አርባ ምንጭ

ከውክፔዲያ

አርባ ምንጭኢትዮጵያደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል ከተማ ሲሆን በጋሞጎፋ ዞን (ቀድሞ ሰሜን ኦሞ ዞን)ና በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ72,507 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 36,296 ወንዶችና 36,211 ሴቶች ይገኙበታል።[1]

በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ68,816 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ6°2′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°33′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።[2]

አርባ ምንጭ እንደ ሌሎች የስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ሞቃታማ ከተማ ናት። ሙቀቷን የሚያስረሳ ልምላሜን እና የተፈጥሮ ቸርንት የታደለች ከተማ ነች። አርባ ምንጭ ከስሟ መረዳት እንደሚቻለው በአንድ አከባቢ የሚፈልቁ ከ40 በላይ ምንጮች አሉ። የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች አሉ።በዋነኛነት የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ መገኛ ከተማ ነች። የአዞ ማርቢያ፣ ጫሞና አብያታ ከከተማዋ በቅርብ ይገኛሉ። የኮንስ፣ የዶርዜ እና የሱርሜ ማኅበረሰቦች ደግሞ የበለጠ የሚማርክ ባህሎችን ለተመልካች ማጋራት ይችላሉ።

ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን Archived ኦገስት 13, 2007 at the Wayback Machine, population.pdf
  2. ^ Butler, Rhett A., 2005 population estimates for cities in Ethiopia