Jump to content

ኃይለማሪያም ደሳለኝ

ከውክፔዲያ


ኃይለማሪያም ደሳለኝ
ኃይለማርያም ደሳለኝ በዓለም የኢኮኖሚ መድረክ፣ 2003 ዓ.ም.
ኃይለማርያም ደሳለኝ በዓለም የኢኮኖሚ መድረክ፣ 2003 ዓ.ም.
፲፪ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር
ከነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ጀምሮ
(ከነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፬ እስከ መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በተጠባባቂ ደረጃ)
ፕሬዝዳንት መ/አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ
ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ
ምክትል አስቴር ማሞ
ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
ደመቀ መኮንን
ቀዳሚ መለስ ዜናዊ
የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር
ከጥር ፲፱ ቀን ፳፻፭ እስከ ጥር ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.
ቀዳሚ ቶማስ ያዪ ቦኒ
ተከታይ ሞሐመድ ኡልድ አብደል አዚዝ
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
ነሐሴ ፳፮ ቀን ፳፻፪ እስከ መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ቀዳሚ አዲሱ ለገሰ
ተከታይ ደመቀ መኮንን
ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
ሙክታር ከድር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ነሐሴ ፳፮ ቀን ፳፻፪ እስከ መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ቀዳሚ ስዩም መስፍን
ተከታይ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ፕሬዝዳንት
ከኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. እስከ የካቲት/መጋቢት ፲፱፻፺፰ ዓ.ም.
ቀዳሚ አባተ ኪሾ
ተከታይ ሽፈራው ሽጉጤ
የፖለቲካ ፓርቲ ደኢህዴንኢህአዴግ
ባለቤት ሮማን ተስፋዬ[1]
ትምህርት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ
ተምፐሬ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
አዙሳ ፓሲፊክ ዩኒቨርስቲ
ሀይማኖት ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ሓዋሪያዊት ቤተክርስቲያን

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝወላይታ አውራጃ በቦሎሶ ወረዳተወለዱ። የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአከባቢያቸው የአየርላንድ ካቶሊክ ሚሺን ባቋቋመው ት/ቤት እንደፈጸሙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወላይታ ሶዶ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፈጽመው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲኢንጂነሪንግ ከተመረቁ በኋላ በአርባምንጭ ውኃ ተቋም አስተማሪ ሆነው እያገለገሉ ሳሉ የማስትሬት ዲግሪያቸውን በፊንላንድ ተምፔ ዩኒቨርስቲ በጽዳት ወይም ሳኒቴሺን አጠናቀው አገር ቤት በመመለስ በአርባምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ዲን ሆነው አገልግለዋል። ከዚያም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በም/ፕሬዚዳንት፣ በፕሬዚዳንትና የኢሕአዴግ ዋና ጸሃፊ ሆነው አገልግለዋል።

ተማሪ በነበሩ ጊዜ የደርግ ደጋፊ የነበሩት አቶ ሃይለማርያም፣ የማስተርስ ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱ የመንግስት ለውጥ ስለነበረ፣ እሳቸውም የአቁዋም ለውጥ አርገው የገዚው መንግስት ደጋፊ መሆን ጀመሩ። የስልጣን ጥማታቸውንም ለማርካት፣ ከፖፑ በላየ ካቶሊክ እንደሞባለው፣ እሳቸውም የዘር ፖለቲካውን ከወያኔ ባለስልጣኖች በላይ ማናቸስ ጀመሩ።

ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ከአከባቢያቸው ከወላይታ ዞን ሲሆኑ በኢኮኖሚክስና በሥራ ሃላፊነት ሁለት የማስተርስ ዲግሪ ምሩቅ ሲሆኑ ባለቤታቸው ወደ አዲስ አበባ እስከመጡበት ድረስ የደቡብ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ቢሮ /የባለቤታቸው/ ልዩ አማካሪና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። ወ/ሮ ሮማን ከሃይስኩል እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድሕረ ምረቃ ድረስ ከባለቤታቸው ጋር አብረዋቸው በከፍተኛ ትምሕርት ዘልቀዋል። ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት መሥርተው በኃላፊነት ከሰሩ በህዋላ ወደ ዩ.ኤን.ዲ.ፒ. ዓለም አቀፍ መሥሪያ ቤት ተዛውረው ሲሰሩ ቆይተው ከህዳር ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የቀዳሚ ወይዘሮ ቢሮ ተረክበዋል። በዚህም ሥራ መስክ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ ና የጎጂ ልማዶችና ባህሎች ማስወገጃ ሰሚናሮች ላይ እየተገኙ ንግግር በማድረግና ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኢሕአዴግ መንግስትና የወላይታ ሕዝብ በቋንቋ ምክንያት በተፈጠረው ውዝግብ ጊዜ የ"ወጋጎዳ" ቋንቋ የወላይታ ልጆች ተገደው እንዲማሩ ጫና አርገዋል ተብለው በሌሎች የአከባቢያቸው ጎሳዎች ዘንድ አለመወደዳቸው ጥቁር ነጥብ በታሪካቸው ጥሎ እንዳለፈ ይነገራል። እንዲሁም በደቡብ ክልል የክልል ምክትል ፕሬዚዳንት በነበሩ ጊዜ በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የበላይ አለቃቸውና የክልሉን ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ አባተ ኪሾን ከስልጣን የሚያስወግድ ደብዳቤ በገዛ እጃቸው የጻፉና በምትካቸው ራሳቸውን ተክተዋል እየተባሉም ይተቻሉ። ይሁን እንጂ በመንግሥት ሚዲያ በኋላ እንደተነገረው አቶ አባተ ኪሾ በሙስና ምክንያት ከስልጣን መወገዳቸው ተዘግቦአል።

