ጅማ
Appearance
(ከጂማ የተዛወረ)
ጅማ Jimma | |
የካቶሊክ ሚሲዮን በጅማ ከተማ 1877 እ.ኤ.ኣ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | ኦሮሚያ ክልል |
ዞን | ጅማ ልዩ ዞን |
ጅማ (ኦሮምኛ፦ Jimma) በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙት ከተሞች በስፋት ትልቋ ከተማ ናት። አሁን በኦሮሚያ ክልል የጅማ ዞን መቀመጫ ከተማ ስትሆን በ 7°40′N ላቲትዩድ እና 36°50′E ሎንግቲዩድ ላይ ትገኛለች። የቀድሞው ከፋ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ሆና አገልግላለች።
በ1998 ዓም የብሔራዊ የስታትስቲክ ባለስልጣን ግምታዊ መረጃ መሠረት የ159,009 ሕዝብ መኖሪያ ናት። ከዚህም መካከል 80,897 ወንዶችና 78,112 ሴቶች ናቸው። ሄርበርት ሉዊስ በ1950ዎቹ የምእራብና ደቡብ ኢትዮጵያ አንጋፋ ገበያ ሲል የሚጠራት ጅማ በአንድ የበጋ ገበያ ቀን እስከ ሰላሳ ሺህ ሰው ይገበያይባት እንደነበር ይናገራል።
በጅማ የቀድሞ የጅማ ነግስታት የገነቧቸው አንዳንድ ቅሪቶች እንደ የአባ ጅፋር ቤተ መንግስት ያሉ ዛሬም ይታያሉ። በከተማዋ አንድ ሙዚየም፣ አንድ ዩኒቨርስቲ፣ የተለያዩ ኮሌጅች፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የተለያዩ ገበያ ማዕከሎችና አንድ ኤርፖርት ይገኙባታል።
|