Jump to content

ወደ ሮማውያን ፱

ከውክፔዲያ
ወደ ሮማውያን ፱
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ወደ ሮማውያን ፰ ቁ. ፲፪ - ፳፪ ፓፒረስ ፳፯
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፱ ሲሆን በ፴፫ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ ስለእግዚአብሔር ስጦታዎች ያነሳል በተለይ የመዳን ስጦታውን እሱን ማለት ጳውሎስን አጥፍቶ ለተከታዮቹ ቢሰጣቸው ምኞቱ እንደሆነ ይገልጻል ፣ (እንደ ሙሴ እንደ ዳዊት) ።

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፱

ጠቃሚ መልዕክቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • ቁጥር ፫
  • ቁጥር ፮
  • ቁጥር ፯
  • ቁጥር ፳፯
  • ቁጥር ፳፰
  • ቁጥር ፴፫

1-2፤ብዙ፡ሐዘን፡የማያቋርጥም፡ጭንቀት፡በልቤ፡አለብኝ፡ስል፡በክርስቶስ፡ኾኜ፡እውነትን፡ እናገራለኹ፤አልዋሽምም፤ኅሊናዬም፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ይመሰክርልኛል። 3፤በሥጋ፡ዘመዶቼ፡ስለኾኑ፡ስለ፡ወንድሞቼ፡ከክርስቶስ፡ተለይቼ፡እኔ፡ራሴ፡የተረገምኹ፡እንድኾን፡እጸልይ፡ ነበርና። 4፤እነርሱ፡እስራኤላውያን፡ናቸውና፥ልጅነትና፡ክብር፡ኪዳንም፡የሕግም፡መሰጠት፡የመቅደስም፡ሥርዐት፡ የተስፋውም፡ቃላት፡ለእነርሱ፡ናቸውና፤ 5፤አባቶችም፡ለእነርሱ፡ናቸውና፤ከነርሱም፡ክርስቶስ፡በሥጋ፡መጣ፥ርሱም፡ከዅሉ፡በላይ፡ኾኖ፡ለዘለዓለም፡ የተባረከ፡አምላክ፡ነው፤አሜን። 6፤ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡የተሻረ፡አይደለም።እነዚህ፡ከእስራኤል፡የሚወለዱ፡ዅሉ፡እስራኤል፡ አይደሉምና፤የአብርሃምም፡ዘር፡ስለ፡ኾኑ፡ዅላቸው፡ልጆች፡አይደሉም፥ 7፤ነገር፡ግን፦በይሥሐቅ፡ዘር፡ይጠራልኻል፡ተባለ። 8፤ይህም፥የተስፋ፡ቃል፡ልጆች፡ዘር፡ኾነው፡ይቈጠራሉ፡እንጂ፡እነዚህ፡የሥጋ፡ልጆች፡የኾኑ፡ የእግዚአብሔር፡ልጆች፡አይደሉም፡ማለት፡ነው። 9፤ይህ፦በዚህ፡ጊዜ፡እመጣለኹ፡ለሳራም፡ልጅ፡ይኾንላታል፡የሚል፡የተስፋ፡ቃል፡ነውና። 10፤ይህ፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ርብቃ፡ደግሞ፡ከአንዱ፡ከአባታችን፡ከይሥሐቅ፡በፀነሰች፡ጊዜ፥

