ኣብይ ኣህመድ

ከውክፔዲያ
(ከዓብይ ኣህመድ የተዛወረ)
Jump to navigation Jump to search
አብይ አህመድ አሊ
ዶ/ር ዓቢይ ኣህመድ
ዶ/ር ዓቢይ ኣህመድ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር
ቀዳሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር
ከ2007ዓ.ም. እሰከ 2008ዓ.ም.
የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ
ከ2000ዓ.ም. እሰከ 2003ዓ.ም.
የተወለዱት [ጂማ]]፣ ኢትዮጵያ
የፖለቲካ ፓርቲ ኢህአዴግ
ዜግነት ኢትዮጵያ
ሀይማኖት ክርስትያን

ዶ/ር ዓቢይ ኣህመድ አሊ

ዶ/ር ዓቢይ ኣህመድ


የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ከማይክሮሊንክ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ኣግኝተዋል ። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በደቡብ ኣፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ሠርተዋል። በግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ እና በሊደርሺፕ ተቋም ደግሞ የሥራ ኣመራር ሳይንስ አጥንተዋል። እንዲሁም ኣሽላንድ ዩኒቨርሲቲ በንግድ ኣስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እና ደህንነት ጥናት ፒኤችዲ ዲግሪ ኣላቸው።

በመጀመሪያ 40ዎቹ የሚገኙት ዶክተር ዓቢይ ኣህመድ ፖለቲካ የተቀላቀሉት በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው። ከፖለቲካ ተሳትፏቸው በተጨማሪ በወታደራዊ ጉዳዮች ሰፊ ተሳትፎ የነበራቸው ሲሆን የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ አላቸው። በተባበሩት መንግሥታት የስላም ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈጸም ሩዋንዳ ዘምተዋል። ከ2000 ዓ.ም. እሰከ 2003 የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መስራች እና ዳይሬክተር በመሆነ ኣገልግለዋል። ከእዚያም የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር በመሆን ሠርተዋል። ከ2002 ጀምሮ የኦ.ሕ.ዴ.ድ.ODP (ኦሮሞ ሕዝባዊ ደሞክራሲያዊ ድርጅት) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ሲሆን፤ ከ2007 ጀምሮ ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከእዚህ በተጨማሪ ላለፉት ሦስት ዓመታት የኢ.ሕ.ኣ.ዴ.ግ. (የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኣንድነት ዴሞክራሲያዊ ግንባር) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እየሠሩ ይገኛሉ።

የኢ.ሕ.ኣ.ዴ.ግ. ሊቀ-መንበር ሆነው በቅርቡ የተመረጡት ዶክተር ዓቢይ በኣሁኑ ጊዜ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው። ዶ/ር ዓቢይ ኣህመድ ከመጋቢት ፳፬ ቀን ፳፻፲ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው። የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ቀልብ ወደቤተመንግሥት ከመግባታቸው በፊት መግዛት የቻሉት እኚህ መሪ የሚያራምዱት የመደመር ፍልስፍና በብዙ ዜጎች ተወዳጅ ስለኣደረጋቸው ነው።

መደመር

የሚያስለቅስ ሳይሆን አብሮ የምያለቅስ መሪ!

ኣዲስ ኣበባ ሰኔ ፲፮፣ ፳፻፲ ዓ.ም.