ወደ ሮማውያን ፮

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ወደ ሮማውያን ፮
በ፶፮ ፶፰ ዓ.ም. ወደ ሮማውያን ፓፒረስ ፵ ወረቀት ላይ የተጻፈ መልዕክት ። ይህም የሚያሳየው ስብርባሪውን ነው
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶፮ - ፶፰ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፮ ሲሆን በ፳፫ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። መልዕክቱም የሚያስረዳው ፣ ክርስቲያኖች በማመንና በመጠመቅ ለኃጢያት ሙት እደሚሆኑና መሆንም እንዳለባቸው ነው ።

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፮

ቁጥር ፩ - ፲[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧ጸጋ፡እንዲበዛ፡በኀጢአት፡ጸንተን፡እንኑርን፧አይደለም። 2፤ለኀጢአት፡የሞትን፡እኛ፡ወደ፡ፊት፡እንዴት፡አድርገን፡በርሱ፡እንኖራለን፧ 3፤ወይስ፡ከክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ጋራ፡አንድ፡እንኾን፡ዘንድ፡የተጠመቅን፡ዅላችን፡ከሞቱ፡ጋራ፡አንድ፡ እንኾን፡ዘንድ፡እንደ፡ተጠመቅን፡አታውቁምን፧ 4፤እንግዲህ፡ክርስቶስ፡በአብ፡ክብር፡ከሙታን፡እንደ፡ተነሣ፡እንዲሁ፡እኛም፡በዐዲስ፡ሕይወት፡እንድንመላለስ፥ከሞቱ፡ጋራ፡አንድ፡እንኾን፡ዘንድ፡በጥምቀት፡ከርሱ፡ጋራ፡ተቀበርን። 5፤ሞቱንም፡በሚመስል፡ሞት፡ከርሱ፡ጋራ፡ከተባበርን፡ትንሣኤውን፡በሚመስል፡ትንሣኤ፡ደግሞ፡ከርሱ፡ጋራ፡ እንተባበራለን፤ 6፤ከእንግዲህስ፡ወዲያ፡ለኀጢአት፡እንዳንገዛ፡የኀጢአት፡ሥጋ፡ይሻር፡ዘንድ፡አሮጌው፡ሰዋችን፡ከርሱ፡ጋራ፡ እንደ፡ተሰቀለ፡እናውቃለን፤የሞተስ፡ከኀጢአቱ፡ጸድቋልና። 7-8፤ነገር፡ግን፥ከክርስቶስ፡ጋራ፡ከሞትን፡ከርሱ፡ጋራ፡ደግሞ፡በሕይወት፡እንድንኖር፡እናምናለን፤ 9፤ክርስቶስ፡ከሙታን፡ተነሥቶ፡ወደ፡ፊት፡እንዳይሞት፡ሞትም፡ወደ፡ፊት፡እንዳይገዛው፡እናውቃለንና። 10፤መሞትን፡አንድ፡ጊዜ፡ፈጽሞ፡ለኀጢአት፡ሞቷልና፤በሕይወት፡መኖርን፡ግን፡ለእግዚአብሔር፡ይኖራል።

ቁጥር ፲፩ - ፳፫[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

11፤እንዲሁም፡እናንተ፡ደግሞ፡ለኀጢአት፡እንደ፡ሞታችኹ፥ግን፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡በጌታችን፡ኾናችኹ፡ ለእግዚአብሔር፡ሕያዋን፡እንደ፡ኾናችኹ፡ራሳችኹን፡ቈጠሩ። 12፤እንግዲህ፡ለምኞቱ፡እንድትታዘዙ፡በሚሞት፡ሥጋችኹ፡ኀጢአት፡አይንገሥ፤ 13፤ብልቶቻችኹንም፡የዐመፃ፡የጦር፡ዕቃ፡አድርጋችኹ፡ለኀጢአት፡አታቅርቡ፥ነገር፡ግን፥ከሙታን፡ ተለይታችኹ፡በሕይወት፡እንደምትኖሩ፡ራሳችኹን፡ለእግዚአብሔር፡አቅርቡ፥ብልቶቻችኹንም፡የጽድቅ፡የጦር፡ ዕቃ፡አድርጋችኹ፡ለእግዚአብሔር፡አቅርቡ። 14፤ኀጢአት፡አይገዛችኹምና፤ከጸጋ፡በታች፡እንጂ፡ከሕግ፡በታች፡አይደላችኹምና። 15፤እንግዲህ፡ምን፡ይኹን፧ከጸጋ፡በታች፡እንጂ፡ከሕግ፡በታች፡ስላይደለን፡ኀጢአትን፡እንሥራን፧አይደለም። 16፤ለመታዘዝ፡ባሪያዎች፡እንድትኾኑ፡ራሳችኹን፡ለምታቀርቡለት፥ለርሱ፡ለምትታዘዙለት፡ባሪያዎች፡እንደ፡ ኾናችኹ፡አታውቁምን፧ወይም፡ለሞት፡የኀጢአት፡ባሪያዎች፡ወይም፡ለጽድቅ፡የመታዘዝ፡ባሪያዎች፡ናችኹ። 17-18፤ነገር፡ግን፥አስቀድማችኹ፡የኀጢአት፡ባሪያዎች፡ከኾናችኹ፥ለተሰጣችኹለት፡ለትምህርት፡ዐይነት፡ ከልባችኹ፡ስለ፡ታዘዛችኹ፥ከኀጢአትም፡ሐራነት፡ወጥታችኹ፡ለጽድቅ፡ስለ፡ተገዛችኹ፡ለእግዚአብሔር፡ ምስጋና፡ይኹን። 19፤ስለሥጋችኹ፡ድካም፡እንደ፡ሰው፡ልማድ፡እላለኹ፦ብልቶቻችኹ፡ዐመፃ፡ሊያደርጉ፡ለርኩስነትና፡ ለዐመፃ፡ባሪያዎች፡አድርጋችኹ፡እንዳቀረባችኹ፥እንደዚሁ፡ብልቶቻችኹ፡ሊቀደሱ፡ለጽድቅ፡ባሪያዎች፡ አድርጋችኹ፡አኹን፡አቅርቡ። 20፤የኀጢአት፡ባሪያዎች፡ሳላችኹ፡ከጽድቅ፡ነጻ፡ነበራችኹና። 21፤እንግዲህ፡ዛሬ፡ከምታፍሩበት፡ነገር፡ያን፡ጊዜ፡ምን፡ፍሬ፡ነበራችኹ፧የዚህ፡ነገር፡መጨረሻው፡ሞት፡ ነውና። 22፤አኹን፡ግን፡ከኀጢአት፡ሐራነት፡ወጥታችኹ፡ለእግዚአብሔርም፡ተገዝታችኹ፥ልትቀደሱ፡ፍሬ፡ አላችኹ፤መጨረሻውም፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡ነው። 23፤የኀጢአት፡ደመ፡ወዝ፡ሞት፡ነውና፤የእግዚአብሔር፡የጸጋ፡ስጦታ፡ግን፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡በጌታችን፡ የዘለዓለም፡ሕይወት፡ነው።

Commons-logo.svg
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Christianity የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።