ወደ ሮማውያን ፯

ከውክፔዲያ
ወደ ሮማውያን ፯
በ፶፮ ፶፰ ዓ.ም. ወደ ሮማውያን ፓፒረስ ፵ ወረቀት ላይ የተጻፈ መልዕክት ። ይህም የሚያሳየው ስብርባሪውን ነው
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፯ ሲሆን በ፳፭ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ።

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፯

ቁጥር ፩ - ፲[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1፤ወንድሞች፡ሆይ፥ሕግን፡ለሚያውቁ፡እናገራለኹና፡ሰው፡ባለበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ሕግ፡እንዲገዛው፡ አታውቁምን፧ 2፤ያገባች፡ሴት፡ባሏ፡በሕይወት፡ሲኖር፡ከርሱ፡ጋራ፡በሕግ፡ታስራለችና፤ባሏ፡ቢሞት፡ግን፡ስለ፡ባል፡ ከኾነው፡ሕግ፡ተፈታ፟ለች። 3፤ስለዚህ፥ባሏ፡በሕይወት፡ሳለ፡ለሌላ፡ወንድ፡ብትኾን፥አመንዝራ፡ትባላለች፤ባሏ፡ቢሞት፡ግን፥ከሕጉ፡ ሐራነት፡ወጥታለችና፥ለሌላ፡ወንድ፡ብትኾን፡አመንዝራ፡አይደለችም። 4፤እንዲሁ፥ወንድሞቼ፡ሆይ፥እናንተ፡ደግሞ፡በክርስቶስ፡ሥጋ፡ለሕግ፡ተገድላችዃል፤ለእግዚአብሔር፡ፍሬ፡ እንድናፈራ፥እናንተ፡ለሌላው፥ከሙታን፡ለተነሣው፥ለርሱ፡ትኾኑ፡ዘንድ። 5፤በሥጋ፡ሳለን፡በሕግ፡የሚኾን፡የኀጢአት፡መሻት፡ለሞት፡ፍሬ፡ሊያፈራ፡በብልቶቻችን፡ይሠራ፡ነበርና፤ 6፤አኹን፡ግን፡ለርሱ፡ለታሰርንበት፡ስለ፡ሞትን፥ከሕግ፡ተፈተ፟ናል፥ስለዚህም፡በዐዲሱ፡በመንፈስ፡ኑሮ፡ እንገዛለን፡እንጂ፡በአሮጌው፡በፊደል፡ኑሮ፡አይደለም። 7፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧ሕግ፡ኀጢአት፡ነውን፧አይደለም፤ነገር፡ግን፥በሕግ፡ባይኾን፡ኀጢአትን፡ ባላወቅኹም፡ነበር፤ሕጉ፦አትመኝ፡ባላለ፥ምኞትን፡ባላወቅኹም፡ነበርና። 8፤ኀጢአት፡ግን፡ምክንያት፡አግኝቶ፡ምኞትን፡ዅሉ፡በትእዛዝ፡ሠራብኝ፤ኀጢአት፡ያለሕግ፡ምውት፡ነውና። 9፤እኔም፡ዱሮ፡ያለሕግ፡ሕያው፡ነበርኹ፤ትእዛዝ፡በመጣች፡ጊዜ፡ግን፥ኀጢአት፡ሕያው፡ኾነ፥እኔም፡ ሞትኹ፤ 10፤ለሕይወትም፡የተሰጠችውን፡ትእዛዝ፥ርሷን፡ለሞት፡ኾና፡አገኘዃት፤

