ዓክልበ.
Appearance
ዓክልበ. (ዓመቶች ከክርስቶስ ልደት በፊት) ወይም ክ.በ. (ከክርስቶስ በፊት) ወይም ቅ.ል.ክ. (ግዕዝ፣ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ማለት ከ1ኛው ዓመተ ምሕረት (ዓ.ም.) አስቀድሞ የነበሩት ዓመቶች የመቆጠሪያ ዘዴ ነው።
1 ዓ.ም. የዓመተ ምህረት መጀመርያ ዓመት እንዲሆን የወሰነው መኖኩሴ አኒያኖስ እስክንድራዊ ተባለ። የፈረንጅ አቆጣጠር ግን የአኒያኖስን ሳይሆን የሌላውን መነኮሴ የዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ቁጠራ በመከተሉ፣ ዓመቱ 1 እ.ኤ.አ. ከዚያው 8 ዓመታት በፊት (ወይም በ8 ዓክልበ.) ይጀመራል። የአሁኑ መምህራን ደግሞ ኢየሱስ የተወለደበት ዓመት 12 ዓክልበ. ግድም እንደ ሆነ የሚል ግምት አላቸው።
በዚሁ አቆጣጠር ዘዴ ዓመቶቹ ወደፊት እየሄዱ ቁጥራቸው ይቀነሳል። ስለዚህ 3000 ዓክልበ. ከ2000 ዓክልበ. በፊት ሆነ፣ ይህም ከ1000 ዓክልበ. በፊት ነበር።
አንዳንዴ ይህ የመቆጠር ዘዴ በስሕተት «ዓ.ዓ.» (ዓመተ ዓለም) ይባላል። በትክክል ዓመተ ዓለም (ሮማይስጥ፦ Anno Mundi) ግን ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ የሚቆጠር ዘዴ ስለሆነ፣ ዓመቶቹ ወደፊት እየሄዱ ቁጥራቸው ይበዛል። 1000 ዓ.ዓ. ከ2000 ዓ.ዓ. በፊት፣ 2000 ዓ.ዓ. ከ3000 ዓ.ዓ. በፊት ደረሰ ማለት ነው።
ደግሞ ይዩ