ወልቂጤ
ወልቂጤ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል |
ዞን | ጉራጌ ዞን |
ከፍታ | 1,026 ሜትር |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 27,775 |
ወልቂጤ በደቡብ ኢትዮጵያ የምትገኝ የንግድ ከተማ ሰትሆን የጉራጌ ዞን ዋና ከተማም ነች። ከተማዋም በአበሽጌ ወረዳ የምትገኝ ሲሆን የከተማዉ አቀማመጥ በ8°17′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°47′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ይገኛል። በኦሮሚያ ክል በሰሜን በኩል ሲዋሰን፣ የደቡብ ክልል መጀመሪያም ነው። ብዙ ብሔረሰቦች በዉስጡ ሲኖሩ፣ በሃይማኖትም እጅግ የተለያዩ ሰዎች አሉበት።
በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው ከሆነ የ 27,775 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 13,691 ወንዶችና 14,084 ሴቶች ይገኙበታል።[1]ወልቂጤ ከአዲስ አበባ በደቡብ ምእራብ በኩልና ከጂማ በደቡብ በኩል ትገኛለች። በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ41,652 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል።[2]
ታሪክ
ከመቶ ሀምሳ በላይ አመቶች ቀድሞ በደብረጽዮን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተክርስትያን እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን መተከል የተነሳ፣ ከተማው እየሰፋ ሄደ። የፊትአውራሪ ዲነግዴ ጉልት ሆኖም የነበረ ነው። በጉራጌ ዞን ዉስጥ ከቡታጅራ ከተማ ጋር ብቸኛው የከተማ አስተዳደር ሆኖ እስከቅርቡ የቆየ ነበር።[3]
ዋናዋና ገጽታዎች
ወልቂጤ በሃይማኖት መመዘኛ፣ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ እስልምና፣ ፕሮቴስታንት፣ አምልኮ ማእከሎች አሏት። ብዙ ምግብቤቶች፣ ሲኖሩ ከብዙ ከተማዎች የተሻለ መስተንግዶ እንዳለ ብዙዎች ይናገራሉ። የአየርላንድ መንግስት ድጋፍ ደግሞ፣ የዞን መቀመጫ እና የህዝብ ቤተመጽሐፍት በዘጠናዎቹ መጨረሻ ገንብቶ የነበረ ቢሆንም፣ መጽሐፍቤቱን የከተማው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በቅርቡ ጠቅልሎት ህዝቡ ቤተመጽሐፍ የሌለው ነው። ከተማው ላይ ከአዲስአበባ ሲገባ፣ የቤተመንግስት ሲገኝ፣ ትላልቅ መሪዎች ከተማዋን ሲጎበኙ ያርፉበት ነበር። አሁን ደ፣ ወታደር እንደሰፈረበት ወይም ከተማው ጸጥታ ላይ ጉዳዮች ሲጭር፣ ወታደር መጥቶ ያርፍበታል እሚባል ነው። የመጠነኛ ትእይንተሜዳ (ስታዲየም) ሲኖር፣ የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ክለብ (ክትፎዎቹ) የቤት ሜዳውም ነው። ክለቡ፣ በ2012 አም. በኢትዮጵያ ዋና ማህበር (ሊግ) ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ ለመሆን በቅቷል።
አየርንብረት
ወደ ቆላማነት ያመዘነ ነው። ከተማው መግቢያ አካበቢ የሬቡ ወንዝ፣ ወጣ ብሎ ደግሞ የሬቡ ወንዝ አለ። የከተማው ቅርጽ በአንዱ አውራጎዳና እሚጓዝ የመንገድ ዳር ከተማ ሲሆን የጥፍሪት (ክሬሰንት) ቅርጽ አለው።[4]
- ^ "ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን". Archived from the original on 2007-08-13. በ2014-06-30 የተወሰደ.
- ^ Butler, Rhett A., 2005 population estimates for cities in Ethiopia
- ^ ግርማ ደሴ ቀለብ፣ የወልቂጤ ከተማ ታሪክ፣ (ወልቂጤ ከተማ፣ የጎሮ (አበሩስ) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ታሪክ መምህር፣ መመረቂያ ዳግ-ምርምር (re-search)
- ^ ዝኒ ከማሁ፦ የታሪክ መምህሩ መመረቂያ ጽሑፍ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
|