ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 28
Appearance
- ፲፱፻፴፬ ዓ.ም. የጃፓን ንጉሠ ነገሥት የባሕር ኃይል የአሜሪካንን የሰላማዊ ውቅያኖስ የባሕር ኃይል እና አብሮ የተሰለፈውን የጦር ኃይል በሃዋይ ደሴቶች ላይ ባለችው ፐርል ሃርበር ‘Pearl Harbour’ በተሰኘችው ወደብ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ አደጋ ጥላባቸው አሜሪካን የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ውስጥ እንድትገባ የገፋፋትን ታሪካዊ ሁኔታ ከሰተች።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. በሮዴዥያ የሽግግር መንግሥትን እንዲያስተዳድሩ የተመረጡት የዊንስተን ቸርችል አማች የነበሩት እንግሊዛዊው ‘ሎርድ ሶምስ’ (Lord Soames) እጩነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. አገራቸውን አይቮሪ ኮስትን ከፈረንሳይ ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በፕሬዚደንትነት የመሩት ፊሊክስ ሁፌ ቧኜ በተወለዱ በ ሰማንያ ስምንት ዓመታቸው አረፉ።