Jump to content
ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሚያዝያ 18
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙት ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው አንድ አገር መሠረቱ። ይሄም የተዋሕዶ አገር ከሁለቱም ስም በተውጣጣው አዲሱ ስም ታንዛኒያ ተብሎ ተሰየመ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ከደርግ በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት፣ የፖሊስ አለቆች፤ የቀድሞ ሚኒስትሮችና ባለ ሥልጣናት ታሠሩ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ የቸርኖቢል የኑክሊዬር መብራት ኃይል ማምረቻ ክፉ አደጋ ተከሰተ። የዚህን አደጋ ክስተት የስካንዲናቪያ አገሮች ይፋ እስካደረጉት ድረስ የሶቪዬት ሕብረት ባለ ሥልጣናት ደፋፍነውት ነበር።