ካሮት ፑሬ
Appearance
- 3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተከተፈ የሲለሪ ግንድ
- 5 የቡና ስኒ (250 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
- 1 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
- 10 መካከለኛ ጭልፋ (1 ኪሎ ግራም) የተከተፈ ካሮት
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተከተፈ ባሮ ሽንኩርት
- 8 የሾርባ ማንኪያ (200 ግራም) የገበታ ቅቤ
- ቡኬጋርኒ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- ግማሽ ሊትር ወተት ወይም ክሬም
- 1 ኪሎ ግራም በትንንሹ የተቆራረጠ ዳቦ
- 3 ሊትር ነጭ የበሬ ወይም የበግ መረቅ (ቢፍ/ላምብ ኋይት ስቶክ)
- ሩብ ሊትር ዘይት
- 1. በወፍራም ብረት ድስት ቅቤውን ማቅለጥና ማሞቅ፤
- 2. ቀይ ሽንኩርት፣ ሲለሪ፣ ካሮትና ባሮ ሽንኩርቱን ጨምሮ በነጩ በደንብ ማብሰልና ዱቄቱን ጨምሮ ማማሰል፤
- 3. የቲማቲም ድልሁን መጨመር፤
- 4. በዝግታ መረቁን እየጨመሩ በማማሰል ጨውና ቁንዶ በርበሬውን ጨምሮ እንዲበስል ማድረግ፤
- 5. ቡኬጋርኒውን ጨምሮ ለአንድ ሰዓት ያህል ማብሰል፤
- 6. ቡኬጋርኒውን አውጥቶ ድስቱን ካወረዱ በኋላ ንፁህ ብረት ድስት ከሥሩ በማድረግ በአትክልት መፍጫ መፍጨት፤
- 7. ድስቱን ለግማሽ ሠዓት ለሰስ ያለ እሳት ላይ አብስሎ ማውረድ፤
- 8. ክሬም ወይም ወተቱን አፍልቶ በትኩሱ መጨመር፤
- 9. ዳቦውን በትንሹ በአራት ማዕዘን ቅርፅ ቆርጦ ዘይቱን አግሎ መጥበስ፤
- 10. ለገበታ ሲፈለግ የተጠበሰውን ዳቦ በላዩ ጨምሮ ማቅረብ፡፡