Jump to content

እንዳስላሴ

ከውክፔዲያ

ሽረ እንዳሥላሴ የሽረ ምድር ትልቋ ከተማ ስትሆን ከአሁን በፊት የነበረችውን ጥንታዊት የዓዲ ወንፊቶ 1 ከተማ ወራሪው ጣልያን ኢትዮጵያ በወረረበት ወቅት ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ካወደማት በኋላ በማይማፃ በደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሥር በ1930 ዓ/ም የተመሰረተች ከተማ ናት፡፡ ከተማዋ ከጥንታዊው የማይተሮኽሮዃ ማይድራሻ በቅርብ ርቀት ስትሆን የጭልሜዳ፣ወቓር ዱባ፣ጩማይ2፣ዓዲ ፍልሖ ሜዳዎች እንዲሁም የማይዑመት ጎቦ አንጠልጢላ፣እምባ መለኸዅስም ኮረብቶች እንዲሁም የለዃምባ ጊዮርጊስና የቈየፃ ገዳማት ተራራዎችም በግርማ ሞጎስ የሚጠብቋት ውብ ከተማ ናት፡፡  

እንዳስላሴኢትዮጵያትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በምዕራባዊ ዞንና በታህታይ ቆራሮ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ43,967 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 21,333 ወንዶችና 22,634 ሴቶች ይገኙበታል።[1]. የከተማው አቀማመጥ በ13°52′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°44′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።

ከታላቋ ሽረ እንዳሥላሴ ከተማ ሌላ ሑመራ፣ ማይፀብሪ፣ ዓዲ ገብሩ፣ እንዳባጉና፣ ሸራሮ፣ ዓዲጎሹ፣ ሰለኽለኻ፣ ሰመማ፣ ደብረ ከርበ፣ ክሳድ ጋባ፣ ባድመ፣ ዓዲ ዳዕሮ፣ ዓዲ ነብርኢድ፣ ዓዲ ሃገራይ፣ ዓዲ አውዓላ፣ ዓዲ ረመፅ፣ ቆራሪት፣ ከተማ ንጉሥ፣ ኣደባይ፣ ባዕኸር፣ ዳንሻ፣ ማይካድራ፣ ማይ ሓንሰ፣ ጭላ የሚባሉ ከተሞች ሲኖሩ ሌሎች የቀበሌ ትናንሽ ከተሞችም በዙርያዋ አሉ፡፡

ምንጮች www.shiremunicipal.gov.et[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1 = ዓዲ ወንፊቶ ከ14 መ/ክ/ዘመን በፊት ጀምራ ያደገች ከተማ እንደነበረችና በ1790 ዓ/ም በከተማው ያለፈ ጀምስ ብሩስ የሚባል የስኮትላንድ (እንግሊዝ) አገር አሳሽ ደግሞ ከተማው አኵስምን ጨምሮ ከተመለከታቸው ሁሉ የተለቀና የብዙ ከጡጥ የተሰሩ ልብሶች ማምረቻዎች የነበሩት እና በከተማው በጣም የሚያምሩ ጥሩ ህድሞዎችና ሰገነቶች እንደተመለከተ ጽፏል፡፡ BRUCE’S JOURNEY page 235

2 = ጥሪ 10/1889 ዓ/ም በጊዜው የትግራይ ዓድዋ ገዢ በነበሩ የራስ አሉላ ሰራዊትና የሽረ ገዢ የነበሩ ራእሲ ሓጎስ ሰራዊት መካከል ውጊያ የተደረገበትና የራስ አሉላ ታላቅ ወንድማቸው ባሻ ገብረእግዚኣብሔር በራስ ሓጎስ ተማርከው የተገደሉበት እንዲሁም ራስ ሓጎስ ተማርከው ሲገደሉ ድል ለራስ አሉላ ቢሆኑም በመቁሰላው ምክንያት የካቲት 5/1889 ዓ/ም በአኵስም እንዳረፉ Ehrlich በ1996 እ/አ/አቆጣጠር ባሳተመው መጽሓፍ በገጽ 196 ገልፆታል፡፡

  1. ^ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን Archived ኦገስት 13, 2007 at the Wayback Machine, population.pdf