ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 23
Appearance
- ፲፱፻፯ ዓ.ም. - በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሩሲያ በኦቶማን ንጉዛት ላይ ጦርነት አወጀች።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ታዋቂው ደራሲ ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ላይ ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. - በኢትዮጵያ፣ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በድንገተኛ ሞት ከአለፉ በኋላ አልጋ ወራሹ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን ተተክተው በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ ጭነው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተባሉ።
- ፲፱፻፶፯ዓ.ም. - የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ፤ በአዲስ አበባ አካባቢ ማሰራጨት ጀመረ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የዓመቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ሽልማት ከ ፵ሺ የኢትዮጵያ ብር ጋር ለብሪታኒያዊው የታሪክ ምሁር፣ ባዝል ዴቪድሶን (Mr. Basil Davidson) ተሰጠ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲሱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) የታወጀውን “ብሔራዊ የሥራ ዘመቻ” እንደምትደግፍ አስታወቀች።
- ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን በየዓመቱ የማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ቀን እንዲከበር የሚያስችለውን ብሔራዊ ሕግ ፈረሙ።
- ፳፻ ዓ.ም. - በሰሜን ሸዋ አስተዳደር፣ በሀገረ-ማርያም ከሰም ወረዳ፣ ኮረማሽ አጥቢያ የሚገኘው የየለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ መልክ ከተገነባ በኋላ ተመርቆ አገልግሎት ላይ ዋለ።