Jump to content

ዙር

ከውክፔዲያ

ዙርሥነ አምክንዮ ጽንስ ሐሳብ ሲሆን አንድ የተሰጠ አረፍተ ነገርን ክፍሎች በማዘዋወር አዲስ አረፍተ ነገር የምናገኝበት ዘዴ ነው።

ምሳሌ፡

ኢትዮጵያዊ ከሆንክ አፍሪቃዊ ነህ።

የዚህ አረፍተ ነገር ዙር፣

አፍሪቃዊ ከሆንክ ኢትዮጵያዊ ነህ።

ከላይ እንደሚታይ የአንድ አረፍተ ነገር ዙር ከዋናው አረፍተ ነገር ዙር ጋር ጥገኝነት የለውም። የመጀመሪያው አረፍተ ነገር እውነትም ሆነ ውሸት፣ ሁለተኛው አረፍተ ነገር እንዲሁ እውነትም ሆነ ውሸት ይሆናል። ነገር ግን አንድ መረዳት ያለብን ነገር፣ ዙር የግልባጭ ዙር ግልባጭ መሆኑን ነው። ስለዚህም ዙርና ግልባጭ ምንጊዜም አንድ ላይ እውነት ወይም ውሸት ይሆናሉ።

ደግሞ ይዩ፦