ወይዘሮ የሺ እመቤት

ከውክፔዲያ

ወይዘሮ የሺመቤትልዑል ራስ መኮንን ባለቤት እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እናት ነበሩ።

የሺመቤት አሊ ጋምጩ ማናቸው? ልዕልት የሺእመቤት እናታቸው ወ/ሮ ወለተጊዮርጊስ  የምሩ  ሲባሉ አባታቸው ደግሞ አሊ ጋምጩ ይባላሉ፡፡ የተወለዱት አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት  ደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ዶሉ በሚባል ቦታ ነው፡፡የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ከ20 አመት በፊት በወረኢሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የታሪክ መምህር ሆኜ በማገለግልበት  ወቅት የአካባቢውን ታሪክ የያዘ አጠር ያለ ታሪካዊ የጥናት ፅሁፍ ለት/ቤቱ አቅርቤ ነበር፡፡  ጥናት ከቀረበባቸው ታሪካዊ የአካባቢው ጉዳዮች አንዱ የልዕልት የሺእመቤት አሊ ጋምጩ ታሪክ ነበር፡፡ የልዕልቷ ቤተሰቦች ማለትም ተወላጆቻቸው በማነጋገር ጥርት ያለ እና ታሪኩን እንደወረደ ለመፃፍ ተሞክሯል፡፡ የልዕልቷ አራተኛ እና አምስተኛ ተወላጆች በአካባቢው በሕይወት ስላሉ የሚያውቁትን እና ከቀደምት ቤተሰቦቻቸው የተነገራቸውን ምንም ሣይሸራረፉ ቃል በቃል ነግረውኛል፡፡ የተወለዱበት ቦታ ሣይቀር በአካል በመገኘት አይቼዋለሁ፡፡ አሁን በምን ደረጃ ላይ እንደለ ባላውቅም  በወቅቱ እጅግ በጣም ትልልቅ እድሜ ጠገብ ዛፎች እና በመፈራረስ ላይ የሚገኝ ቤት እና አጥር ነበረው፡፡ ልዕልት የሺመቤትን የተመለከተ የሰነድ ማስረጃ ማግኘት ግን አልቻልኩም፡፡ ይህ ምናልባትም ልዕልቲቷ አካባቢውን በህፃንነታቸው ስለለቀቁት ይመስለኛል፡፡ ዘውዴ ረታ ተፈሪ መኮንን ረጅሙ የስልጣን ጉዞ በሚባለው መፅሃፋቸው ገፅ 18 ላይ “ወ/ሮ ወለተ ጊዮርጊስ ከወረኢሉ ባላባት ከሼህ ዓሊ የወለዷትን ሴት ልጅ ይዘው ወደ ሸዋ ለመመለስ የቻሉት አፄ ምኒሊክ ከቴዎድሮስ አምልጠው ከተመለሱ ከአንድ አመት በኋላ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ህፃኗ የሺእመቤት የአራት አመት ልጅ ነበረች” ይላሉ፡፡ ይህ የሚያመለክተው ልዕልት የሺመቤት አካባቢው የለቀቁት በህፃንነታቸው ስለነበር ታሪካዊ የሰነድ ማስረጃዎች በአካባቢው አለመገኘቱ ግልፅ ነው፡፡    ልዕልት የሺእመቤት፤ ሃሰን አሊ እና ስናፍቅሽ አሊ የሚባሉ ሁለት ወንድም እና እህት ነበራቸው፡፤ ሆኖም ግን በእናት የሚገናኙ አይመስለኝም፡፡ የስናፍቅሽ እና የሃሰን አሊ ተወላጆች ወረኢሉ እና ጃማ ወረዳ በብዛት ስለሚገኙ የልዕልቷን ታሪክ መፃፍ ለሚፈልጉ ጥሩ አጋጣሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡  በተለይ የስናፍቅሽ አሊ ልጅ የነበሩት እና በኃ/ስላሴ ጊዜ የጃማ ወረዳ (በደቡብ ወሎ የሚገኝ ወረዳ ነው) አስተዳዳሪ የነበሩት ፊታውራሪ ከበደ ባንተአይምጣ የአባቴ የቅርብ ጓደኛ ስለነበሩ ቤታችን እየመጡ

ስለቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ቤተሰብ እና አንዳንድ ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ከአባቴ ጋር የሚያደርጉት ውይይት እና ጭውውት ሁልጊዜ አስታውሰዋለሁ፡፡ የፊታውራሪ ከበደ ልጆች ጋር አብሮ አደጎች ስለሆንን ይሄንን የታሪክ ማስታወሻ ሳዘጋጅ ኑሮዋን ጃማ ወረዳ ያደረገችውን ልጃቸውን ወ/ሮ ተዋበች ከበደን በስልክ አናግሬአት ነበር፡፡ በማዘጋጀው ማስታወሻ ደስተኛ ብትሆንም የልዕልት የሺመቤት አሊ ጋምጩ ታሪክ አስታዋሽ ማጣቱ ግን ቅር እንዳሰኛት አልሸሸገችኝም፡፡ በቅርብ የታተመው እና ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ” በሚለው መጽሃፋቸው ገጽ 241 ላይ “እናቱ ( ቀዳማዊ ሃይለስላሴን) የሺመቤት አሊ ጋምጮ በአባትዋ በኩል የወረሂመኑ ኦሮሞ ናት፡፡ በአዲሱ ግኝት መሰረት ይብረሁልሽ በተባለችው ስልጤ- ጉራጌ እናትዋ `ቂቶ ` ትባል የነበረችው አያትዋ ወ/ሮ ወለተ -ጊዎርጊስ የወሎው ኦሮሞ ነብይ የሸህ ሁሴን ጅብሪል ልጅ ናት፡፡ ይህ ማለት ሼኽ ሁሴን ጅብሪል የአጼ ሀይለስላሴ ቅድመ አያት ናቸው ማለት ነው” በማለት ጽፈዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ የታሪክ ግድፈት ነው፡፡አጼ ኃ/ስላሴ ከሸኽ ሁሴን ጅብሪልም ሆነ ከወረሂመኑ ተወላጆች ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ልዕልት የሺእመቤት አሊን የሚያውቅ እና ስለ እሳቸው አንጀት አርስ ፅሁፍ የተፃፈው በፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ነው፡፡ እኚህ ግለሰብ በልዕልቲቷ ቤት ያደጉ በመሆናቸው ደግነታቸውን፣ ባህሪያቸውን፣ መልካቸውን እና ከዚያም ባሻገር ዘግናኝ አሟሟታቸውንም ሂደት ፅፈውልናል፡፡ ፊታውራሪ ተክለኃዋርያት ተክለማርያም የህይወቴ ታሪክ በሚባለው እና በ1998 ዓ.ም ቤተሰቦቻቸው ባሳተሙት መፅሀፍ ገፅ 32 ላይ ተክለሃዋሪያት ልእልት የሺመቤትን መጀመሪያ ያያዋቸው ቀን የነበረውን ሁኔታ ሲገልፁ ወ/ሮ የሺእመቤት በጣም ወፍራም ብስል ቀይ ናቸው፡፡ ቆንጆ ናቸው፡፡ ሹሩባቸው በትከሻቸው ላይ ተንዘርፍፏል ይላሉ፡፡ በርግጥ ቁንጅናቸውን ለመመስከር የቀዳማዊ ኃ/ስላሴን መልክ ማየት በቂ ይመስለኛል፡፡ የጅማ ኦሮሞም ነበሩ