አረካ

ከውክፔዲያ
አረካ
Araka Ambbaa
ከተማ
አገር  ኢትዮጵያ
ክልል ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
ዞን ወላይታ
ወረዳ ቦሎሶ ሶሬ
ከንቲባ ጰጥሮስ ወልደማሪያም
ከፍታ 1,774 ሜ.
አረካ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
አረካ
የአረካ ፡ አቀማመጥ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ

7°04′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°42′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

አረካ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ከተማ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ በወላይታ የሚገኝ ከተማ ነው። ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ይህ ከተማ ኬክሮስ እና ኬንትሮስ 7°4′ሰሜን 37°42′ምስራቅ እና ከባህር ጠለል በላይ 1774 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ከተማው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር ማዕከል ነው። በከተማ ውስጥ ያለው ምቹ ሁኔታዎች ባጭሩ፤ 24 ሰዓታት የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ንጹህ የህዝብ ውሃ፣ ባንኮች፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ የፖስታ አገልግሎት, የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጤና ማዕከል፣ የግል ክሊኒኮች፣ መድኃኒቶች መደብር፣ የሕዝብ ገበያ፣ መንገዶች ዙሪያ ያሉ መብራት፣ የውስጥ እና ከተማ ማቋረጥ አስፋልት እና ጌጠኛ መንገዶች እና ሌሎች አሉት።

የህዝብ ቁጥር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አረካ በደቡብ ብሔረሰቦች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በብዛት ሰው ከሚኖርባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። በ2020 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባደረገው የህዝብ ቁጥር ትንቢያ መሰረት፣ የከተማዋ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛት 80,693 ነው። ከነዚህም 38,880 ሴቶች ሲሆኑ 41,813 የሚሆኑት ደግሞ ወንዶች ናቸው።[1]

ዋቢ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "የአረካ ከተማ የህዝብ ብዛት". Archived from the original on 2022-07-07. በ2022-02-05 የተወሰደ.