Jump to content

ጉመር

ከውክፔዲያ

ጉመር የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና የጉራጌ ዞን ወረዳ ነው። ስሙ የመጣውም ከሚኖሩበት ሰባትቤት ጉራጌ ብሔሮች የአንዱ ነው፤ እነሱም ጉመርኛ (ጉራግኛ) ተናጋሪዎች ናቸው።

በጉመር ውስጥ ያሉት ከተሞች አረቅጥና ቄቡል ናቸው። አረቅጥ ሐይቅ በወረዳውም አለ። ደብረ ሙጎ ሁለት የ19ኛ ክፍለ ዘመን መስጊዶችና ብዙ የበለስ፣ ወይራ፣ ዝግባ፣ ጥድና ዋንዛ ደን አለበት፤ እንዲሁም ዮ፣ አይሰጪ እና ባልከች የተባሉ ወንዞች መነሻ ነው።