ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 11
Appearance
- ፲፫፻፳፬ ዓ/ም - ቀዳማዊ አጼ አምደ ጽዮን በደቡብ ኢትዮጵያ እስላማዊ ግዛቶችን ለማስገበር ዘመቱ።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለራስ ወልደ ጊዮርጊስአቦዬ ዘውድ ጭነውላቸው ንጉሠ ዘቤጌምድርና ስሜን አድርገው ሾሟቸው።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት የመምህራን አድማ ተደረገ። ከዚህም ጋር አብሮ የአዲስ አበባ ታክሲ ነጅዎች አድማ አደረጉ። የታክሲ ነጅዎቹ አድማ ለስድስት ቀናት ቆየ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥትን መስከረም ፪ ቀን የገለበጠውን፣ የኅብረተ ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር (ደርግ) ለመገርሰስ፣ በቀድሞ አጠራሩ ተጋድሎ ሓርነት ሕዝብ ትግራይ (ተሓሕት"፣ በኋላም ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ተመሠረተ፤ በምዕራባዊ ትግራይ ደደቢት በተባለ ሥፍራም የትጥቅ ትግሉን ጀመረ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ደራስያን አንድነት ማኅበር (ኢደአማ) ስሙን ወደ ኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር (ኢደማ) የለወጠበት ዕለት።