የማልታ-ቡረት ሥልጣኔ

ከውክፔዲያ
ቡረት ሳይቤሪያ የተገኘ የዝሆን ጥርስ ቅርጽ

የማልታ-ቡረት ሥልጣኔባይካል ሐይቅ ዙሪያ በሳይቤሪያሩስያ የተገኘ ቅድመ-ታሪካዊ የሥነ ቅርስ ሥልጣኔ ነው።

በዚህ ስፍራ በተለይ ከቀንደ መሬት (ጥንት የጠፋ የዝሆን ዝርያ) በመጣ በዝሆን ጥርስ ብዙ እቃዎችና ቅርጾች ተሠርተው ተገኝተዋል። በጥንት የሥፍራው ኗሪዎች ቀንደ መሬቱን ያደኑት አዳኞች ይሆናሉ።

አውሮፓና ምዕራባውያን ሊቃውንት እንደ ገመቱ ሥፍራው የተሰፈረው ከ22,000 እስከ 13,000 ዓክልበ. ነበረ ወይም ለ9,000 ዓመታት በሙሉ ከዚያ ደረጃ በጣም አልተነሡም። እንዲሁም በነዚህ ሊቃውንት ዘንድ የሰው ልጅ ዘሮችና ቀንደ መሬቱ አንድላይ ከ42,000 እስከ 2,000 ዓክልበ. ድረስ ይኖሩ ነበር፤ ወይም በጠቅላላ ለ40,000 ዓመታት ሰዎች እጅግ ቀስ ባለ እርምጃ ኑሮአቸውን ያሻሸሉ ማለት ነው። ነገር ግን ይህ ዘመን 40,000 ዓመታት ሆኖ የተጻፉ መዝገቦች ከተጀመሩት 5,000 ዓመታት በ8 እጥፍ ይበልጣል፤ ይህ ሁሉ ረጅም ጊዜ የሰው ልጅ በአንድ ሁኔታ ያህል መቆየቱ ስለዚህ አጠያያቂ ነው። በዚያም ላይ ሰዎች የሚበዙበት መጠን በማናቸውም ጊዜ ከዚህ ዝግተኛ መጠን እጅግ መበልጡ ስለሚታወቅ፣ ዓለሙን በሙሉ ለመሸፈን በጥቂት ሺህ አመታት ውስጥ እንጂ 40,000 ምናምንት አመታት እንዳስፈለገ አይመስልም።

የቀንደ መሬቱ ስዕል

ልክ መቼ እንደኖሩ ያለ ክርክር ባይታወቅም፣ የተገኙት ጥንታዊ እቃዎች ትኩረት ስበዋል። የዝሆኑ ታላላቅ አጥንት ደግሞ ለቤቶቻቸው መዋቅር ይጠቅማቸው ነበር። የፈረንጅ አጋዘን ቀንድ ደግሞ ተገኝቷል።

በብዙዎች የዝሆን ጥርስ ቅርጾች ትንሽ ቀዳዳ ያላቸው ከአንገት ድሪ ተለበሱ። የወንዶች እቃዎች (መሣርያዎች ወዘተ.) ከምድጃው ወደ ቀኝ ተቀበሩ፣ ድሪያቸው በራሪ ይብራ ይምሰል ነበር። የሴቶች እቃዎች (የስፌት፣ መርፌ ወዘተ.) ወደ ምድጃው ግራ ተቀብረው ድርያቸው የሴት ምስል ነበር። በአውሮፓም በጣም ተመሳሳይ የሴት ምስሎች ተገኝተዋል፤ ግን የአውሮፓ ምስሎች ከፊታቸው ይልቅ ሰውነታቸውን በዝርዝር ቀረጹ። በነዚህ ሳይበሪያዊ ምስሎች ግን ከሰውነታቸው ይልቅ ፊታቸውን በዝርዝር ቀረጹ።