ቁጥር ፲፩ - ፳[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

11፤ኀጢአት፡ምክንያት፡አግኝቶ፡በትእዛዝ፡አታ፟ሎ፟ኛልና፥በርሷም፡ገድሎኛል። 12፤ስለዚህ፥ሕጉ፡ቅዱስ፡ነው፥ትእዛዚቱም፡ቅድስትና፡ጻድቅት፣በጎም፡ናት። 13፤እንግዲህ፡በጎ፡የኾነው፡ነገር፡ለእኔ፡ሞት፡ኾነብኝን፧አይደለም፥ነገር፡ግን፥ኀጢአት፡ኾነ፤ኀጢአትም፡ በትእዛዝ፡ምክንያት፡ያለልክ፡ኀጢአተኛ፡ይኾን፡ዘንድ፥ኀጢአትም፡እንዲኾን፡ይገለጥ፡ዘንድ፡በጎ፡በኾነው፡ ነገር፡ለእኔ፡ሞትን፡ይሠራ፡ነበር። 14፤ሕግ፡መንፈሳዊ፡እንደ፡ኾነ፡እናውቃለንና፤እኔ፡ግን፡ከኀጢአት፡በታች፡ልኾን፡የተሸጥኹ፡የሥጋ፡ነኝ። 15፤የማደርገውን፡አላውቅምና፤የምጠላውን፡ያን፡አደርጋለኹና፡ዳሩ፡ግን፡የምወደ፟ውን፡ርሱን፡አላደርገውም። 16፤የማልወደ፟ውን፡ግን፡የማደርግ፡ከኾንኹ፡ሕግ፡መልካም፡እንደ፡ኾነ፡እመሰክራለኹ። 17፤እንደዚህ፡ከኾነ፡ያን፡የማደርገው፡አኹን፡እኔ፡አይደለኹም፥በእኔ፡የሚያድር፡ኀጢአት፡ነው፡እንጂ። 18፤በእኔ፡ማለት፡በሥጋዬ፡በጎ፡ነገር፡እንዳይኖር፡ዐውቃለኹና፤ፈቃድ፡አለኝና፥መልካሙን፡ግን፡ማድረግ፡ የለኝም። 19፤የማልወደ፟ውን፡ክፉን፡ነገር፡አደርጋለኹና፡ዳሩ፡ግን፡የምወደ፟ውን፡በጎውን፡ነገር፡አላደርገውም። 20፤የማልወደ፟ውን፡የማደርግ፡ከኾንኹ፡ግን፡ያን፡የማደርገው፡አኹን፡እኔ፡አይደለኹም፥በእኔ፡የሚኖር፡ ኀጢአት፡ነው፡እንጂ።

ቁጥር ፳፩ - ፳፭[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

21፤እንግዲያስ፡መልካሙን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡ስወድ፡በእኔ፡ክፉ፡እንዲያድርብኝ፡ሕግን፡አገኛለኹ። 22፤በውስጡ፡ሰውነቴ፡በእግዚአብሔር፡ሕግ፡ደስ፡ይለኛልና፥ 23፤ነገር፡ግን፥በብልቶቼ፡ከአእምሮዬ፡ሕግ፡ጋራ፡የሚዋጋውንና፡በብልቶቼ፡ባለ፡በኀጢአት፡ሕግ፡ የሚማርከኝን፡ሌላ፡ሕግ፡አያለኹ። 24፤እኔ፡ምንኛ፡ጐስቋላ፡ሰው፡ነኝ! ለዚህ፡ሞት፡ከተሰጠ፡ሰውነት፡ማን፡ያድነኛል፧ 25፤በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በጌታችን፡ለእግዚአብሔር፡ምስጋና፡ይኹን።እንግዲያስ፡እኔ፡በአእምሮዬ፡ ለእግዚአብሔር፡ሕግ፥በሥጋዬ፡ግን፡ለኀጢአት፡ሕግ፡እገዛለኹ።

ትኩረት የሚገባቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በሮማውያን ፯
ቁጥር ፫ ፣ ፬ ፣ ፳፭ ትኩረት የሚገባቸው መልዕክቶች ናቸው።
ብሉይ ኪዳን እንዲመለከቱ ደሞ
ሮማውያን ፯ ቁ.፯ ወደ ኦሪት ዘጸ.፳ ቁ.፲፯
ኦሪት ዘዳ.፭ ቁ.፳፩ ይወስደናል ።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Bible የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Christianity የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።