ወደ ሮማውያን ፰

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ወደ ሮማውያን ፰
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ወደ ሮማውያን ፰ ቁ. ፲፪ - ፳፪ ፓፒረስ ፳፯
አጭር መግለጫ
ጸሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ አርእስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፰ ሲሆን በ፴፱ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። የሚያተኩረውም በክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ነው ።

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፰

ጠቃሚ መልዕክቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ቁጥር ፴፩
  • ቁጥር ፴፯
  • ቁጥር ፴፰ - ፴፱

ቁጥር ፩ - ፲[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1፤እንግዲህ፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ላሉት፡አኹን፡ኵነኔ፡የለባቸውም። 2፤በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ያለው፡የሕይወት፡መንፈስ፡ሕግ፡ከኀጢአትና፡ከሞት፡ሕግ፡ሐራነት፡አውጥቶኛልና። 3-4፤ከሥጋ፡የተነሣ፡ስለ፡ደከመ፡ለሕግ፡ያልተቻለውን፥እግዚአብሔር፡የገዛ፡ልጁን፡በኀጢአተኛ፡ሥጋ፡ ምሳሌ፡በኀጢአትም፡ምክንያት፡ልኮ፡አድርጓልና፤እንደ፡መንፈስ፡ፈቃድ፡እንጂ፡እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡ በማንመላለስ፡በእኛ፡የሕግ፡ትእዛዝ፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ኀጢአትን፡በሥጋ፡ኰነነ። 5፤እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡የሚኖሩ፡የሥጋን፡ነገር፡ያስባሉና፥እንደ፡መንፈስ፡ፈቃድ፡የሚኖሩ፡ግን፡የመንፈስን፡ ነገር፡ያስባሉ። 6፤ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡ሞት፡ነውና፥ስለ፡መንፈስ፡ማሰብ፡ግን፡ሕይወትና፡ሰላም፡ነው። 7፤ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ጥል፡ነውና፤ለእግዚአብሔር፡ሕግ፡አይገዛምና፥መገዛትም፡ ተስኖታል፤ 8፤በሥጋ፡ያሉትም፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ሊያሠኙት፡አይችሉም። 9፤እናንተ፡ግን፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በእናንተ፡ዘንድ፡ቢኖር፥በመንፈስ፡እንጂ፡በሥጋ፡ አይደላችኹም።የክርስቶስ፡መንፈስ፡የሌለው፡ከኾነ፡ግን፡ይኸው፡የርሱ፡ወገን፡አይደለም። 10፤ክርስቶስ፡በእናንተ፡ውስጥ፡ቢኾን፡ሰውነታችኹ፡በኀጢአት፡ምክንያት፡የሞተ፡ነው፥መንፈሳችኹ፡ግን፡በጽድቅ፡ምክንያት፡ሕያው፡ነው።

ቁጥር ፲፩ - ፳[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

11፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስን፡ከሙታን፡ያስነሣው፡የርሱ፡መንፈስ፡በእናንተ፡ዘንድ፡ቢኖር፥ክርስቶስ፡ኢየሱስን፡ ከሙታን፡ያስነሣው፡ርሱ፡በእናንተ፡በሚኖረው፡በመንፈሱ፥ለሚሞተው፡ሰውነታችኹ፡ደግሞ፡ሕይወትን፡ይሰጠዋል። 12፤እንግዲህ፥ወንድሞች፡ሆይ፥ዕዳ፡አለብን፥እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡ግን፡እንኖር፡ዘንድ፡ለሥጋ፡አይደለም። 13፤እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡ብትኖሩ፡ትሞቱ፡ዘንድ፡አላችኹና፤በመንፈስ፡ግን፡የሰውነትን፡ሥራ፡ብትገድሉ፡ በሕይወት፡ትኖራላችኹ። 14፤በእግዚአብሔር፡መንፈስ፡የሚመሩ፡ዅሉ፡እነዚህ፡የእግዚአብሔር፡ልጆች፡ናቸውና። 15፤አባ፡አባት፡ብለን፡የምንጮኽበትን፡የልጅነት፡መንፈስ፡ተቀበላችኹ፡እንጂ፡እንደገና፡ለፍርሀት፡የባርነትን፡ መንፈስ፡አልተቀበላችኹምና። 16፤የእግዚአብሔር፡ልጆች፡መኾናችንን፡ያ፡መንፈስ፡ራሱ፡ከመንፈሳችን፡ጋራ፡ይመሰክራል። 17፤ልጆች፡ከኾን፟፡ወራሾች፡ደግሞ፡ነን፤ማለት፡የእግዚአብሔር፡ወራሾች፡ነን፥ዐብረንም፡ደግሞ፡ እንድንከበር፡ዐብረን፡መከራ፡ብንቀበል፡ከክርስቶስ፡ጋራ፡ዐብረን፡ወራሾች፡ነን። 18፤ለእኛም፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ካለው፡ክብር፡ጋራ፡ቢመዛዘን፡የአኹኑ፡ዘመን፡ሥቃይ፡ምንም፡እንዳይደለ፡ ዐስባለኹ። 19፤የፍጥረት፡ናፍቆት፡የእግዚአብሔርን፡ልጆች፡መገለጥ፡ይጠባበቃልና። 20፤ፍጥረት፡ለከንቱነት፡ተገዝቷልና፥በተስፋ፡ስላስገዛው፡ነው፡እንጂ፡በፈቃዱ፡አይደለም፤