በዚህም የተነሳ በጊዜው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መስተዳድር አስተዳደራቸውና እውቅናቸው እይደበዘዘ ስለመጣ የአካከባቢው ተወላጆች በተደጋጋሚ በሚቀሰቅሱት ተቃውሞች ከሥልጣናቸው ተነስተው ወዲያውኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው በታላቁ ቤተመንግሥት አከባቢ ቆይተው በ2003 በ8ኛው የኢሕአዴግ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የቀድሞውን ብሄረ አማር ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ አዲሱ አበበን በመተካት የኢሕአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ለመሆን በቅተዋል። በተጨማሪም የደቡብ ክልላዊ መንግሥት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆናቸው በፓርቲው ታሪክ የመጀመሪያው በትጥቅ ትግል ያልተሳተፉ ከፍተኛ ባለሥልጣን መሆን ብቻ ሳይሆን ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ ያለውን 2ኛውን ትልቅ ቦታ በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመቆናጠጣቸውም በላይ የኢትዮጵያ 24ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል።

ይህም በመሆኑ፡ ከሶስት ትላልቅ ብሄሮች ውጪ ማለትም አማራትግሬኦሮሞ ብሄር አባል ያልሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የደቡብ ተወላጅና ከኦርቶዶክስ እምነትተከታይ ውጪ ፕሮተስታንትየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እ.ኤ.አ ኦገስት 22 /2012 ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ አቶ ኃ/ማሪያም ወደ ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ ከፍ ብለው ለአንድ ወር ያህል ከቆዩ በኋላ የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የፓርቲው ሊቀመንበርና ባለሙሉ ስም ጠ/ሚኒስትር እንዲሆኑ በመመረጣቸው እስከ 2015 ምርጫ ቀጣዩ የኢትዮጵያ መሪ በመሆን በኢትዮጵያ ታሪክ መዝገብ ላይ ስማቸውን አኑረዋል።

የሚከተለው አስረጅ ከአይጋ ፎረም የተወሰደ ነው

የ47 ዓመቱ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በአረካ ከተማ ነው የተወለዱት ። የወጣትነት ዘመናቸውንም በዚህ በተወለዱበት ሰፍራ ያሳለፉ ሲሆን ፥ በ1980 ዓመተ ምህረት የባችለር ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና አግኝተዋል። ገና በወጣትነት ዘመናቸው የያኔውን የአርባምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የዛሬውን አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲን በመምህርነት አገልግለዋል ። በተቋሙ ቆይታቸው ባገኙት ነፃ የትምህርት እድልም ወደ ፊንላንድ በማቅናት ከታምፔሬ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በስነ ንፅህና ምህንድስና የማስተርስ ድግሪያቸውን ተከታትለዋል ። ከተመለሱም በኋላ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዲን በመሆን ለ13 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን ፥ በነዚህ ጊዜያት ውስጥም ከአሜሪካው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በድርጅት አመራር የማስተርስ ድግሪ አግኝተዋል ። አቶ ሀይለማሪያመ ደሳለኝ በ1990ዎቹ መግቢያ ላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ አባል በመሆን በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ጀምረዋል ። የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስትን በምክትል ርእሰ መስተዳደርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሀይለማሪያም በ1998 ለአራት ዓመታት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሆነው ሰርተዋል ። በመቀጠልም አቶ ሀይለማሪያም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን የተንቀሳቀሱ ሲሆን ፥ በምክር ቤቱ የመንግስት ጉዳዮች ተጠሪ ሚኒስትርም ነበሩ ። ከዚህ በተጓዳኝም በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አማካሪም ሆነው የሰሩ ሲሆን ፥ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች ፣ የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ልዩ አማካሪም ሆነው የሰሩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ ።ከ2002 አገር አቀፍ መርጫ በኋላም በድጋሚ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡ ሲሆን ፥ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ካቢኔ ውስጥም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ተሹመው በማገልገል ላይ ይግኛሉ ። በፓርቲያቸው ውስጥ ባላቸው እንቀስቃሴም የኢህአዴግ አባል በሆነው ድርጅታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ንቅናቄ / ደኢህዴን/ ሊቀመንበር በመሆን ከ10 ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ እየሰሩ ይገኛሉ ። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልም ሲሆኑ ፥ ከሁለት ዓመት በፊት የድርጅቱ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ምክትል ሊቀመንበር ሆነውም ተመርጠዋል ። ከወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር ትዳር መስርተውና ሶሳት ልጆች አፈርተው እየኖሩ የሚገኙት አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ዛሬ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። በፓርቲው አሰራርም መሰረት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለግላሉ።

ማመዛገቢያዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ (እንግሊዝኛ) "Hailemariam Desalegn's Biography". Durame News Online. 22 August 2012. http://www.durame.com/2012/09/biography-of-haile-mariam-desalegne.html በ2012-08-2012 የተቃኘ.