ዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን

ከውክፔዲያ
«ይህ ገጽ ከእንግሊዝኛው በቀጥታ የተቀዳ ነው። ቀስ በቀስ ይተረጎማል በማለት ነው።»


ዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንቤጂንግ ቻይና1909 ዓ.ም. የተመሠረተ ነፃ ቤተ ክርስቲያን ነው። በ6 አህጉር ላይ 1.5 ሚሊዮን የሚያሕሉ ምዕመናን አሉት። ቤተ ክርስቲያኑ በቻይና የወጣ ከጰንጤ እንቅስቃሴ የተነሣ ነው።

ይህ ቤተ ክርስቲያን ግን የሥላሴ ጽንሰ ሐሳብ አይቀበልምና «የኢየሱስ ስም ትምሀርት» ተከታዮች ናቸው።

አምስቱ ዋና ትምህርቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን 5 አይነተኛ ትምሀርቶች እንደሚከተል ናቸው፦

መንፈስ ቅዱስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«መንግሥተ ሰማያትን የመውረሳችን ዋስትና መንፈስ ቅዱስ በመቀበል ነውና እሱም ባልታወቀ ልሳናት በመናገር ይገለጻል።» መንግስተ ሰማያት የመውረሳችህን ዋና ነገር ገታ እየሱስ እንደግል አዳናችን በመቀበል ነው

ጥምቀት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«የውሃ ጥምቀትኃጥአት ስርየት ለተሐድሶ የሆነው ቁርባን ነው። ጥምቀቱ መደረግ ያለበት በተፈጥሮ ኗሪ ውኃ ለምሳሌ እንደ ወንዝ፣ ባሕር ወይም ምንጭ ውስጥ እንዲሆን ያስፈልጋል።

ከዚህ ቀድሞ የውኃ ጥምቀትመንፈስ ቅዱስ የተቀበለው መጥምቅ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያጠምቀዋል። ተጠቃሚውም ራሱን አጎንብሶ ወደ ታች ሲመለከት በውኃ በሙሉ እንዲታጠብ ነው።»

እግር ማጠብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«የግሮች ማጠብ ምስጢር ሰው ከጌታ ኢየሱስ ጋር ድርሻ እንዲኖረው ያስችለዋል። ደግሞ ፍቅር፣ ቅድስና፣ ትሕትና፣ ይቅርታ እና አገልግሎት እንደሚያስፈልጉት እንደ ዘወትር ማስታሰቢያ ያገለግላል።

የውኃ ጥምቀት የተቀበለ ሰው ሁሉ እግሮቹን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲታጠብ አለበት። በሚገባበት ጊዜ እርስ በርስ መታጣጠብ ሊሠራ ይችላል።»

ቅዱስ ቁርባን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«ቅዱስ ቁርባን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ መሞት የሚያከብረው ምስጢር ነው።

ዘላለማዊ ሕይወት እናገኝ ዘንድ በመጨረሻም ቀኝ እንነሣ ዘንድ፣ ከጌታችን ሥጋ ወደም ለማሳተፍ ከሱም ጋር ለመቈረብ ያስችለናል። ይኸው ቁርባን እስከሚቻል ድረስ ብዙ ጊዜ ይደረጋል። አንድ ቂጣ እና የወይን ጭማቂ ብቻ ይጠቀማል።»

የሰንበት ቀን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«የሰንበት ቀን፥ የሣምንቱ ሰባተኛ ቀን (ቅዳሜ) በእግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሠ ቅዱስ ቀን ነው። የእግዚአብሄርን ፍጥረትና መድኃኒት ለማስታወስና በሚመጣው ሕይወት የዘላለማዊ ዕረፍት ተስፋ ከማድረግ ጋራ በጌታ ጸጋ መሠረት ይከብራል።»

ተጨማሪ ትምህርቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በኋላ በ1980ዎቹ የዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን 10 መሠረታዊ እምነቶች ለመሆን በነዚህ 5 ዋና ትምህርቶች ላይ ሌሎች ተጨመሩ፦

ኢየሱስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ሥጋ ሆኖ በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአተኞች ቤዛነት የሞተው፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን የተነሣውና ወደ ሰማያት ያረገው ነው፤ እርሱ የሰው ልጆች ብቸኛ አዳኝና የሰማይና የምድር ፈጣሪ እንዲሁም እውነተኛ አምላክ ነው።

«እየሱስ ክርስቶስ፣ ስጋ የሆነው ቃል፣ ሀጥያተኞችን ለማዳን በመስቀሉ ላይ ሞተ፣ በሶስተኛው ቀንም ተነሳ እና ወደ ሰማይ አረገ። የሰው ልጅ አዳኝ፣ የዚች ዓለምና የሰማይ ፈጣሪ፣ አንዱና ብቸኛው አምላክ እሱ ብቻ ነው።».

መጽሐፍ ቅዱስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«መጽሀፍ ቅዱስ፣ አዲሱና ያለፈውን ኪዳን ይዞ፣ በእግዚአብሄር ነው የተናሳሳው፣ ብቸኛው የተጻፈ እውነት ነው፣ የክሪስቲያን አኗኗር ደንብ ነው።».


ደኀንነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«ደኀንነት በእግዚአብሔር ጸጋ በእምነት ይሰጣል። ቅድስናን ለመከተል፣ እግዚአብሔርን ለማክበርና ሰዎችን ለመውደድ፤ አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ላይ መታመን አለባቸው።»

እውነተኛ ቤተክርስቲያን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«በ'ኋለኛ ዝናብ' ጊዜ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተው እውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የሃዋርያዊ ዘመን የታደሰ እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ነው።»

ዳግመኛ ምጣት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«የጌታው ዳግመኛ ምጽአት የሚደርሰው ዓለምን እንዲፈርድ ከሰማይ በወረደበት በመጨረሻ ቀን ነው። በዚያን ጊዜ ጻድቃን የዘላለምን ሕይወት ይቀበላሉ፤ ክፉዎችም ለዘላለም ይኮነናሉ።»