ቁጥር ፳፩ - ፴[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

21፤ተስፋውም፡ፍጥረት፡ራሱ፡ደግሞ፡ከጥፋት፡ባርነት፡ነጻነት፡ወጥቶ፡ለእግዚአብሔር፡ልጆች፡ወደሚኾን፡ ክብር፡ነጻነት፡እንዲደርስ፡ነው። 22፤ፍጥረት፡ዅሉ፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ዐብሮ፡በመቃተትና፡በምጥ፡መኖሩን፡እናውቃለንና። 23፤ርሱም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥የመንፈስ፡በኵራት፡ያለን፡ራሳችን፡ደግሞ፡የሰውነታችን፡ቤዛ፡ የኾነውን፡ልጅነት፡እየተጠባበቅን፡ራሳችን፡በውስጣችን፡እንቃትታለን። 24፤በተስፋ፡ድነናልና፤ነገር፡ግን፥ተስፋ፡የሚደረግበቱ፡ነገር፡ቢታይ፡ተስፋ፡አይደለም፤የሚያየውንማ፡ማን፡ ተስፋ፡ያደርገዋል፧ 25፤የማናየውን፡ግን፡ተስፋ፡ብናደርገው፡በትዕግሥት፡እንጠባበቃለን። 26፤እንዲሁም፡ደግሞ፡መንፈስ፡ድካማችንን፡ያግዛል፤እንዴት፡እንድንጸልይ፡እንደሚገ፟ባ፟ን፡አናውቅምና፥ነገር፡ ግን፥መንፈስ፡ራሱ፡በማይነገር፡መቃተት፡ይማልድልናል፤ 27፤ልብንም፡የሚመረምረው፡የመንፈስ፡ዐሳብ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ያውቃል፥እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ስለ፡ ቅዱሳን፡ይማልዳልና። 28፤እግዚአብሔርንም፡ለሚወዱት፡እንደ፡ዐሳቡም፡ለተጠሩት፡ነገር፡ዅሉ፡ለበጎ፡እንዲደረግ፡እናውቃለን። 29፤ልጁ፡በብዙ፡ወንድሞች፡መካከል፡በኵር፡ይኾን፡ዘንድ፥አስቀድሞ፡ያወቃቸው፡የልጁን፡መልክ፡ እንዲመስሉ፡አስቀድሞ፡ደግሞ፡ወስኗልና፤ 30፤አስቀድሞም፡የወሰናቸውን፡እነዚህን፡ደግሞ፡ጠራቸው፤የጠራቸውንም፡እነዚህን፡ደግሞ፡ አጸደቃቸው፤ያጸደቃቸውንም፡እነዚህን፡ደግሞ፡አከበራቸው።

ቁጥር ፴፩ - ፴፱[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

31፤እንግዲህ፡ስለዚህ፡ነገር፡ምን፡እንላለን፧እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡ከኾነ፡ማን፡ይቃወመናል፧ 32፤ለገዛ፡ልጁ፡ያልራራለት፥ነገር፡ግን፥ስለ፡ዅላችን፡አሳልፎ፡የሰጠው፡ያው፡ከርሱ፡ጋራ፡ደግሞ፡ዅሉን፡ ነገር፡እንዲያው፡እንዴት፡አይሰጠንም፧ 33፤እግዚአብሔር፡የመረጣቸውን፡ማን፡ይከሳቸዋል፧የሚያጸድቅ፡እግዚአብሔር፡ነው፥የሚኰንንስ፡ማን፡ነው፧ 34፤የሞተው፥ይልቁንም፡ከሙታን፡የተነሣው፥በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ያለው፥ደግሞ፡ስለ፡እኛ፡የሚከራከረው፡ ክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ነው። 35፤ከክርስቶስ፡ፍቅር፡ማን፡ይለየናል፧መከራ፥ወይስ፡ጭንቀት፥ወይስ፡ስደት፥ወይስ፡ራብ፥ወይስ፡ ራቍትነት፥ወይስ፡ፍርሀት፥ወይስ፡ሰይፍ፡ነውን፧ 36፤ስለ፡አንተ፡ቀኑን፡ዅሉ፡እንገደላለን፥እንደሚታረዱ፡በጎች፡ተቈጠርን፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ነው። 37፤በዚህ፡ዅሉ፡ግን፡በወደደን፡በርሱ፡ከአሸናፊዎች፡እንበልጣለን። 38፤ሞት፡ቢኾን፥ሕይወትም፡ቢኾን፥መላእክትም፡ቢኾኑ፥ግዛትም፡ቢኾን፥ያለውም፡ቢኾን፥የሚመጣውም፡ ቢኾን፥ኀይላትም፡ቢኾኑ፥ 39፤ከፍታም፡ቢኾን፥ዝቅታም፡ቢኾን፥ልዩ፡ፍጥረትም፡ቢኾን፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡በጌታችን፡ካለ፡ከእግዚአብሔር፡ፍቅር፡ሊለየን፡እንዳይችል፡ተረድቻለኹ።