ዙር ግልባጭ
Appearance
በሥነ አምክንዮ "ዙር ግልባጭ" ማለት አንድን ዐረፍተ ነገር አዙረን ስንገለብጠው የምናገኘው አዲስ ዐረፍተ ነገር ነው። በተለይ ይህ የሚሰራው ለጥገኛ አምክንዮ ነው። ለምሳሌ የሚከተለውን ጥገኛ አረፍተ ነገር እንውሰድ፡
- አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ከ ሆነ፣ አፍሪቃዊ ነው።
የዚህ አረፍተ ነገር ዙር ግልባጭ እንዲህ ይገኛል፦
- አንድ ሰው አፍሪቃዊ ካልሆነ፣ ኢትዮጵያዊ አይደለም።
ከላይ እንደምንረዳው ሁለቱም አረፍተ ነገሮች እኩል ናቸው። በሌላ አነጋገር፣ አንዱ እውነት ከሆነ ሌላውም የግዴታ እውነት ነው። አንዱ ውሸት ከሆነ ሌላውም የግዴታ ውሸት ነው። ስለዚህ ዙር ግልብጥ ከዋናው አረፍተ ነገር ጋር እኩል ነው፣ ወይም አንድ ነው እንላለን።
ከዙር ግልብጥ በተጨማሪ ሌሎች የአምክንዮ አረፍተ ነገር አንቀሳቃሾች አሉ። የላዩን ምሳሌ ተከተለን እንመርምራቸው
- ግልባጭ (ኢንቨርስ): "አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ካልሆነ፣ አፍሪቃዊ አይደለም።" ይህ እንጊድህ የተሰጠውን አረፍተ ነገር ቀጥታ የሚገለብጥ ነው። ሆኖም ከዙር ግልብጥ ለየት ባለ መልኩ የመጀመሪያው አረፍተ ነገር ውሸት ይሁን እውነት አያገባውም። ከላይ እንደምናየው አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ሳይሆን አፍሪቃዊ ለመሆን ይችላል። ስለዚህ አረፍተ ነገሩ ውሸት ነው። ይሄ ማለት ግን የማንኛውም አረፍተ ነገር ግልባጭ ውሸት ነው ማለት አይደለም።
- ዙር(ኮንቨርስ): "አንድ ሰው አፍሪቃዊ ከሆነ፣ ኢትዮጵያዊ ነው።" የመጀመሪያውን አረፍተ ነገር ቀጥታ ስናዞረው ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ዙር ማለት የግልባጭ ዙር ግልባጭ ነው። ማለት የእውነትነት ዋጋው ከግልባጭ ጋር አንድ ነው። ስለሆነም ከላይ በተሰጠው ምሳሌ ዙር ውሸት ነው እናለልን።
- ተቃርኖ: "ኢትዮጵያዊ ሆኖ አፍሪቃዊ ያልሆነ አለ። " ተቃርኖ እወንት ከሆነ የመጀመሪያው አረፍተ ነገር ውሸት ነው ማለት ነው።
ከጎን የሚታየውን ቬን ዳያግራም ያስተውሉ። ከስዕሉ እንደምንረዳ ማናቸውም A ውስጥ ያሉ ነገሮች B ውስጥ አሉ። በሌላ አነጋገር
በሌላ ጎን B ውስጥ የሌለ ማናቸው ነገር A ውስጥ ሊኖር አይችልም። ይህ እውነታ በሒሳብ ምልክቶች ሲጻፍ፡
ይህ እንግዲህ ዙር ግልባጭ ነው። ስለዚህ የሚከተለውን እውነታ መናገር እንችላለን
- ≡
ለማጠቃለል ያክል፣ A ያመላክታል B እሚል አረፍተ ነገር ከተሰጠን የዚህ አረፍተ ነገር ዙር ግልባጭ አይደለም B ምንጊዜም አይደለም Aን ያመላክታል ።