ቁጥር ፲፩ - ፳

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

11፤ልጆቹ፡ገና፡ሳይወለዱ፥በጎ፡ወይም፡ክፉ፡ምንም፡ሳያደርጉ፥ከጠሪው፡እንጂ፡ከሥራ፡ሳይኾን፡በምርጫ፡ የሚኾን፡የእግዚአብሔር፡ዐሳብ፡ይጸና፡ዘንድ፥ 12፤ለርሷ፦ታላቁ፡ለታናሹ፡ይገዛል፡ተባለላት። 13፤ያዕቆብን፡ወደድኹ፡ኤሳውን፡ግን፡ጠላኹ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ነው። 14፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ዐመፃ፡አለ፡ወይ፧አይደለም። 15፤ለሙሴ፦የምምረውን፡ዅሉ፡እምረዋለኹ፡ለምራራለትም፡ዅሉ፡እራራለታለኹ፡ይላልና። 16፤እንግዲህ፡ምሕረት፡ለወደደ፡ወይም፡ለሮጠ፡አይደለም፥ከሚምር፡ከእግዚአብሔር፡ነው፡እንጂ። 17፤መጽሐፍ፡ፈርዖንን፦ኀይሌን፡ባንተ፡አሳይ፡ዘንድ፡ስሜም፡በምድር፡ዅሉ፡ይነገር፡ዘንድ፡ለዚህ፡አስነሣኹኽ፡ይላልና። 18፤እንግዲህ፡የሚወደ፟ውን፡ይምረዋል፥የሚወደ፟ውንም፡እልከኛ፡ያደርገዋል። 19፤እንግዲህ፡ስለ፡ምን፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ይነቅፋል፧ፈቃዱንስ፡የሚቃወም፡ማን፡ነው፧ትለኝ፡ይኾናል። 20፤ነገር፡ግን፥አንተ፡ሰው፡ሆይ፥ለእግዚአብሔር፡የምትመልስ፡ማን፡ነኽ፧ሥራ፡ሠሪውን፦ስለ፡ምን፡ እንዲህ፡አድርገኽ፡ሠራኸኝ፡ይለዋልን፧

ቁጥር ፳፩ - ፴፫

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

21፤ወይም፡ሸክላ፡ሠሪ፡ከአንዱ፡ጭቃ፡ክፍል፡አንዱን፡ዕቃ፡ለክብር፡አንዱንም፡ለውርደት፡ሊሠራ፡በጭቃ፡ ላይ፡ሥልጣን፡የለውምን፧ 22-23፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ቍጣውን፡ሊያሳይ፡ኀይሉንም፡ሊገልጥ፡ወዶ፥አስቀድሞ፡ለክብር፡ ባዘጋጃቸው፡በምሕረት፡ዕቃዎች፡ላይ፡የክብሩን፡ባለጠግነት፡ይገልጥ፡ዘንድ፥ለጥፋት፡የተዘጋጁትን፡የቍጣ፡ ዕቃዎች፡በብዙ፡ትዕግሥት፡ከቻለ፥እንዴት፡ነው፧ 24፤የምሕረቱ፡ዕቃዎችም፡ከአይሁድ፡ብቻ፡አይደሉም፥ነገር፡ግን፥ከአሕዛብ፡ደግሞ፡የጠራን፡እኛ፡ነን። 25፤እንዲሁ፡ደግሞ፡በሆሴዕ።ሕዝቤ፡ያልኾነውን፡ሕዝቤ፡ብዬ፥ያልተወደደችውንም፡የተወደደችው፡ብዬ፡ እጠራለኹ፤ 26፤እናንተ፡ሕዝቤ፡አይደላችኹም፡በተባለላቸውም፡ስፍራ፡በዚያ፡የሕያው፡እግዚአብሔር፡ልጆች፡ተብለው፡ ይጠራሉ፡ይላል። 27-28፤ኢሳይያስም፦የእስራኤል፡ልጆች፡ቍጥር፡ምንም፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡ቢኾን፡ቅሬታው፡ ይድናል፤ጌታ፡ነገሩን፡ፈጽሞና፡ቈርጦ፡በምድር፡ላይ፡ያደርገዋልና፥ብሎ፡ስለ፡እስራኤል፡ይጮኻል። 29፤ኢሳይያስም፡እንደዚሁ፦ጌታ፡ጸባኦት፡ዘር፡ባላስቀረልን፡እንደ፡ሰዶም፡በኾን፟፡ገሞራንም፡በመሰልን፡ነበር፡ ብሎ፡አስቀድሞ፡ተናገረ። 30፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧ጽድቅን፡ያልተከተሉት፡አሕዛብ፡ጽድቅን፡አገኙ፥ርሱ፡ግን፡ከእምነት፡የኾነ፡ ጽድቅ፡ነው፤ 31፤እስራኤል፡ግን፡የጽድቅን፡ሕግ፡እየተከተሉ፡ወደ፡ሕግ፡አልደረሱም። 32-33፤ይህስ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧በሥራ፡እንጂ፡በእምነት፡ጽድቅን፡ስላልተከተሉ፡ነው፤እንሆ፥በጽዮን፡ የእንቅፋት፡ድንጋይና፡የማሰናከያ፡አለት፡አኖራለኹ፡በርሱም፡የሚያምን፡አያፍርም፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ በእንቅፋት፡ድንጋይ፡ተሰናከሉ።