ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 16
Appearance
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ እና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ ራስ ተፈሪ መኮንን «ስለ ባሮች አስተዳደርና ነፃነት የቆመ ደንብ» በሚል ርእስ የተጻፈ ባለ አሥር ገጽ መመሪያ አሳተሙ። በአገሪቱም “ባሪያ” እንዳይሸጥ፣ እንዳይገዛ የሚከለክል አዋጅ መጋቢት ፳፪ ቀን ታወጀ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት ንቅንቅ፣ በኮሎኔል የዓለም ዘውዴ የተመራ የአየር ወለድ ሠራዊት በደብረ ዘይት የአየር ኃይል ረብሸኞችን በመምታት በቁጥጥር ስር አዋለ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የባለ ሥልጣናትን አቋም እና ወንጀል የሚያጠና አጣሪ ሸንጎ እንደመሠረቱ አስታወቁ።