አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ከውክፔዲያ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ፃድቁ ቅዱስ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካደረጉት ታአምር አንዱን የሚያሳይ ከገድላቸው የተገኘ ስዕል ።
አናብስትንና አናምርት የተገዙላቸው
የተወለዱት ታኅሣሥ ፳፱ ፣ የሚከበረው ጥር ፭መጋቢት ፭ ተዝካረ ልደቱ
የትውልድ ቦታ ንኂሳግብፅ
የአባት ስም ስምዖን
የእናት ስም አቅሌሲያ
የሚከበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንኮፕት ቤተክርስቲያን የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ታዋቂ ገዳማቸው ዝቋላ አቦ
አውሬው የአቦዬን እምባ ሲጠጣ ወይም ዐይናቸውን ሲያነቁር
ሥጋዊ ሥርዓተ ቀብራቸው መጋቢት ፭ [1]


ገብረ መንፈስ ቅዱስ (በእንግሊዘኛ ፡Gabra Manfas Qeddus) በልምድ አቦ ፣ ግብፃዊ ሲሆኑ ከዕድሜያቸው ከ፭፻ዎቹ ፫፷፪ቱን በኢትዮጵያ ሲያሳልፉ የዝቋላን ታላቅ ደብር የመሠረቱና ብዙ ታአምር የሠሩ ፃድቅ ቅዱስ ናቸው ።

ንኂሳ በሚባል አገር የሚኖሩ ስምዖንና አቅሌሲያ የተባሉ፣ ልጅ በማጣት ለሠላሳ ዓመታት ያህል ሲያዝኑ ሲኖሩ፣ ሥሉስ ቅዱስ በአቅሌሲያ መኀፀን ሀብተ ፀጋን ቢያሳድሩ በአምላኩ ኃይል አናብስትን የሚገዛ ኃጢያትን ይቅር የሚያስብል ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተወለደ፣ የስሙም ትርጉም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ማለት ነው።

መንፈሳዊ ሥራቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ብፁዕ አባታችን አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በተወለዱ ዕለት ከእናታቸው ጭን ወርደው እግዚአብሔር አመሰገኑ። እናታቸው ሳትታቀፋቸው የእናታቸውን ጡት ከንፈራቸው ሳይነካ በጉሮሯቸው የወተት ጠብታ ሳይወርድ በመንፈስ ቅዱስ ሞግዚትነት ለ፫ ዓመት ከቆዩ በኋላ መላኩ ቅዱስ ገብርኤል በክንፉ ታቅፎ ወስዶ ዘመደ ብርሃን ለሚባል አበ ምነቴ ሰጣቸው፣ በዚያም በኃይለ እግዚአብሔር ከጎለመሱና በመንፈስ ጥበብ ከአደጉ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምቅዱስ ሚካኤልገብርኤል ጋር መጥታ ባረከቻቸው እዲህ ብላ "አራዊት ይገዙልህ"።[2]

ከበቁም በኋላ አባ ተባሉ፣ ቅዱሳን ቦታዎችንም ጎበኙ ቤተልሄምናዝሬትዮርዳኖስን…።

ብዙ ተአምራትም አደረጉ ሰዎችም ዝናቸውን እየሰሙ ከአሉበት ድረስ እየሄዱ ይጎበኙዋቸውና ምረትም ቡራኬም ይቀበሉ ነበር ። ተጋድሎዋቸውን በአውሬው ላይ ግብፅ አገር እያኪያሄዱ እያለ አንድ ቀን ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ጭው ያለውን በረኃ እንዲያዩና ከአናብስትና ከአናምርት ጋር እንዲኖሩ አዘዛቸው፣ በዛም በረኃ እግዚአብሔር በፀጋው በመላ አካላቸው ፀጉር እንዲበቅል ልብስም እንዲሆናቸው አደረገ[3]

ይህን ስጦታ ካገኙ በኋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ክርስትና እንዲሰብኩ የሆነው ።

አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብርሃናዊ ኮከብ በአቅሌስያ ኅዋው የተገኘው ለግብፅና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ሆነ ብርሃናቸው[4]

አቦዬ በኢትዮጵያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያ ደርሰው ከቆዩ በኋላ ዝቋላ ገዳም በአሁኑ ሸዋ ክፍለ ሀገር መሥርተዋል ከዛም ወደ ምድረ ከብድ ተጋድሎዋቸውን ቀጥለው ፣ ብዙ ፈተናም በሳጥናኤል ደርሶባቸዋል እኒህንም በአሸናፊነት ተወጥተዋል ። በአንድ ወቅት ወደ ገነት ተመንጥቀው ሥላሴ ስመው እንደባረኩዋቸው በድርሳናቸው ተጽፎ ይነበባል ።

ከአደረጉት አንዱ ተአምር ፡ በምድረ ከብድ ሦስት ቅዱሳን አባ ሳሙኤል የዋልድባውና አባ አንበስ የሀዘሎ አባ ቢንያም የበጌምድር ከነ አናብስትና አናምርታቸው ሊጎበኙዋቸው መተው አቦዬ በሌሉበት የአቦዬ አናብስትና አናምርት የቅዱሳኖቹን እንሰሳት ዋጡዋቸው ከዛም አቦዬ ደርሰው እንዲተፉዋቸው አዘው አስተፍተው መለሱላቸው በዚህም ተደንቀው እነ አባ ሳሙኤል አከበሩዋቸው ማንነታቸውን አወቁ ።[5] ብፁዕ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓመት ፫ጊዜ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ይጉዋዙ ነበር የተለያዩ ቋንቋም ይናገሩ ነበር ። ሲያርፉም ሰውነታቸውን ክርስቶስ እንደተሰቀለው እጃቸውን በቀኝና በግራ ዘርግተው መሬት ላይ ተኝተው ተገኙ ።

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ እጅግ አስደናቂ የሆነ ታሪካቸው በመጋቢት ፭ በስንክሳር መጽሐፍ የሰማዕታትና ቅዱሳን ታሪክ ውስጥ ይነበባል
  2. ^ መልክዐ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
  3. ^ መልከዐ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
  4. ^ መልከዐ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
  5. ^ ድርሳነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