ሶዶ (ወረዳ)
Appearance
(ከኪስታኒ የተዛወረ)
ሶዶ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና የጉራጌ ዞን ወረዳ ነው። ስሙ የመጣውም ከሚኖሩበት ጉራጌ ሶዶ ወይም ክስታኔ ብሔር ነው፤ እነሱም የሶዶኛ (ጉራግኛ) ተናጋሪዎች ናቸው።
በሶዶ ውስጥ ያለው ዋና ከተማ ቡዌ ነው። የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መቃብር በመድረከብድ አቦ ገዳም ይገኛል፤ የጢያ ድንጋይ ሐውልቶችም በወረዳው አሉ።