ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥር 30
Appearance
- ፲፰፻፴፬ ዓ/ም - በዘመነ መሣፍንት፣ የራስ አሊ አሉላ ሠራዊት ደብረ ታቦር ላይ ከሰሜኑ ገዥ ደጃዝማች ውቤ ኃይለ ማርያም ሠራዊት ጋር በጦርነት ገጥሞ ድሉ የራስ አሊ ሆነ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - በፍልውሃ አቅራቢያ በዘመናዊ ዕቅድ አዲስ የተሠራው ኢዮቤልዩ (የአሁኑ ብሔራዊ) ቤተ መንግሥት ተመረቀ
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የአፍሪቃ ኢኮኖሚ ኮሚሲዮን ዋና መሥሪያ ቤትና በአዲስ አበባ ከተማ ለሚደረገው ልዩ ልዩ የአፍሪቃ መንግሥታት ጉባኤዎች መሰብሰቢያ፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት የተሠራውን የአፍሪካ አዳራሽ፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፸፭ ዓ/ም - ለባንኮች የስፖርት ክለብ የእግር ኳስ ቡድን እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በመሀል ሜዳ መደብ የሚጫወተው ተሾመ አዳሙ ጌጡ በዚህ ዕለት ተወለደ። ተሾመ ወደ ባንኮች ከመዛወሩ በፊት ለመብራት ኃይል የእግር ኳስ ክለብ ይጫወት ነበር።