ዓሳ ጥብስ

ከውክፔዲያ

ዓሳ ጥብስ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የምግብ አይነት ሲሆን፣ የሚሰራውም ከዓሳ ነው።

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

800 ግራም ናይል ፐርች
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
4 የቡና ስኒ (200 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
ግማሽ ሊትር ዘይት
2 መካከለኛ ሎሚ

አዘገጃጀት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1. ዓሣውን በደንብ አፅድቶና አራት ቦታ ከፍሎ የሎሚ ጭማቂውን በሁሉም በኩል ማፍሰስ፤
2. ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና የፉርኖ ዱቄቱን ቀላቅሎ ዓሣውን ውስጡ እያገላበጡ መለወስ፤
3. በጋለ ዘይት ዱቄቱን እያራገፉ መጥበስ፣
4. የተጠበሰው ዓሳ ካሮትጐመን፣ የድንች ጥብስና ሎሚ አጅበውት ሊቀርቡ ይችላሉ። ዓሣው ሲጠበስ በርከት ያለ ዘይት ከተጠቀሙ ዓሣውን ጠብሰው ካበቁ በኋላ ዘይቱን አቀዝቅዞ ለሌላ ጊዜ የዓሣ ምግቦች ሲያዘጋጁ መጠቀም ይቻላል፡፡]