ካምቦብላስኮን

ከውክፔዲያ
(ከካምቦ ብላስኮን የተዛወረ)

ካምቦብላስኮን (ካምቦ ብላስኮን) በጣልያን አገር አፈ ታሪክ ዘንድ በራዜና (ኤትሩርያ) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዩፒተር» ነበር።

አኒዩስ ደ ቪተርቦ ባሳተመው ጽሑፍ እንደሚለው፣ ካምቦብላስኮን የሞርጌስ ተከታይ ነበር። አባቱ የፊተኛው ንጉሥ አልቴዩስ ልጅ ብላስኮን ሲሆን፣ የሞርጌስ አባት አትላስ ኪቲም በነገሠበት ጊዜ አትላስ ሴት ልጁን ኤሌክትራ ለልዑል ካምቦብላስኮብ በትዳር ሰጥቶ ነበር። ከዚህ በላይ ከሠፈርኞች ጋራ እጮኞቹን ወደ አልፕ ተራሮች እንዲሠፈሩ ላካቸው።

ሞርጌስ አባቱን ተከትሎ ምናልባት የልዑል ካምቦብላስኮን ድርሻ ትክክል እንዳልሆነ አስቦ ካምቦብላስኮንን አልጋ ወራሹን (ኮሪቱስ) አደረገው። ከዚህ ትንሽ በኋላ አልፎ ካምቦብላስኮን የአያቱን የአልቴዩስን መንግሥት ወረሰ።

ካምቦብላስኮን በበኩሉ በ1828 ዓክልበ. ግድም ልጁን ያሲዩስ ያኒጌና «ኮሪቱስ» (አልጋ ወራሽ አደረገው። ይህም ያሲዩስ በሚከተለው ዓመት (1827 ዓክልበ. ግ.) የኬልቲካ ዙፋን ከዘመዱ ከቤሊጊዩስ ወረሰ። በዚህም ወቅት የተራራ ኗሪዎች (የ«አቦሪጌኔስ» ወገን) ንግሥት ሮማ ልጅ ሮማነሦስ ተከተላት።

ካምቦብላስኮን የ«ሞንትብላስኮን» (አሁን ሞንተፊያስኮኔ በጣልያን) እንዲሁም የ«ኮሪቱስ» (አሁን ታርኲኒያ) ከተሞች መሥራች ይባላል። የካምቦብላስኮንና የኤሌክትራ ሦስት ልጆች ያሲዩስ፣ ዳርዳኑስአርሞኒያ ይባላሉ፤ ዳርዳኑስም በመጨረሻ ወንድሙን ያሲዩስን በጦርነት ከገደለው በኋላ ወደ አናቶሊያ ፈልሶ ትሮያን እንደ መሠረተ ይባላል።

ቀዳሚው
ሞርጌስ
የኢታሊያ ንጉሥ (አፈታሪክ)
1837-1804 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ያሲዩስ ያኒጌና