Pages for logged out editors learn more
እዣ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና የጉራጌ ዞን ወረዳ ነው። ስሙ የመጣውም ከሚኖሩበት ሰባትቤት ጉራጌ ብሔሮች የአንዱ ነው፤ እነሱም እዣኛ (ጉራግኛ) ተናጋሪዎች ናቸው።
ከ1999 ዓም በፊት የቀድሞው እዣና ወለኔ ወረዳ ክፍል ነበረ። በእዣ ውስጥ ያለው ዋና ከተማ አገና ነው። ከአገነና በተጨማሪ ሻመነ ቦዠባር አምበለሊ ፍንትየ የመሳሰሉ ገበያዎች አሉ