝ የትግርኛ ዘፈኖች በተጨማሪ ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን በውጭ ሀገር ማለትም በሊቢያና በመካከለኛው ምሥራቅ ኢትዮጵያን በመወከል ተዘዋውሮ ሠርቷል።[1]

  1. ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 30". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-18 የተወሰደ.